ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ! በአውሮፓ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ

May 8, 2012

Click here for PDF

የአፋር የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ከኢትዮጵያዊያን ኮሚውኒቲ በቤልጂየም፣ና የሉቅማን የኢትዮ ቤልጄያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ማኅበር በህብረት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ሰልፉ የሚካሄድበት ቀንና ሰአት፦ ሜይ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ከ13፡00 ሰዓት ጀምሮ

ሰልፉ የሚካሄድበት ቦታ፦ በብራስልስ አውሮፓ ካውንስል ፊት ለፊት

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ከዕለት ወደ ዕለት አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ ላይ እየደረሰ ይገኛል። በግለሰቦች ላይ ከሚደርሰው የመሰወር፣ የጅምላ እስራት፣ በድብደባ:ማሰቃየት፣ አፈና እና ግድያ፣ ከስራ መባረር፣ ንብረት መነጠቅ እና ሌሎች በደሎች ;…ወዘተ, በተጨማሪ የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን፣ የኃይማኖት ተቋማትን፣ የሙያና የሲቪክ ማኅበራትን፣ የሰብዋዊ መብቶች ድርጅቶችን እና የፖለቲካ ፓሪቲዎችን ኢላማ ያደረገ የጥቃት እርምጃ በተደጋጋሚ በመንግስት በኩል እየተወሰደ ይገኛል። ይህ ሁኔታም መፍትሄ ሳይበጅላቸው ለረዥም ዘመናት ከቆዩት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ቀውሶች ጋር ተዳምሮ አገሪቱን እጅግ አስፈሪ ወደሆነ ሁኔታ እያመራት ይገኛል። ነገሮች ሙሉ በሙሉ ከመንግስት ቁጥጥር ስር ወጥተው አገሪቱ ማቆሚያ ወደ ሌለው ቀውስና እልቂት ውስጥ ከመግቧቷ በፊት የአለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ተገቢውን ጫና በመንግስት ላይ ያደርግ ዘንድ ለማሳሰብ ይህን የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅተናል። በዚህም መሰረት ለአለም አቀፉ ማኅበረሰቡ የምናቀርባቸው ነጥቦች ሚከተሉት ናቸው ::

1,መንግስት የተለያዩ ሰበቦችን በመፍጠር በአገሪቱ የተለያዩ ማጎሪያ ቤቶች ያሰራቸውን የፖለቲካ እስረኞች ባፋጣኝ እንዲፈታ፣!!

2,መንግስት ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ሰበብ በሃሰት በአሸባሪነት ወንጅሎ ያሰራቸውን ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ባስቸኳይ እንዲፈታ፣

3, በአፋር ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላ እና በኒሻንጉል ክልል ውስጥ ልማትን ለማስፋፋት በሚል ሽፋን ዜጎችን ከመኖሪያ ቄያቸው የማፍናቀል እርምጃ ባፋጣኝ እንዲቆም፤, እንዲሁም ይህን የመንግስትን ሕገ ወጥ እርምጃ በመቃወማቸው የተነሳ ለእስር የተዳረጉ አርሶ አደሮች እና ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ባፋጣኝ እንዲፈቱ፣::

4,መንግስት በኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ጣልቃ በመግባት እያደረገ ያለውን ሕገ ወጥ ተግባር ባፋጣኝ እንዲያቆም፤ በተለይም በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ፣ ጫና እና ጣልቃ ገብነት ግዲያና ዛቻ እንዲቆም፣እና በኦርቶዶክ በተክርስቲያን ገዳማትና ታሪካዊ ስፍራዎች ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት እንዲገታ !!

5,ሕጋዊ በሆነ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ብቻ ከሥራ ገበታቸው የተባረሩ መምህራ ባፋጣኝ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ፤ እንዲሁም መንግስት የመምህራኑን አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ከማፈን ተቆጥቦ ተገቢዎን ምላሽ እንዲሰጥ፣!!

6,በአጠቃላይም በኢትዮጵያ በነጻነት የመደራጀት፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽ፣ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ የመቃወም እና ሌሎች መሰረታዊ መብቶች ላይ የሚደረገው ከፍተኛ አፈና እና ጫና እንዲቆም፤ እንጠይቃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ,      0477 327 090 ወይም

0486 454 955 ወይም

0486 336 367

የኃይማኖት፣ የዘር፣ የቋንቋ እና የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶቻችን የኢትዮጵያዊነታችን ውበት እና የአንድነታችን መገለጫዎች ናቸው!

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!አስተባባር ኮሚቴው !!

3 Responses to ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ! በአውሮፓ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ

 1. mertework Reply

  May 10, 2012 at 5:23 pm

  we need VOICE OF AMHARA!!menawe yemicohlen selef yemewetalen atene?
  hageru new eko zare be AMARANETU BICHA mekera yemidersbet minew? self ayewataletem? AMHARA is so kind for all know AMHARAS the woyane evil rigem they have degeading. and the AMHARA were victims of genocide countless ETHIOPIA, who foll victim to evil meles, and SHAME ON YOU WOYANES PARLIAMENT MEMMERS HODAMOCH weganachu eytefa,

 2. DASSENNECH Reply

  May 9, 2012 at 4:38 am

  Amara be amaranetu bicha keyebotaw eyetefenaqele yalewun minew resachihut? mizan aldefa bilo new?

  • Eskenche Reply

   May 10, 2012 at 7:30 am

   Sele amarawe yalagebabe mefenakel yehe yetkawemo selef ayemeleketewm?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>