የመለስ አልጋ ወራሾች (ከተስፋዬ ገብረአብ)

July 19, 2012

Click here for PDF

ከተስፋዬ ገብረአብ

“መለስ ታመመ” የሚለውን ወሬ ተከትሎ፣ ኮማ ውስጥ መግባቱና መሞቱ እየተነገረ ሰንብቶአል። የወያኔ መንግስት ግን ወሬውን አፍኖ ለመቆየት ተጨናነቀ። መለስ ጀርመን ሃገር ላይPM Meles Zenawi ቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉ በአንድ ወገን ሲገለፅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቤልጅየም 10 ቀናት አልጋ ይዞ መሰንበቱ ተሰምቶአል። “አዲሳባ ገባ” የሚለው ተሰምቶ ሳያበቃ፣ “ብራስልስ ላይ መሆኑ ተረጋገጠ” ተባለ። ወሬዎቹ መልከ ብዙና ውል አልባ ነበሩ። ዞረም ቀረ መለስ ታሞአል። ከመለስ መታመም ጋር በተያያዘ እንዲሞትም ሆነ እንዲፈወስ የሚፀልዩ ተደምጠዋል። ከህይወት ልምድ እንደተረዳሁት ከሆነ፣ አምላክ የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ እጁን ስለማያስገባ የሁለቱንም ወገን ፀሎት የሚሰማ አይመስለኝም። መፍትሄው አበበ ገላው እንዳደረገው፣ እያንዳንዱ ለአላማው መሳካት አንድ ነገር ማድረግ ብቻ ነው።

እርግጥ ነው፣ መለስ በደም ካንሰር እና በአንጎል እጢ ህመም በመሰቃየት ላይ መሆኑ ተረጋግጦአል። በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው፣ ከዚህ በሁዋላ እንደቀድሞው ወደ ቢሮው ገብቶ ስራውን መስራት ይቸገር ይሆናል። እንደሚሰማው ከማንበብና ከመፃፍ እንዲገለል በሃኪም የተመከረው ከስድስት ወራት በፊት ነበር። ዞሮ ዞሮ መለስ በህይወት አለ። እንዲህ በአጭር ጊዜ ለህይወቱ የሚያሰጋው አለመሆኑም ይሰማል። እንደተነገረው ቀዶ ህክምናም አላደረገም። የአንጎል እጢውን በጨረር ሊያክሙት ሲሞክሩ ነበር የከረሙት። ቀዶ ህክምና ለመሞከር ጊዜው ገና መሆኑን ዶክተሮቹ ለመለስ ነግረውታል። ይህን መረጃ እንደ ጥሬ እውነታ በመያዝ ግን ስለ አጠቃላዩ የአካባቢያችን ፖለቲካ አንዳንድ ነጥቦችን ማንሳት ይቻል ይሆናል።
የመለስን መታመም ተከትሎ በኢህአዴግ የአመራር አባላትና በጄኔራል መኮንኖች መካከል የተፈጠረው መቧደን በጣም አሳሳቢና ለውይይት የሚጋብዝ ሆኖ ሰንብቶአል። አመራር አባላቱ የመለስ እድሜ አጭር መሆኑን በመገመታቸው ለህልውናቸው ሲሉ አይኖቻቸውን ወደ ምኒልክ ቤተመንግስት ልከው ከረሙ። አሁንም በሰራዊትና በሲቪል ባለስልጣናት መካከል የስልጣን ሽኩቻ ስለመኖሩ እየተፃፈ ነው። ኢህአዴግ ቀድሞውንም አንድነት አልነበረውምና ከመለስ መታመም ጋር ድርጅቱ በየአቅጣጫው ሲፈነዳዳ ታይቶአል። የመለስ አልጋ ወራሽ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉ ስሞችም በየሚዲያው እየተገለፀ ቆይቷል። ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ አዜብ መስፍን እና ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ቀዳሚ እጩዎች ሆነዋል።

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ የፃፈውን አይቻለሁ። የግምት ወይም የመረጃ ስህተት አለባቸው። ለአብነት በረከት ስምኦንና አዜብ መስፍን በአንድ ቡድን ውስጥ ሊሰሩ አይችሉም። በሁለቱ መካከል ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ጦርነት ተነስቶ ሰንብቶአል። አዜብ በሚዲያ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ገብታ በረከትን ለማዘዝ ሞክራ ነበር። በረከት በጣም በመበሳጨቱ፣

“አንቺን በዚህ ጉዳይ ውስጥ ምን ያገባሻል? ሚስት ብቻ መሆንሽን ለምን ትረሽዋለሽ?” ይላታል።

በበረከት ልቅ ንግግር እብደት ውስጥ የገባችው አዜብ በሃይለማርያም ደሳለኝ በኩል በረከት ላይ ተፅእኖ ለማድረግ ሞከረች። እዚህ ላይ ግን በረከት ችግር ውስጥ ገባ። ወደደም ጠላ ሃይለማርያም የበላይ አለቃው ነው። መንበርከክ ግን አልቻለም። የብአዴን ምንጮች እንደሚገልፁት፣ በረከት ስምኦን አኩርፎ ወደ እናት ክልሉ ዋና ከተማ ወደ ባህርዳር ኮበለለ። ስራውን ትቶ ባህርዳር አንድ ሳምንት እንደቆየ በአዲሱ ለገሰ ልመና እና ማግባባት ወደ አዲስአበባ ሊመለስ ችሎአል። የመለስን መታመም ተከትሎ በረከት ወላጅ አልባ ልጅ መስሎ ታየ። መለስ ከስራው ገለል ከማለቱ የተፈጠረ ቁጥር አንድ ሽኩቻ ነበር። አዜብ ሃይለማርያም ደሳለኝን መጋለብ መጀመሯ እውነት ነው። እዚህ ላይ ሃይለማርያም ወደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሳበበትን ዋና አላማም ለመረዳት ያሰችላል። ነባር ሚኒስትሮችና ትግሬ ያልሆኑ ታጋዮችን በዚህ መንገድ ከቤተመንግስቱ ለማራቅ ሃይለማርያም መልካም መንገድ ሆኖ ሊያገለግል ይቻለዋል።

የህወሃት ነባር የአመራር አባላት በዚህ ወቅት ይከፋፈላሉ ማለት ግን ለእውነት የቀረበ አይደለም። ከተከፋፈሉ ቤተመንግስት ውስጥ ማን እንደሚገባ ያውቃሉ። የምኒልክን ቤተመንግስት አንድ ጊዜ ከለቀቁ፣ ዳግም እንደማይመለሱባትም ይረዳሉ። ስለዚህ ህወሃት ለአራት ወይም ለሶስት ተከፋፍሎ ትርምስ ውስጥ እንደሚገባ መጠበቅ የዋህነት ነው።

ከተመስገን ትንታኔ የምስማማበት የብአዴን ተፎካካሪነት ጉዳይ ነው። በዚህ ወቅት አዲሱ ለገሰ እንደሚገመተው በጡረታ የተገለለ አይደለም። እንደ ጆርጅ ኦርዌል ውሾች ሸሽጎ ያኖራቸው ከፍተኛ መኮንኖች ካሉት ብልህነቱን ማድነቅ ይቻላል። ብአዴን ተሸፋፍኖና ተጠጋግኖ ያደፈጠ ድርጅት ነው። አብዛኞቹ የብአዴን ካድሬዎች ቁጭት ይሰማቸዋል። ህወሃትን የሚገለብጡበት አጋጣሚ ከተገኘ፣ ከመጠቀም አይመለሱም ተብሎ ይታሰባል። በርግጥ ከህወሃት የተሻለ ስርአት መገንባት ይችላሉ ተብሎ ተስፋ አይደረግም። ህላዌና ካሳ ሸሪፎ ከኢህአፓ መንፈስ ጋር አብረው ያሉ እንደመሆናቸው፣ ኢህአፓን ወደ ጓዳቸው ለመጋበዝ ይሞክሩ ይሆናል። መለስ ዜናዊ ዘግይቶም ሆነ ፈጥኖ በሞት የሚሰናበት ከሆነ የብአዴን አመራር አባላት ከባድ ፈተና ውስጥ ይገባሉ። ምክንያቱም የመለስ ዜናዊ መንግስታዊ ወንበር በሌላ የህወሃት ሰው የሚወረስ ከሆነ፣ ለብአዴን ታሪካዊ ውርደት ይሆንበታል። ብአዴን ለ23 አመታት የኢህአዴግ ምክትልነትን ወንበር ይዞ ቆይቶአል። ከ23 አመታት በሁዋላ ሊቀመንበሩ “በሞት” ቦታውን ሲለቅ፣ ብአዴን ሊቀመንበርነቱን መተካት ካልቻለ ለዘመናት የሚወነጀሉበትን አሽከርነት በማፅደቅ እነርሱም ወደ መቃብራቸው ያመራሉ። በግብፅ የቀበሌ አስተዳደር ውስጥ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ምንጊዜም ምክትልነት ቋሚ ቦታቸው እንደሆነው ሁሉ፣ ብአዴንም ምክትልነትን አምኖ ሳይቀበል አልቀረም። ከዚህ ውርደት ለመዳን ብአዴን ሁለት አማራጮች አሉት። የመጀመሪያው መለስ እንዳይሞት መፀለይ ሲሆን፣ ሁለተኛው የመለስን ወንበር ለመያዝ ሽምጥ መጋለብ ናቸው።

መለስ የሰራዊቱን ትግርኛ ተናጋሪ አመራር ለሁለት ከፍሎ ሲያስተዳድረው ነበር። በቀጥታ ሳሞራ የኑስ የሰራዊቱ አዛዥ ቢሆንም፣ በጎን ደግሞ ሌላ መዋቅር ዘርግቶ ቆይቶአል። ታደሰ ወረደ እና ወዲ አሸብር የሚባሉት ጄኔራሎች ከሳሞራ እዝ ውጭ ከመለስ ጋር ግንኙነት ነበራቸው። ታደሰ ወረደ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ድፍረቱም ብቃቱም ሊኖረው ይችላል። ወዲ አሸብር እብድ ነው። ምን ሊያደርግ እንደሚችል ከወዲሁ መገመት አይቻልም። የመለስን ልጅ ክርስትና ያነሳው ጄኔራል ወዲ መድህን፣ አቅሙ ባይኖረውም የታዘዘውን የመፈፀም ችግር የለበትም። እነዚህ ሶስት ጄኔራሎች አዜብና ቴዎድሮስ ላይ ሊደርስ የሚችል አደጋ ካለ ለመመከት ተወርዋሪ ሃይል ይዘው የሚጠብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። በተቀረ የህወሃት ጥቅምና ስልጣን እስካልተነካ ድረስ ሰራዊቱ ወደ ቤተመንግስት ታንክ ለማንቀሳቀስ አይገደድም።

ከመለስ መታመም ጋር ተያይዞ በኢህአዴግ ውስጥ ከብአዴንና ከህወሃት ነባር አመራር አባላት በቀር ለሽኩቻው ብቃት ያለው ሃይል ማየት አይቻልም።
ለመሆኑ በዚህ ወቅት የተቃዋሚ ሃይላት ቦታ የት ነው?

አንዳንድ ተቃዋሚዎች እራሳቸውን ከምርጫ ውጭ በማድረግ፣ “አዜብ ትተካለች፣ የለም ሃይለማርያም ነው” ሲባባሉ ስሰማ ጠጉሬን ማከኬ አልቀረም። በትግርኛ ተናጋሪዎች ቁጥጥር ስር የወደቀው መድረክ ራሱን እንደ አማራጭ በማየት ፈንታ፣ “የሚተካ የተዘጋጀ ሃይል የለም። መጥፎም ቢሆን መንግስት ያስፈልጋል” አይነት ህወሃትን የማዳን አዝማሚያ ያላቸው ይመስላል። “የአንድነት” መሪ ዶክተር ነጋሶ የሚሰማቸው ጠፋ እንጂ እሳቸውም እንደ መለስ ታመዋል። እግዜር ይማራቸው። “ኢህአፓ ምን እያሉ ይሆን?” በሚል ወደ ድረገፃቸው ገብቼ ነበር። “ኢህአፓ በአዲስ አበባ ወረቀት በተነ” የሚል ዜና ለጥፈዋል። ከ30 አመታት በሁዋላም የትግል ስልት አልቀየሩም። ፌስቡክ እና ኢሜይል በተስፋፋበት ዘመን ወረቀት መበተን ለምን ያስፈልጋል? በጥንት ዘመን ወረቀት መበተን ያስፈለገው ሌላ አማራጭ ስላልነበረ ነው። የዶክተር ፍስሃ እሸቱ የሽግግር ምክርቤት፣ “መለስ ሞቶአል፣ አረጋግጠናል” ብለው አውጀዋል። ፊሽ መቼም ችኩል ነው። አዲስ ናቸውና ከልምድ እየተማሩ ይሄዱ ይሆናል። የፖለቲካ ድርጅቶች ለዜና መሽቀዳደም የለባቸውም። ዜና መቅደም የጋዜጠኞች ስራ ነው። እንደ ሽግግር ምክርቤት አቅጣጫ ማሳየት ነው የሚጠበቅባቸው። በመሰረቱ የመለስ መሞት የችግሮች መፍትሄ አይሆንም። ከመለስ መወገድ በሁዋላ ስልጣኑን ህዝብ እንዲቆጣጠር ታክቲክና ስትራቴጂ መንደፍ ያስፈልጋል። በመጨረሻ የተስፋ አይኖች የሚያርፉት በታጠቁት ሃይሎች ላይ ነው። ኦነግ፣ ግንቦት 7 እና ሌሎችም ሃይሎች ተቀናጅተው አንድ የታጠቀ የጋራ ሃይል ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል። አለመረጋጋት ቢፈጠር የሚያረጋጋ ሃይል ያስፈልጋልና ይህ ለነገ ሊባል የማይገባ ተግባር ይመስለኛል። አንዲህም ሆኖ የሃይል ሚዛኑን ስመረምረው በአስፈሪ ጭጋግ ውስጥ ያለን መስሎ ይሰማኛል። ህወሃት ደክሞታል። የሚገፈትረው ግን አጣ። ተቃዋሚዎችም አልተደራጁም። መንገዱ ወዴት ያደርስ ይሆን? እንደ ፕሮፌሰር መስፍን፣ “እግዜር ያውቃል” ማለት ብቻ ይሆን የቀረን?

በጥንት ዘመን አንድ ጋዜጣ፣ “ማርክ ትዌይን ሞተ” የሚል ዜና አትሞ ነበር። ማርክ ትዌይን ለጋዜጣው በላከው የማስተባበያ ደብዳቤ፣ “ስለኔ መሞት የፃፋችሁትን ዜና አንብቤዋለሁ። ተጋንኖአል።” ብሎ ነበር። ምናልባት መለስ በቴሌቭዥን ብቅ ብሎ፣ ተመሳሳይ ነገር ይነግረን ይሆናል። የሚበጀው ህወሃት እንደ ስርአት ይሞት ዘንድ፣ ታክቲክና ስትራቴጂ ነድፎ መትጋት ብቻ ይመስለኛል።

19 Responses to የመለስ አልጋ ወራሾች (ከተስፋዬ ገብረአብ)

 1. አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ Reply

  July 21, 2012 at 4:27 pm

  እነዚህ በአግድሞሽ የትግሬ ጉጅሌን የሚያንቆላጰላጥሱት ተቃዋሚዎች ተብዬዎች ናቸው ጭራቸው ያልተያዘው::ከነዚህም አንዱ ተስፋዬ ገ/አብ ነው የወያኔነት ፍቅሩ ያልለቀቀውና በተቃዋሚ ከመ-ፈረጅ ይልቅ ከዳር ሆኖ የሚጣፍጡ ቃላትና መደበኛ ሐረጎችን እየሸመጠጠ የ”እኔም አለኝ”ቱልቱላውን ይነፋል:-ብዙዎችንም መጥቀስ ይቻላል::
  የኢትዮጵያ ሕዝብ እነዚህን የከይሲ ቡድን ደምሥሶ በምትኩ በሕዝብ የነጻነት ምርጫ ብቻ ወደፊት ለመራመድ እና መሪውን ለመምረጥ የሕይወት እና የደም መስዋዕትነት እየከፈለ ባለበት የፈተና ወቅት ቀስቃሽ ፅሁፎችን ከማቅረብ ይልቅ የተለቃለቀ የኋልዮሽ ጦማር ያቀርባሉ::ዶባቶ ብርሃኑ ነጋም ሆነ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ የአበበ ገላውን ዓይነት(የዳዊት አሎሎ-ለጎሊያድ)ባይሆንም በዚህ ወቅት ቃለመጠይቅ ብቻ ሳይሆን ሥልት እና አዳዲስ የትግል መመሪያዎችን በኢሳት እና በሬዲዮ በመጠቀም በየሳምንቱ ማጣደፍ ይገባል::ለመሆኑ የዲክታተሩ ለገሰ ዜናዊ በሥልጣኑ ላይ አለመኖር ለውጥ አያመጣም እስኪባል የስነልቡና ትግሉ ውስጥ አልተሳተፉም???እንዴትስ ባደባባይ እነአቦይ ሥብሃት ነጋ”…የነፋጢማ” እያሉ ቢያንስ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲያናፋ የምሁራን አፃፋዊ ፕሮፓጋንዳ እንጣ???አለቃ ተክሌ መልካም አመላካች ነው::
  ማጣደፍ ተገቢና አስፈላጊ ነው::ወረት አይደለም የመለስ ዜናዊ መንፈቀል የመጀመሪያው ሥራችን ነው:-አዎ ለውጥ ይጀምራል ኋላም ያመጣል::ሌሎች የሚያጣጥሉትን እንተወው እና አዎ ጭንቅላቱ ስለገማ ራሱ የመለስም የጀመረው ከዚያው ነው እንበል::ለማጠቃለል የአማርኛ መሽቆጥቆጥ ይብቃ ኢላማው ከፊታችን ይታየናል እዚያ የነበረውን ማውራት ይብቃ ቀጥታ ወደሕዝቡ ትንሿ ጠጠር እናተኩር እናላቃት ተራራውን ራሱ ሕዝቡ ይንደዋል:: እባክህ አቶ ተስፋዬ ገ/አብ በሰው በተለይም በሕዝብ ቁስል እንጨት አትስደድ በአሁኑ ወቅት::ለትግሉ የሚጠበቅብህን አስተዋፅኦ አበርክት እንጂ ያለፉትን ቅራቅንቦዎች እያጣጣምክ በአሁኑ ግዜ ለሕዝብ ከነጻነታችን በፊት አታቅርብ ካንተ ይልቅ ስለጉዳዮቹ የተሻለ ጠልቀው የሚያውቁ በአደባባይ ይመጣሉ::

 2. Girum Teshome Reply

  July 20, 2012 at 8:47 am

  DEDEB !

 3. miki Reply

  July 20, 2012 at 4:22 am

  keep up the good writing, tesfesh. But forget about EPRP or those non-sense of the 1960s politic group, who r responsible for all political problem in the country now. They still distribute flyer…dam ass!

 4. beth says Reply

  July 20, 2012 at 2:54 am

  The genocidal mercilessness we have never forget the bedeno, Arbagugu, the Gambella virtual geneocide you have committed on innocent Ethiopians who never did any wrong to you all but for your hate that they are Amhara and the as to the Gambellas simply their confrontation and stood for their legitimate basic rights.

  I like to remind you some similar past examples such as the genocide that was committed in Cambodia took 30 years but it did not go unpunished; the first genocide Turkish committed on Armenian Orthodox Christians, the second the Nazi fascist genocide trial still on going on individual basis one by one after all those years.

  By comparison our case is fresh and it is committed in the 21st century when civilization,technology and societies perception is advancing which makes the trial even easy and faster.
  So be warned we know our place and yours as well as others.

 5. Yohanis Girma Reply

  July 19, 2012 at 8:08 pm

  We Ethiopians we need change for everlasting but in other side we Find fault of each other, it’s big shame on all commentaries and ECADFORUM to post such analysis. B/s the time is not finding personal fault. We are looking freedom so better make Unity to refused this racist Wayne. Of course somebody make a mistake but we better forget the wrong thing and narrow the gap b/n us then all activist, bloggers, politicians, in/out of the country, If we painful truly to bring democracy in Ethiopia soon stop shot slang words for each other. Readers understand what the aim of each political analyst when they blame each other, I also as a follower of ECADF and other news sites confused somewhat who is stand in right way to bring freedom for Ethiopians.
  If we will continued criticise never we will bring freedom in this country so criticise better after freedom of Ethiopian peoples.

 6. tezebet Reply

  July 19, 2012 at 5:22 pm

  ተስፋየ ገ/አብ ምን የባጥ የቆጡን ያስቀባጥርሃል!! እንዴት አወቅህ በረከት ባህርዳር አኩርፎ መሄዱን?! ይህ የሚያሳየው ከእናት ድርጅትህ ወያኔ ጋር ጥልቅ የሆነ ግንኙነትህን ሲሆን፡ ያንተ ስደተኝነት የይስሙላ ነው!!
  ግን በነገራችን ላይ ስምኦን በረከት ባህርዳር የሄደው አማራ ነኝና አድኑኝ ሊል?!! አሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሀ!!!!
  ወያኔ በአማራ ስም የራሱን ሰዎች የሰገሰገበትን ብአዴንን የአማራ ድርጅት መስሎህ ልታጥላላ የምትሞክረው?! ብትፈልግ ብአዴን ሁለተኛው የወያኔው ስብስብ እነበረከት፡ እነ ሃይለማርያም፡ እነአዜብ፡ህላዊ፡….ወዘተ ምድረ ወያኔ ሰለሆነ እራስ በራሱ ቢጫረስ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ መልካም ይሆናል!!
  በመጀመሪያ እንደተመስገን ደሳለኝ በህዝብ መወደድና ከህዝብ ጎን መሰለፍና ለህዝብ መቆም፡ ከዚያ ሃሳብን መተቸት።
  ተስፋየ ማንነትህን ህዝቡ ጠንቅቆ ስላወቀ ተቀባይ ለሌለህ ነገር መለቅለቅህን ብትተው የተሻለ ሳይሆን አይቀርም!! ግን እንጀራ የማገኛበት ነው ካልክ ከቁም ነገር የሚቆጥርህ እንደሌለ ነው!!!!
  ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም ትኑር!!!!!!!!

  • M. W.A. Reply

   July 20, 2012 at 3:56 am

   Maybe Tesfaye gets his information from Newaye GebreAb.

  • solomon Reply

   July 20, 2012 at 7:21 pm

   Tezebt Can u hear me ?
   እኔ ተስፋየን እወደዋለሁ።ተስፋየ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ ነው።ተስፍሽ አገራችን ነጻ ስትሆን አብረን በቀያዮቹ ዛፎች ስር እንሸራሸራለን።ተባረክ።ከላይ የጻፍከውን ትንታኔም ወድጄዋለሁ።ሌላም ጨምር።ዝምም አትበል።አመሰግንሃለሁ።

 7. getachew Reply

  July 19, 2012 at 5:20 pm

  a new religion is imposed on ethiopian muslims. they do not want to accept as a result they are leblled as terriorist. and they are killed arrested, suffering , what is the consequence. may it become peaceful?

 8. misraq Reply

  July 19, 2012 at 3:52 pm

  There is no difference between BEADEN and TPLF may be individual ambition to be a PM even this individual interest is dealt with in 1991.The current system works – TPLF PM, BEADEN deputy PM, and OPDO an Oromo a President and will continue to work. Fighting to change just this arrangement is too foolish thing to do and entirely meaningless. So the possibility is near zero.

  If there is change it will come from TPLF itself only. So far TPLF moderators are outside TPLF in MEDREK or ARENA. Both are unable to rally all peoples together. There are rumours on Arkebe or a faction contending for power but it is only rumours. What is left is TPLFs in the Military who may take over if internal chaos follows Meles’s
  death. So here is where OPDO and BEADEN wing of the military can do miracles and this is what cunning T G/ab wants us not to see. (afer yibla!)

  Though it is difficult to defend toothless opposition and T G/ab’s contempt. His comment on professor Mesfin’s leaving it for “God” is on the mark and hilarious.

  Ecadforum is fond of this man who is telling us no secrets and give us no analysis. Sorry for ECADForum

 9. Alex Reply

  July 19, 2012 at 3:49 pm

  Bereket going to Bahirdar, because Azeb pushed him via Hailemariam? So difficult to believe that. Hailemariam is a puppet and whatever he says, not even the lowest rank of weyane cadre will take him seriously, let alone Bereket. So, Tesfaye u’d better come up with something else why Bereket went to BD, if at all he did.

 10. beth says Reply

  July 19, 2012 at 3:14 pm

  Ato Tesfaye, let me tell you one thing you should always remember is we Ethiopians are the owners of our land/property/country/identity, because it is our birth right it is our God given right, but not rationing by TPLF and EPLF ok!. So do not preach us your racist and colonialist dirty ideology about our affairs and how to lead our life.

  We know our national/international legitimate, legal and human rights, we also know how to govern our selves. We do not need your unlawful interference in our private life. This is not your concern it is ours so you have to stop by now because you have insulted us enough for 21 years since your narrow minded racist ethnic managed to pull through by the help of the west who hate Derge regime for its socialist ideology.

  Also I like to remind you that the enemy of Ethiopia such as Ghadafi, Saddam and the like they have never succeed for ever hence, every body has his time God willing.

  Till then leave us alone and do your dirty tricks away.

 11. ANDENET Reply

  July 19, 2012 at 2:27 pm

  Look this guy!He really fears very much!This man is trying 2 inform 2 his former masters his paranoid!He knows what he has done on this community.What a lie!can anyone imagine Berket has been in Gojjam &came back after being begged by…?!What a nonsense look??!!U better keep silent at least on these political issues.There is no word in your vocabulary after all.U are using your pen 2 hurt those whom u think r your enemies!!!!!!!!

 12. ZerYihun Dandibo Reply

  July 19, 2012 at 12:47 pm

  Tesfaye,

  You have a hangup against EPRP. I can guess what the reasons are but it don’t matter for now. Distributing leaflet/flyers is NOT to be comapared to facebook or emails as your highness know-it-all thinks. In current day Ethiopia, for that matter your Eritrea as well, how many people have access to the internet leave alone facebook etc? The answer is in your reply for what eprp did. So, time again for you to eat your words raw!!

  Hope this helps you

  ECAD Forum Admin,

  You always remove my comments which are in support of EPRP. If you are runing a public web then please have the descency to let other views expressed even though you don’t agree with or approve of them.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>