ተስፋዬ ገብረአብ ከሚበጀው የሚፈጀው

July 7, 2012

ፍትህ
ዓለማየሁ ገላጋይ

ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ሰሞኑን የኖህን ልጅ ካምን ሆኖ ከረመ ማለት ይቻላል። አባቱ ኖህ በወይን ጠጅ ሰክሮ እራሱን በማይቆጣጠርበት ጊዜ እራቁትነቱን (ነውሩን) ያየውን ካምን… አይቶ ያልበቃውን፣ ወንድሞቹም የአባታቸውን እራቁትነት አይተው እንዲሳለቁ የጋበዘውን ካምን… ይህን በማድረጉም ዘር ማንዘሩ በአባቱ የተረገመውን ካምን… ተስፋዬ ሆኖ ከረመ። ካምን ለመሆን ህሊና ቢስነት እንጂ ሌላ ችሎታ አለመጠየቁን ተስፋዬ የተረዳው አይመስልም። ድፍረት እንጂ ብልሃት ግድ እንደማይል የገባው አይመስልም። ይህም በሚያቀርባቸው ቁንፅል ታሪኮች ላይ በጉልህ ይነበባል።ተስፋዬ ገብረአብ ከሚበጀው የሚፈጀው
ተስፋዬ ገብረአብ ሰሞኑን ካምን የሆነው እንዲህ ነው። ባትወልደውም ያሳደገችውን አገር የታሪክ ጉንፍ እየገላለጠ እራቁትነት ለማየት እጅግ በመጣር ላይ ይገኛል። ለማየት መጣሩ ሳይበቃው ሌሎችም እንዲሳለቁ ‹‹የቅዳሜ ማስታወሻ›› ብሎ በሰየመው ብሎጉ በመጋበዝ ላይ ነው። በተለይ አፄ ምኒልክን፣ አፄ ኃይለሥላሴን፣ እቴጌ ጣይቱ እና እቴጌ መነን የቀጥታ ተጠቂ ለማድረግ ፍላጐት እንዳለው በጉልህ ይታያል። ከእነሱ በሰተጀርባ ደግሞ እኛን ኢላማ አድርጓል፡፡ ‹‹የንጉሠ-ነገሥቱ እናት››፣ ‹‹የጎጃም ልዕልት›› እና ‹‹የመነን አራተኛ ባል›› በተሰኘ ፅሁፉ እነዚህ አጤዎችና ንግሥቶች ላይ ቦጫቂ የንሥር ጥፍር የመሰለ ብዕሩ ሲያንዣብብ በገሃድ ይስተዋላል። እንዴት? ለምን? ምን ፍለጋ? ምን ለማትረፍ? ይሄን ከመፈተሻችን በፊት ተስፋዬ ገብረአብን በጥቂቱ ለማየት እንሞክር።

የማይታበለው ነገር ተስፋዬ ገብረአብ ለአማርኛ ሥነ-ፅሁፍ ባለውለታ ነው። ‹‹ያልተመለሰው ባቡር››፣ ‹‹የቢሾፍቱ ቆሪጦች›› እና ‹‹የቡርቃ ዝምታ›› የተሰኙ ልቦለዶቹ እንደውርዴ ከወላጆቻቸው የወረሱት የዘር ጠባይ ቢኖርባቸውም የትረካ ጥበባቸው ቅርሳችን መሆኑን መካድ አይቻልም። እንዲሁም ሁለት ‹‹ባለቅፅ›› መጽሐፎችንም አበርክቶልናል። ‹‹ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ›› እና ‹‹እፍታ›› የተሰኙት እነዚህ ‹‹ባለቅፅ›› መጽሐፎች ተስፋዬ የጡት አባት ሆኗቸው በጉዲፈቻነት ባያሳድጋቸው ኖሮ ምናልባትም የሥነ- ፅሁፍ አፀድ ውስጥ የማይቀበሩ በጨቅላነት የተቀጠፉ በሆኑ ነበር። ከእነዚህ ሁሉ በኋላ ደግሞ ሁለቱ ‹‹የጋዜጠኛው›› እና ‹‹የደራሲው›› ማስታወሻዎች ተከትለዋል። የዘር በሽታው ካንዱ ሥራ አንዱ የማይሻል ቢሆንም በሁለቱ ‹‹ማስታወሻዎች›› ላይ ተስፋዬ ለጋነቱን አጥቶ፣ እንደዛፍ ተንጋዶ መብቀሉ በጉልህ የሚስተዋልባቸው ሆነዋል።

የተስፋዬ ገብረአብ አብዛኞቹ ሥራዎች (ብሎጉን ጨምሮ) እንደ ገጠር ሴትወይዘሮ መኳኳያቸው ‹‹ጥላሸት›› ነው። ‹‹ጥላሸቱ›› ደግሞ ከስም ማጥፋት ጥቀርሻ የሚገኝ ነው። ይሁንና ሥራዎቹ ገና በፈገግታ ሲቀርቡን ጉራማይሌአቸው የጥላሸት እንዳልሆነ ሁሉ በውበት ይጠልፉናል። ተስፋዬ ‹‹የሚነቅስበት›› የራሱ የሆነ የቋንቋ እሾህም አለው። እየጠቀጠቀ ከሚያደማው ‹‹ድድ›› ሆነ ‹‹አንገት›› ውስጥ ከማዝጐርጐር የሚመነጭ ውበት ያፈልቃል። ይሄንን ደግሞ ተስፋዬ ያውቃልና የስም ማጥፋት ጥቀርሻውን ሆነ መጠቅጠቂያ እሾሁን አይጥልም። ‹‹የጋዜጠኛው ማስታወሻ›› ላይ ስለመኳኳያ ‹‹ጥላሸቱ›› እንዲህ ይላል።

‹‹በዚህ መጽሐፍ ባልተለመደ ሁኔታ እውነተኛ ስማችሁን ለተጠቀምኩ ሁሉ ባለማስፈቀዴ ይቅርታ እየጠየቅሁ፤ አትቀየሙኝም ብዬ በመገመቴ ደግሞ አመሰግናለሁ።››
ከእጅ ያፈተለከ የጫካ እርግብ ይመስል መጽሐፍን ያህል የረጅም ዘመን ነዋሪ በዘፈቀደ መልቀቅ ከባድ ጥፋት ነው። ተስፋዬ ገብረአብ ሆን ብሎ ለሰራው ጥፋት ይቅርታውን የጥፋቱ አባሪ አድርጐ መልቀቁ ደግሞ ትልቅ ሹፈት ይሆንብናል። ተስፋዬ የጥፋቱን ጥፋትነት ቀድሞ ቢረዳውም እራሱን ገስፆ መተው የሚችል አይመስልም። ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው። የተጋባበትን ሳይሆን የለማበትን አንጡራ ባህርይ ስለሚያስተናግድ ብቻ ነው። ልጅ ሆኖ በእናቱ ላይ ያደረገውን ‹‹የደራሲው ማስታወሻ›› ላይ እንዲህ ይተርክልናል። ንዑስ ርዕሱ ‹‹የልጅነት ተራሮች›› ነው።

የጓደኛው የነብዩ አባት ኢሬቻን ለማክበር ወደሆራ እየወሰዱአቸው ነው። መንገድ ላይ ስለክብረ በዓሉ መልካም መልካም ነገር ይነግሯቸዋል። ተስፋዬ በጨዋታው መካከል ገብቶ ‹‹እናቴ ግን እንዲህ አልነገረችኝም›› በማለት ክብረ- በዓሉን የሚያጥላላ ነገር ይዘበዝባል። የነብዩ አባት ይሄን በሆዳቸው ይዘው ወደ ተስፋዬ እናት ይሄዳሉ። በነገሩም ላይ ይነጋገራሉ። ሰውዬው ገና እግራቸው ከቤት እንደወጣ እናት ከጉማሬ ቆዳ የተሰራውን አለንጋ አንስተው ተስፋዬ ላይ ይወርዱበታል። ‹‹ስትገርፈኝ እንዲህ እያለች ነበር›› ይላል፡ –

የቤትህን ምስጢር ደጅ እያወጣህ ትዘረግፋለህ? ጅላጅል የሆንክ ፍጡር። ለሰው የሚነገርና የማይነገረው መቼ ይሆን የሚገባህ? በችግር ጊዜ ከሚደርሱልኝ፣ ተከባብረን ከኖርነው ጐረቤቶቼ ልታጣላኝ! ጅል!፣ ልጅ የሆንክ ፍጥረት… (ከገፅ 38-39)

ተስፋዬ ገብረአብ በመጽሐፎቹና በብሎጉ ሥማቸውን ካነሳቸው አራት ግለሰቦች ጋር በጉዳዩ ላይ አውርቼአለሁ። የእናቱን እሮሮ ነው ሁሉም የደገሙልኝ። በተለይ አንደኛው ‹‹ለምን እኔን ማጥቂያ ያደርገኛል? ስለምን ከሚጐዱኝ ሰዎች ጋር ያያይዘኛል?›› ነበር ያለኝ። ቀላል የሚመስሉ ግን ከባድ የሆኑ የእናቱ ሮሮዎች ተስፋዬ እስካለ ድረስ ለመቀጠላቸው ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለበትም። እናቱ ካሉት ውስጥ ‹‹ጅል›› የምትለው ቃል ብቻ የምትታመን አይሆንም። እናት በመሆናቸው የልጃቸውን ጥፋት ከጅልነት ቆጥረውታል፣ ካልሆነም ተስፋዬ ለማደናገሪያነት እናቱ አፍ ላይ ቃሏን አኑሯታል እንጂ ተስፋዬ ጅል አይደለም። ውጤቱን እየገመተ ብቻ ሳይሆን ቀድሞ እያወቀ የሚያደርግ ለመሰሪነት የቀረበ ሰው ነው።

ተስፋዬ ገብረአብ የአካባቢ ተቆርቋሪ ይመስል ከውድቅዳቂ የታሪክ ፌስታል ቆሻሻ ኢትዮጵያዊ ዘንቢል የመስራቱ የሰሞኑ ሙከራ በጅልነት የተፈፀመ አይደለም። ያስወነጨፈብን ጫፉ የክፋት መርዝ የተቀባ የጠላትነት ቀስት ነው። በሚያመረቅዝ የሐፍረት ቁስል ሊመታን ሆን ብሎ የታሪክ ምሁራንን ከለላ አድርጐ ሰንዝሮብናል። ቁንፅል እውነታዎችን በመቅመል መላው ታሪካችንን የውቤ-በረሃ ገድል ሊያስመስለው ሞክሯል። ነገሥታቱን፣ መኳንንቱንና ሴትወይዘሮዎቹን ለድሪያ ብቻ የተፈጠሩ አሻንጉሊቶች በማድረግ ከኢትዮጵያ ውስጥ በታሪክ መኩራትን ጠራርጐ ለማጥፋት አልሞ አንዲት የዶሎዶመች ሙሬ አዘጋጅቷል።

ኢትዮጵያዊ የስብዕና ነውጥ በመሻት ከታሪክ ነቁጥ ተነስቶ የፃፈው አንዱ ሥራው ‹‹የንጉሠ ነገሥቱ እናት›› የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል፡፡ የሚተርከው አጤ ምኒልክ ‹‹ከሥራየ ቤት›› (ገረድ) ስለወለዷት ሸዋረጋ ነው። ገና በእናቷ ሆድ ሳለች ከአጤ ምኒልክ እንደተረገዘች ያወቁት እቴጌ ጣይቱ ከቤተመንግሥት እንዳባረሯት ይተርካል። የሰባት አመት ልጅ ሳለች እናቷ ስለሞተችባት እንዴት የመከራ ጊዜ እንደገፋች ያጫውተናል። በመጨረሻ ወታደር አግብታ ሐረር ስትኖር የአባቷ ስም ማተቧ ላይ ተፅፎ በመገኘቱ ባሏ ወደቤተመንግሥት ያመጣታል። አጤ ምኒልክ ከልጃገረዶች መካከል ይለይዋታል፣ ለራስ አሊም ይድሯታል። በ1888 ዓ.ም. ልጅ እያሱ የተወለደው ከሸዋረጋ እንደሆነ ይነግረናል።

እዚህ የተስፋዬ ትርክት ውስጥ ፅሁፉን ወደ ውሸትነት ሊለውጥ የሚችል ከፍተኛ የዘመን ዝንፈት ይታያል። ሸዋረጋ ስትረገዝ እናቷን ከቤተመንግሥት ያባረሯት እቴጌ ጣይቱ እንደሆኑ በገደምዳሜ ተነግሮናል። እንዲያ ከሆነ ጉዳዩ የተፈፀመው ከ1876 ዓ.ም. ወዲህ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም እቴጌ ጣይቱና አጤ ምኒልክ ተገናኝተው የተጋቡት በዚህ ዘመን በመሆኑ ነው። ሸዋረጋ እንደው ከአመት በኋላ ተወለደች ቢባል እንኳን ከ1877 ልጅ ኢያሱን እስከወለደች ጊዜ (1888 ዓ.ም) ያለው ዕድሜ ገና አስራ አንድ ዓመት ብቻ ይሆናል። ተስፋዬ፣ ሸዋረጋ ወታደሩን ያገባችው ለአቅመ ሔዋን ደርሳ መሆኑን ደግሞ ነግሮናል። ታዲያ እንዴት በአስራ አንድ አመት ዕድሜዋ ልትወልድ ቻለች? ድሎት በዝቶ የሴት ወጓን ቀድማ አየች እንዳይባል ሸዋረጋ በችግር ተቆራምዳ ያደገች ናት። ታዲያስ? እንዴት? በምን?…

ሙግት እንጂ ስድብ በመረጃ አይደገፍም። ተስፋዬ ገብረአብ ከዘመኑ አፋትቶና አፍኖ እዚህ ዘመን ያመጣው ታሪክ ለዚህ ትውልድ ነውር የሚመስል ጥቃቅን ነገር ስላለበት ብቻ ሙሉ ትኩረቱን የሰጠው ታሪኩን አቅርቦ አንጡራ ኢትዮጵያውያኑን ማሸማቀቁ ላይ ነው። ከዚያም ኢትዮጵያዊ ኩራትን ሰብሮ ሀገር ተከላካይነትን ማዳከም። ከዚያስ? ተስፋዬ ገብረአብ ታሪካችንን ከክብሩ አውርዶ የሴትና የወንድ ‹‹ሎሚ ውርወራ›› ብቻ ለማስመሰል የጣረው ተደጋጋሚና አንድ አይነት ቁመና ያላቸውን ታሪክ ነክ ፅሁፎች በማቅረብ ነው። ‹‹የጎጃም ልዕልት›› የተሰኘው ፅሁፉ በንጉሥ ተክለኃይማኖት ልጅ የተነሳው መኳንንታዊ የጋብቻ ውርክብ እንዴት ለአጠቃላይ ጦርነት አስግቶ እንደነበር ይተርክልናል። በመጨረሻ አጤ ምኒልክ እንዴት እንደቋጩት ይነግረናል። ከቁመታቸውም፣ ከወርዳቸውም ቀናንሶ ለመፍጠር የፈለጋቸውን አጤ ምኒሊክ በዘዴ ያስተዋውቀናል።

‹‹የመነን 4ኛ ባል›› የተሰኘ ፅሁፉ ደግሞ ያነጣጠረው አጼ ኃይለሥላሴ ላይ ነው። መነን በፊት ሁለት አግብተው ፈትተዋል ይለናል። ልጆችም አሏቸው። በኋላ ሦስተኛ ትዳራቸው ላይ ሳሉ ነው ልጅ ኢያሱ አፋትቶ ለራስ ተፈሪ ሲድራቸው የምንመለከተው ‹‹አምላክ በዚሁ በቃሽ ይበለኝ›› በማለት አራተኛ ትዳራቸውን የተቀበሉት እቴጌ መነን ዘመኑና ዘመነኞቹ ያደረሱባቸው ‹‹ጥቃት›› አጥንታችንን ሰርስሮ ይገባል። ይሄ እንግዲህ ተስፋዬ ገብረአብ ቆንፅሎ እንዳቀረበው ሁሉ ነገሩን ከሁኔታዎች ነጥለን ስንመለከተው ነው ሀፍረት እንዲሰማን የምንሆነው። ከዚያ ውጭ ግን ነገሩ ሌላ ነው። የዚያ ዘመን ፖለቲካዊ ሀይል የሚመነጨው ከዘር ብቻ ነበር። በመሆኑም አካባቢዎችና ግዛቶች ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ተሳስረው የሚቆዩት በፍትሃዊ የበጀት ክፍፍል ሳይሆን በሚዛናዊ የትዳር ስርጭት ነበር። ሁሉም አካባቢና ግዛት የጋብቻ ዝምድናንና መዋለድን ለዙፋኑ የነገ ተስፋ በዋስትናነት ከያዙ ብቻ የሰላሙ ተባባሪዎች ናቸው። ስለዚህ በንጉሠ ነገሥቱና በመኳንንቱ አካባቢ የነበሩ ሴቶች እንደ ዋነኛ የፖለቲካ መሣሪያ መታየታቸው ግድ ነበር ይሄ በእኛ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓውያን ታሪክ ውስጥ ቦታ ያለው ክስተት ነበር። የሔነሪ ስምንተኛን ታሪክ ማንበብ በቂ ነው።

የተስፋዬ ገብረአብ በዚህ ዘመን አስተሳሰብ ለማስዳኘት ከታሪክ ጋር የመካሰስ አዝማሚያ ጅልነት ሳይሆን፣ መሰሪነት እንዳለበት እንድንጠረጥር የሚያደርገን ይሄ ነው። ተስፋዬ ያለጥርጥር ከታሪክ ነቁጥ ኢትዮጵያዊ የስብዕና ነውጥ ለመፍጠር በመሞከር ላይ ነው። በተስፋዬ ገብረአብ መስገር ሁልጊዜም የሚፈልገው ቦታ የሚደርሰው ጀርባውን የተከራየው አካል እንደሆነ ግልፅ ነው። ተስፋዬ የራሱ መዳረሻ የለውም። ተስፋዬን እዚህ ታሪክ የመቅመል ሥራ ውስጥ የከተተው ጀርባን አከራይቶ የመኖር ፈረሳዊ ጣጣ ነው። ጋላቢው መንፈስ በግልፅ እኔ ነኝ ባይልም ከተስፋዬ አሰጋገር አስጋሪውን መለየት የሚያዳግት አይደለም። ግን… ግን ተስፋዬን ያለጋላቢ የማይሰግር ‹‹የጋማ-ከብት›› አድርጐ አጉልኛ የገራው ማን ይሆን? እሱ እንደሚለው ባንወልደውም አሳድገነዋልና ጀርባን አከራይቶ የመኖር ፖለቲካዊ ስብዕናው የእኛም መሰደቢያ ገመና ሳይሆን ይቀራል? ‹‹አሳዳጊ…›› በሚል የገመና ተጋሪዎቹ መሆናችን እርግጥ ነው፡፡

26 Responses to ተስፋዬ ገብረአብ ከሚበጀው የሚፈጀው

 1. tekalign Reply

  October 29, 2013 at 3:19 am

  ተስፋዬ ገብረእባብ የሻዕቢያ ኤጀንት ነው ። ደሞዝ የሚከፈል አጥ ስራውና በላፊነቱ የኢትዮጵያን ታሪክ ማጉደፍና የዘር መርዝን መርጨት ነው ። ዱሮ በጠዋቱ የዚህን የእባብ እንቊላል ማንነት የተረዳን ስለመርዛምነቱ ስንናገር የወያኔን ምስጢር ስላወጣ የምትቃወሙት ወያኔዎች ናችሁ ተባልንና ወያኔነት ተፈረጀብን።

  ተስፋዬ ገ/አባብ የሚጠሓበት ገንዘብ ካስገኘለት እናቱን የሚሸጥ ኦፖርቹኒስት ነው ።

 2. tezebet Reply

  July 11, 2012 at 7:46 am

  አቶ ዓለማየሁ ገላጋይ እግዚአብሄር የኢትዮጵያ አምላክ ይባርከዎት!
  ካሁን በፊት ስለ ኤቴጌ ጣይቱና ስለ እሥራኤል አንድ ጽሁፍ ጽፎ በ EMF ወጥቶ መሰሪና መርዛማ ጽሁፍ መሆኑን፡ በተለይም የኢትዮጵያዊነትን ታሪክ የሚያጎድፍና፡ ኢትዮጵያዊነት ወኔን የሚሰልብ መሆኑን በማስመረኮዝ የተስፋየ ገ/አብ የጀርባ ሁኔታ በደንብ ይጣራ! መድሃኒት የማይገኝለት የጥቁር እቫቭ መርዙን ህብረተሰቡን መስሎ እየረጨ ነውና ጥንቃቄ ያሰፈልጋል!ህዘቡም ሊነቃ ይገባዋለ ብየ ነበር!!ያኔ ታዲያ ባልሸነፍላቸውም አንዳነዶች ሲደገፉኝ አብዛኛዎቹ የወያኔ ቡችሎች እጣታቸውን አሹለው ሞገቱኝ። ግን የይሁዲው ልጅ ፈንክች አላልኩመ።
  (ስለ እሥራኤል የሰጠሁትን መለስ ግን አላወጡትም፡ይመስለኛል ከሚገባው በላይ በማያውቀው ገብቶ ስለፈተፈተ ዘለፌው ነበር)
  አሁንም ለዚህ የጥቁሩ ዳግማዊ ሂትለር (መለስ)አቀንቃኝ በቃ ልንለው ይገባል!!! “ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው አሰስቀድሞ መምታት አሾከሿኪውን” ነው! እንደተባለው፡ እንደዚህ አይነቱን በእሳር ውስጥ የሚሽሎከለክ እቫቭ እዚያው እሳሩ ጋር ማቃጠል ተገቢ ነው!! ብዙ ጊዜ እሳር ውስጥ ያለ መርዛማም እቫቭ ሰውን ሲጎዳ አይታይም። በመሆኑም ሳሩንም ማቃጠለ የግድ ይላል!! ይህ በምሰኪን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስም ወጥቶ ለወያኔ ተልዕኮ አስፈጻሚ ነው!! በቃ!! ተነቃብህ ልንለው ይገባል!!
  ኢትዮጵያ በጀግና ልጆቿ አንድነት በክብር ለዘልዓልም ትኑር!!!!!!!!!!!!!!

 3. ethiogadarmy janderebaw zeriay Reply

  July 10, 2012 at 5:33 pm

  yene clinton ena monica, ye lielt diana ,IMF peresedent kilet firachaw lezarewochu new ? Yesew lesew mels ymeslegnal akafan akafa bemaletu yejundin sado gemena ayinet azagn kibe anguach neh yadefe yegodefe sint yetafene yeweyane good meche teneka ¡¡¡

 4. adane Reply

  July 10, 2012 at 7:42 am

  10 Q ዓለማየሁ ገላጋይ.የተስፋዬን ከለበስ ለምድ ስላወጣኸው፡፡

 5. circle-7 Reply

  July 9, 2012 at 4:40 pm

  Alemayheu Gelagay, thank you so much for the well written article. Few of us saw this coming and voiced our concern when he first puplished his memior. Unfortunately people were not ready to hear our concern at that time. I am glad people are recongnizing his true color now. Thank you for helping people understand about the war wedged against Ethiopianism.
  With God’s help, Ethiopia shall prevail!!

 6. Mahder Reply

  July 9, 2012 at 11:53 am

  This is excellent and long overdue discussion of Tesfaye’s sinister motive. We made him to be what he was not and now let us know him for what he truly is. Although he effectively used the mask of being a good writer that we should admire, he has been working hard to divide and denigrate our people. It is high time to put him in the dustbin where he belongs. The various web sites that give Tesfaye a forum to harm Ethiopis should refrain from allowing him to spread his unsubstantiated and evil allegations.

  Mahder

 7. Girum Teshome Reply

  July 9, 2012 at 10:16 am

  አለማየሁ አውነተኛ ነው የምትነግረን እኛም ባነን ነበር ነገር ግን የመጣፍ ችሎታው የለን ሆኖ ነው።እነደው እባካችሁ ይህንን ሰው አንድ በሉት በፖለቲካውም በኩል እንደዚሁ ውስጣችንን እየወጋን ነው . . . . ለመሆኑ እወዳቸዋለሁ የሚለው ምሁሮች እንደየት ዝም አሉ?ወይስ እንደኛው መሀይሞቹ በቃላት ክሸናው እየተሸወዱ ይሆን መልሱን ለተስፋየው ?
  . . . . . …እኛ እንደሰው ስንገምት እሱም እንደነገረን ሀያቱ ሁሉ የተቀረጠው ላለቃ ማጎብደድ ስለሆነ ጎበዙ ተዋግቶ ሲመጣ እሱ ከሚንሲ ቤት እየተጠራ ከውጊያ ተደብቆ የሚያነበውን መጣፍ ይተርክላቸዋል አለቆቹም የገብሶ ኣረቂ መለኪያ ከጃቸው ወደ ላይ ከፍ አድርገው ምላሰን ከላንቃቸው እያጋጩት . . .(ምጣጣ..ምጣጣ )….አየ ደራሲ አየ ጋዚጠኛ እያሉ ሰቀሉት…….ይኸው ማን ያውርደው?መውረድም ቢያቅተው በዛገ በወዳደቀ ዱልዱም አምሞ ላያም ነቁሮ ላይነቁር መደብደቡነ ተያይዙዋል ….እና ታዲያ ዐለሜ እባክህ ጨምር ጨማምር ቁስላችንን እከክልን ሊድን ይሆን ሚያሳክከን?؟

 8. Robele Ababya Reply

  July 9, 2012 at 8:20 am

  I thak Ato Alemayehu Gelagay for his enlightening excellent article. Tesfaye’s useless pieces of writings expose his little mind bent on spreading farce. Let us ignore him and focus on our noble task of rebuilding our Ethiopia by ending tyranny in the region perpetrated by Meles and Isaias.

 9. gelanew kirar Reply

  July 9, 2012 at 6:19 am

  በነገራችን ላይ የሁለቱም፡ ኢሳያስም ሆነ መለስ፤ ሞት ቅርብ ነው። ሁለቱም ለአመታት ሲሰሩት በኖሩት ወንጀል የገዛ ህሊናቸው ሲያስጨንቃቸው የሚኖሩ፣ ደስታ የሚባል ነገር ያልዞረባቸው በዲፕረሽን ሲማቅቁ የኖሩ ሰዎች ናቸው። እንዲህ አይነት ሰው ደግሞ የበሽታዎች ሁሉ ጎተራ ነው። እናም “they both will die young” የነሱ መሞት ግን ብቻውን ለሃገር ምሉዕ መፍትሄ አይደለም። በየምናምንበት የተቃዋሚ ድርጅቶች መደራጀት እና አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን።

 10. gelanew kirar Reply

  July 9, 2012 at 6:10 am

  አለማየሁ ገላጋይን ከልብ ልናመሰግነው ይገባል። የተስፋዬ ስራ፣ በህይወት የሌሉትን ቀርቶ ያሉትን እና ውብ ሰብእና ያላቸውን ሰዎች (ቡልቻ ደመቅሳ እና ዶ/ር ነጋሶ…) ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ታች ለማውረድ ሆን ብሎ የሚሰራ የጭቃ ውስጥ እሾህ ነው። ሲፈልግ የራያን ኦሮሞነት በተዘዋዋሪ ይነግረናል። የኤርትራውን ኢሳያስ የጤና ደህንነት፣ የመለስን ክፉኛ መያዝ እና የመሞታቸውን አይቀሬነት በተዘዋዋሪ ይነግረናል። በቅርቡ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ያወጡትን “አንገት ሲደፋ ምን ፈሰሰ..” ጽሁፋቸውን ለይቶ ያወጣውም ፕ/ሩ የጻፉት እውነትነት ቢኖረውም፣ ስለ ኤርትራ እሱ በሚፈልገው መልኩ ስለተጻፈ ነው። ” የቤተመንግስት ሹክሹክታ…” በሚል የጻፈውንም፣ ጠንቃቃ አንባቢ ደግሞ ቢያየው፣ መሰሪነቱን በሚገባ ያውቃል። ተስፋዬ ሰብዓዊነትን አደንቃቸዋለሁ ከሚላቸው ከነበዓሉ ግርማ እና ስብሃት ገ/እግዚአብሄር ያልተማሪ እጅግ የሚታዘንለት ቆሻሻ ሰብዕና ያለው ሰው ነው። ይህን በተመለከተ በቅርቡ በሜድያ ብቅ እላለሁ።

 11. betti Reply

  July 8, 2012 at 4:36 pm

  Recentl, tesfaye has started to write about ethiopian king’s, and focused on some issues related to the respective king. why he is interested in writing very simple issues rather than their big history? why he is not mentioning any reference whatsoever? To me it seems he has a goal. As an Eriterian, he always wants a weak , or if possible no Ethiopia at all. He has a strong connection with shabeya. we should be very careful not take what he writes as facts, as they are mere fabrication.

  • alemayehu Reply

   July 10, 2012 at 7:07 am

   you called “as an eritrean” for whom do you try to chet? betti? kikikiki. you are one of the suporter of weyane tuges and leave alon ethiopia for the owners. you do not have moral to talk abot ethiopia.kikiki

 12. ANDENET Reply

  July 8, 2012 at 4:02 pm

  I have red Tesfaye’s many books&smaller pieces of writings.What I understood especially after reading is,he always uses his pen to preach hates systematically on any group whom he wants to attack.Look how much this guy has been taking sides 4 TPLF &preparing different documentary books so as to help this group.Then all of a sudden he turned his compass&began to attack his own colleagues .Even on his two d/t interviews with Addis dimts&ECADF he wants to give us the definition of being an Oromo means&he don’t consider Ato Bulcha Demeksa as an Oromo.Look at the reasons he gave.Dr Negasso is not an Oromo,Ato Bulcha too….Why ?B/c Tesfaye says so….Anyways what is in this man’s mind is sawing poisons b/n any groups or individuals he hated.Even when I think about the reasons b/c he is uneducated.He is reading many books &can write as well.No ethical things he can buy.Life is too short.Thank you anyways.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>