ከመኖርያ መንደራቸው በግፍ እየተባረሩ ያሉ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ መግለጫ

April 16, 2012

Click here for PDF

የኢትዮጵያ ወቅታዊ  ጉዳዮች መወያያ መድረክ መግለጫ

Ethiopian Current Affairs Discussion Forum - ECADFራሱን የትግራይ ተገንጣይ ቡድን የሚለው የሀገር አጥፊዎች ጥርቅምና በስሩ በኮለኮላቸው ከሃዲዎች መልካም ፈቃድና ትብብር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የጀመረውን ዘመቻ በሰፊው ቀጥሎበታል። ምንም አይነት የሕዝብ ውክልና የሌለውና ይሁንታ ያልተሰጠው ይኸው የክብረጠሎች ስብስብ ኢትዮጵያውያንን ከመኖርያ መንደራቸው እያፈናቀለ ተንከባክበው የያዙትን ለም መሬት ለባዕዳን እየቸበቸበ የግል ካዝናውን በማደለብ ላይ ይገኛል። ይህ የተቀነባበረ ዘር የማጥፋት ደባው ደግሞ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማቆየት እንደ ድርና ማግ የደም ትስስር ያለውን አንድ ሕዝብ በዘርና በጎሳ በመነጣጠል አንዱን በሌላው በማነሳሳት የነበረ ቢሆንም ይህ እነደታሰበው ሳይሰራለት ቀርቷል። በዚህም ምክንያት አሁን የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት ያለ ሕዝቡ ይሁንታ በጉልበትና በመሳርያ ሃይል ማፈናቀሉን ቀጥሎበታል።  ይህ በስልትና ተራ በተራ እየተደረገ ያለው ጭፍጨፋ የመሬት ቅርምትና ማፈናቀል በሰፊው ቀጥሎ አሁን ደግሞ የሃይማኖት ደብሮችንና ገዳማትን በማፍረስ፣ በእስልምና ሀይማኖት ዉስጥ ጣልቃ በመግባት የሀገሪቱን ታሪክና ማንነት ለማናጋት በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ነው። ይህ ጥፋት ወሰን አልባና ማቆምያ የሌለው እየሆነ አሁን የለየለት የጥፋት ዘመቻውን በማን አለብኝነት በመቀጠል ኢትዮጵያ የማን ሀገር እንደሆነች ለማወቅ ከማይቻልበት ጊዜ አድርሷታል። ኢትዮጵያ በጠላት ወረራ ከደረሰባት ጥፋት በእጅጉ የከፋ ወንጀል በኒህ አረመኔዎች እየተፈጸመ መሆኑ የሚያስቆጣ ነው። ይህ አገር በግብዣ የሚሰጥ ለምኖ ባርነትን ለትውልድ የሚጋብዝ የከሃዲዎችና የባንዳዎች ጥርቅም ምንጩ ደግሞ ከአንድ ጎጥ ከትግራይ የተለቃቀመና በዙርያው ጥቂት ሆዳሞችን ከየጎጡ የያዘ ቡድን በመሆኑ አደጋው የተነጣጠረውና በይፋ በደልም እየደረሰ ያለው የመሬት ንግዱና ማፈናቀሉ በለምና ለሀገር ብልጽግና ታላቅ ፋይዳ በሚሰጡ ቦታዎችና እና ነዋሪዎች ላይ መሆኑ ሁኔታዎችን የበለጠ አደገኛ እያደረገው መጥቷል።

በመላው አለም የተበተኑ ኢትዮጵያውያን የሚታደሙበት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ እንደ ሁሌውም በወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ላይ ውይይት የሚያደርግና ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ለሚደረገውም ትግል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ያለ የኢትዮጵያውያን ስብስብ ነው። ከሰሞኑ አበይት ጉዳዮች መካከል ይኸው መለስ መራሹ የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ስልጣን ከተቆናጠጠበት ጊዜ አንስቶ በተለይ በአማርኛ ተናጋሪዎች እና በአማራ ብሄር ተወላጅ ገበሬዎችና ከዚያ አካባቢ  መጥተዋል በሚላቸው ኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገው የጥፋት ዘመቻ አሁን ከመቼውም በላይ በከፋ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ህወሀት ገና ከደደቢት ተንኮሉን ጠንስሶ ሲነሳ ጀምሮ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን በኢትዮጵያዊነታቸዉ ጽኑ ዕምነት ስላላቸዉ ብቻ ጨፍጭፎ በጅምላ እንደቀበራቸዉ አቶ ገብረመድህን አርአያ የቀድሞ የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቲ አባል ሲናገሩ ተደምጠዋል።ይህ የባንዳ ጥርቅም ቡድን በኢትዮጵያዊነታቸዉ ጽኑ ዕምነትን ባሳዩ ዜጎች ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታግሎ የቀየረዉን የፊውዳል ስርዐት “ነፍጠኛ” የሚል ስም እንደ መኪና ታርጋ በመለጠፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጽም ከሰላሳ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። የጎንደር አዉራጃን ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል በወልቃይት ጠገዴ  ነዋሪዎችን በመጨፍጨፍ፣ በማባረርና ሴቶችን በመድፈር የአንድ ዘር ልጆች እንዲወለዱ በሚል እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ማንም ኢትዮጵያዊ ዝም ብሎ የሚያልፈው ጉዳይ አይሆንም።በተመሳሳይ በአፋር፣ በጋምቤላና ኦጋዴን ክልል ያሉ ወገኖቻችንም የወያኔ የዘረኝነት ብትር እና መፈናቀል በርትቶባቸው የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው ይህንን አስመልክቶም ለተከታታይ ቀናት ውይይት ሲደረግ ቆየቷል።  በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት ቀደም ሲል በአቦሪጅናሎች (በሀገሬው ተወላጆች) ላይ የተደረገ ዘር የማኮሰስ፣ እኔነትን የማሳጣትና ጨርሶ የማጥፋት ደባ ጋር መመሳሰሉና በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ይህ መደገሙ ደግሞ እጅግ የሚያስቆጣና ኢትዮጵያውያንን በአንድነት የሚያስነሳ ጉዳይ እንደሆነም እናምናለን። ከአንድ አካባቢ ብቻ በገሃድ ሃያ ሺህ በላይ ቤተሰብን በአማራነት ፈርጆ ንብረታቸውን ቤታቸውን ጥለው ከገዛ ሃገራቸው ማፈናቀልና ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ብሎ መበተንና ወደ ግዞትም ማጋዝ የሚያስታውሰን በሩዋንዳ በቱሲዎች ላይ የተደረገውን የዘር ጭፍጨፋ ነው። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ከደቡብ ክልል ብቻ ከ80 እስከ 100 ሺህ የሚጠጉ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ለማፈናቀል እቅድ ተይዟል። የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ይህንን ግፍ ለማን እንደሚያቆየውና የሕዝብ ቁጣ ሊያስከትል የሚችለውን ልብ ያለው ወይም ከሌሎች ተሞክሮዎች የተማረው አይመስልም። የዛሬዎቹ አፈናቃዮች የነገውን እጣቸውን ልብ ቢሉ የዚህ አይነት ግፍና በደል ለትውልድ ለማቆየት ይደፍራሉ ብለን አናምንም። የአፋርን ሕዝብ አፈናቅለው አዋሽን ገድበን ውሃ አናሳጣሃለን ብሎ ማስፈራራትና ለም መሬታቸውን ነጥቆ ማባረር ከውጪ ወራሪ ሃይል እንጂ በተመሳሳይ ሃገር ውስጥ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል የሚፈጽመው ግፍ ብቻ አይመስልም። ወራሪንና ጠላትን በአንድ ፈርጆ መዋጋት ካለበት ከጠላቱ ጋር መተናነቅ የማይችል ሃይል ያለመኖሩን ያለመቀበል የሁልጊዜው የአምባገነኖች በሽታ ነው።  ይህ እብሪት በተባበረ የሕዝብ ክንድ ሊመታ የግድ ነው። መገፋት በቃ! መረገጥ በቃ! የመነሳት ጊዜ አሁን ነው! የምንል ኢትዮጵያውያን ወያኔን፣ የወያኔ ጋሻ ጃግሬዎችንና አገልጋዮችን ከዚህ የግፍ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን።

በአሁኑ ወቅት ከ36 ሃገሮች የተውጣጡ ባለሀብቶች በተደረገላቸው ልመናና ጥሪ መሰረት የኢትዮጵያን ለም መሬት እየተቆጣጠሩ ነው። ኢትዮጵያውያን የመሬት ባለሀብት አይደሉም ባዕዳን ግን የመሬት ባለሀብት ሆነው እንዳሻቸው ማድረግ ይችላሉ። ኢትዮጵያ ማዕድኗን፣ የውሃ ሃብቷን በሙሉ ለገበያ አቅርባለች ወደፊት አደገኛ የአየር መዛባትና ቀውስ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፕሮጀክቶች በየአቅጣጫው እየተጀመሩ ነው። እኒህ ፕሮጀክቶች ባለሃብቶችን ሲያከብሩ ኢትዮጵያውያንን ያለድምጽ የሚገድሉ መሳርያዎች ናቸው። ይህንን በትዕግስት ከተመለከትን ሀገር ማጣታችን ምንም ጥያቄ የለውም። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ከእጃችን እየወጣች መሆኑን አምነን ለማዳን የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እናስታውቃለን። የኢትዮጵያን ታሪክና ቅርስ ክብርና ኩራት የሆኗትን እሴቶች በሙሉ በገሃድ እየመዘበሩ እየሸጡና የቀረውንም እያቃጠሉ ነው። የእምነት ቤታችን እየፈረሰብን ያለን ኢትዮጵያውያን ይህንን ደባ አጥብቀን እናወግዛለን። ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብም አንድ አድርጎ አስተሳስሮ ያኖረህን ኢትዮጵያዊነትህን፣ ሀገርህን፣ መንደርህን ከነጣቂዎች ተከላከል የሚል ጥሪም እናስተላልፋለን።

ለሚከፍልህ ትንሽ ምንዳ ሲባል ወገንህን ለመጨፍጨፍ ወያኔ ያስታጠቀህ ሰራዊት ከሕዝብህ ጎን ቁም፣ ለወገንህ ክብርና ነፃነት እንጂ ለጥቂት ጀንበር ሲጠልቅ ጥለውህ ለሚጠፉ ዘራፊዎቸና ነጣቂዎች መሳርያ አትሁን። ኢትዮጵያን አገርህን ለማዳን የታጠቅኸወን ነፍጥ ወደ ጠላቶችህ እንጂ ወደ ተገፋው ወገንህ አታዙር የሚል ጥሪም እናስተላልፋለን።

ይህ መለስ መራሹ የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ለዘመናት በተለይ በተቀነባበረ መልኩ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገው ጭፍጨፋና ወንጀል ባስቸኳይ እንዲቆምና ከመኖርያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ እንጠይቃለን። በአኝዋክ፣ በኦሞ ሸለቆና በአፋርም የሚፈጸመው ነዋሪዎችን ማፈናቀል ባስቸኳይ እንዲቆምና ሕዝቡ ሰላማዊና የተረጋጋ ኑሮውን መኖር እንዲጀምር በጥብቅ እናሳስባለን፣ ከህዝባችንም ጎን በመቆም ነጻነቱን እንዲቀዳጅ ለሚያደርገው ትግል የሚጠየቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንንም እናስታውቃለን።

ኢትዮጵያ በነፀነቷ ለዘለዓለም ኮርታ ትኑር!!

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ

Ethiopian Current Affairs Discussion Forum (ECADF)

4 Responses to ከመኖርያ መንደራቸው በግፍ እየተባረሩ ያሉ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ መግለጫ

 1. meretework Reply

  August 12, 2012 at 1:52 pm

  ALL tplf”s must go they are enemey of ETHIOPIAN Poeple!!!The Devel meles lease out our land, so we demand our dignity democracy, and territoral integrity our land, for our poeple!

  LONG LIVE ETHIOPIA and her poeple!!!!!!

 2. engizazi Reply

  April 17, 2012 at 7:00 pm

  yes,our common enemies,historically and tradationally have been existing and have also been engaging in distructive activities to harm Ethiopians and Ethiopia.Zinawi and the men and women surround him are of course the children of the rememants of the enemies that we had before them.

  The enemy entered Ethiopia with a lot of guns and bullets,and with a deep hatred towards Ethiopians;it then scattered allover and accross the country and broke into homes and vandalized the lives of Ethiopians.

  We took our common enemy seriously and had launched our struggle against the enemy that has been eating our children alive and destroying our country insanely.We shall not take enemy as the impossible;rather,the possibility is endless for all Ethiopians to retaliate the enemy with victory.Ethiopians,keep the faith keep the fight.

 3. biye Reply

  April 17, 2012 at 12:36 pm

  The blood sucker woyane junta’s capacity to do evil is beyond any comprehension. EVEN BEFORE WE HAVE TIME TO RECOVER FROM ONE ATROCITY THE EVIL WOYANE SOON moves over to another horrendous crime. the woyane are sleepless and dream day and night how they could harm this poor country and its people.
  God save us.

 4. Aregash Solomon Reply

  April 17, 2012 at 11:43 am

  Great press release ,Thanks a million .with a bit additional personal thought; I wish you wrote this release in varous languges and mail it to various media outlets like CNN,REUTERS,BBC,VOA,DW etc..and The World bodies like UN ,UNHCR AU,EU and each and every Government represnetatives for those nations. that Will help us expose TPLF’s heinous crime to the World

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>