የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” እና ጥቂት የተዛቡ የታሪክ እውነቶች

April 16, 2012

Click here for PDF

Teddy Afro New Song 2012

ከዳዊት ከበደ

ይህንን አጭር የታሪክ ማስታወሻ ለመጻፍ ምክንያት የሆነን፤ “ጥቁር ሰው” የተሰኘው አዲሱ የቴዲ አፍሮ ዘፈን ነው። በዚህ ዘፈን ውስጥ በተለይም አጼ ምኒልክን የጥቁር ሰዎች ንጉሥ አድርጎ፤ በዙፋናቸው ላይ ዙፋን ጨምሮ… አግንኖ እና አጉልቶ ስላሳየን፤ አልበሙንም ለአጼ ምኒልክ፣ ለእቴጌ ጣይቱ እና ታሪካቸው ላልተነገረላቸው ጀግኖች በማድረጉ… ለቴዲ አፍሮ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።

“ከኢትዮጵያ ሞት በፊት እኔን ያስቀድመኝ” በሚል የኦሮምኛ ስንኝ የተዋበው ይህ የ”ጥቁር ሰው” ዘፈን ፤ በሙሾ እና በጀግና ሆታ የተቃኘ ነው። በሙሾው እነዚያ ለአገራቸው የወደቁ ኢትዮጵያዊያንን እንድናስብ፣ በሆታው ደግሞ የጀግንነት ዜማ እንድናቀነቅን ያደርገናል። ይሄ እንዳለ ሆኖ በዚህ ስራ ውስጥ የተከሰቱ ስህተቶችን በመቃኘት፤ ስራው ለወደፊት በመድረክ ሲቀርብ ወይም በዲቪዲ ሲሰራ በሲዲው ላይ የታየው ስህተት እንዳይደገም እርምት እንዲደረግበት ነው… የዚህ ማስታወሻ ዋና አላማ።

በዚህ ማስታወሻችን ላይ ዋና ዋናዎቹን ስህተቶች እንግለጽ።

ዋናዎቹ በቴዲ አፍሮ ውስጥ የተከሰቱት ስህተቶች የሚያጠነጥኑት በደጃዝማች ባልቻ እና ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ዙሪያ ነው። ሁለቱም ጀግኖች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና በመጫወታቸው፤ በ’ያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ልዩ ስፍራ አላቸው። ነገር ግን ምንም ያህል ብንወዳቸው የሌላውን ታሪክ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ መስጠት
የለብንም። ቴዲ አፍሮም አውቆት ሳይሆን ባላወቀው መንገድ ይመስለናል ስህተቱን የሰራው። እንዲህ ነው ነገሩ። በዚህ አልበም ውስጥ በተለይም የፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራው እና እና ራስ አባተ ቧያለው አባ ይትረፍ ታሪክ ወይም ስራ ሸርተት ብሎ ለነ አባ ነፍሶ እና አባ መላ ሄዷልና ከዚህ በመቀጠል እርማቱን እየሰጠን፤ በዚያውም ተጨማሪ የታሪክ ዳሰሳ እናደርጋለን።

ምኒልክ ወደ አድዋ ሲሄድ ምናለ፤
አረ አይቀርም በማርያም ስለማለ።
ወይ ሳልለው ብቀር ያኔ
እኔን አልሆንም ነበር እኔ።

ካለ በኋላ… ገና በዘፈኑ ማለዳ ላይ፤ “ባልቻ አባቱ ነፍሶ
መድፉን ጣለው ተኩሶ” ይለናል።

ከላይ ያለውን ስንኝ በህሊናችሁ እንደያዛችሁ ጥቂት ስለ ባልቻ አባ ነፍሶ ላውጋ። – ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ። (ባልቻ አባነፍሶ) በአባታቸው ኦሮሞ፣ በናታቸው የጉራጌ ተወላጅ ናችው። በ1888 ዓ.ም. በአድዋ ጦርነት ወቅት በአጼ ምኒልክ ስር ሆነው በመድፍ አስተኳሽነት ተሰልፈዋል። ቴዲ በዘፈኑ ውስጥ “ባልቻ አባቱ ነፍሶ” በማለት በተደጋጋሚ ገልጿቸዋል። ሆኖም ነፍሶ የፈረሳቸው እንጂ የአባታቸው ስም አለመሆኑን እዚህ ላይ አስምረን እንለፍ። ይህ እንደጉልህ ስህተት ላይታይ ይችላል። ውሎ ሲያድር ግን ለመጪው ትውልድ የተሳሳተ መልዕክት እንዳያስተላልፍ ነው እርምት የሚያሻው። እናም ቴዲ ይሄን ዘፈን መድረክ ላይ እንደገና ሲጫወተው… ባልቻ አባቱ ነፍሶ ሳይሆን “አባቱ ሳፎ” ብሎ እንደሚያቀነቅን ተስፋ አናድርግ። ይቀጥላል…

15 Responses to የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” እና ጥቂት የተዛቡ የታሪክ እውነቶች

 1. ene Reply

  April 23, 2012 at 9:15 pm

  I am all for constructive criticism. The author’s tone, however, is anything but constructive. It is annoying, in fact! Perhaps, he should consider learning how to communicate in a civil manner.

 2. ESKEZARE Reply

  April 20, 2012 at 1:51 pm

  For aged Ethiopian it looks a minor, because you recognise that NEFSO is Dejach Balcha Safo’s Horse name. The coming generation must knew the right Historical background. In other way Weyane propagators will be involved to divert to the dedebit 100 years proposals.
  Already they are doing their job.
  Do you knew Mlass Zenawi’s Horse name? The answer is ABA PRESIENT GIRMA W/GIORGIS.

 3. Aregash Solomon Reply

  April 20, 2012 at 6:08 am

  A minor and almost irrelevant correction for a giant forwarded hiistorical song

 4. Tazabiw Reply

  April 19, 2012 at 9:56 pm

  I think it is good to mention your sources .Unless your comment seem simply story from your dream.

 5. ESKEZARE Reply

  April 19, 2012 at 6:14 pm

  Eskemeche?
  Please learn from Ato Dawit Kebede! Read repeatdly to understand! Dn not trying to divert the polite comment.
  Not Dawit, you are Eskemeche spliting the invisible hair with provocative words.

 6. tassew Reply

  April 18, 2012 at 9:00 pm

  I was expecting something from EMF. Dawit and kinfe was against teddy long ago . it is not surprise to me .

 7. አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ Reply

  April 17, 2012 at 8:48 am

  *******ጥቁር ሰው እንደዶሮ::*******
  የፋሲካ በዓል ቢመጣ ዘንድሮ:-
  በቴዲ ታረደ
  ጥቁር ሰው እንደዶሮ::
  አወይ መሞት ኖሮ:-
  አይበስልም ወይ አሮ???
  እርር ብሎ ከስሎ:-
  የበሰለ መስሎ:-
  በሕዝብ ደም ተማስሎ:-
  ባጥንት ተቀቅሎ:-
  በምንሊክ ምጣድ ቢራገብ ዘንድሮ{-
  በካሴት ታረደ
  ጥቁር ሰው እንደዶሮ::
  ለነጻነት ችቦ በኤሎሄ ትንሳኤ:-
  ለኢትዮጵያ ተስፋ ለሕዝቧ ሱባኤ
  በሙዚቃ ቅላጼው ታሪክ ሊያመላክት:-
  በእስር በወከባ በፍቅር ሲዋትት:-
  አመታት ሲያስቆጥር ፋሲካን ዘንድሮ:-
  ቴዲ አረደልን
  ጥቁር ሰው እንደዶሮ::
  እንግዲህ ትንሳኤ ነጻነት የሚሻ:-
  ትግል ጎራ ይግባ ይቃመስ ከጉርሻ::
  አውቆ የተኛ ሰው ፍፁም አይነሳ:-
  ሕሊናውን አልፎ ልቡ እስከሚበሳ::
  እናም በፋሲካ መግደፊያው ዘንድሮ:-
  በቴዲ ታረደ
  ጥቁር ሰው እንደዶሮ::

 8. እስከ ምቼ Reply

  April 17, 2012 at 5:34 am

  የኔ ወንድም፤ ባልቻ አባ ነፍሶ እየተባለ ግጥም ተፅፏል። ፉከራ ተደርድሮበታል። በተመሣሣይ መልኩ ደግሞ፤ አባ ታጠቅ ካሣ ተብሏል። ይኼን እንደ ስህተት መቁጠር ከቆጣሪው ነው ስህተቱ። ፀጉር መሰንጠቅ ብቻ አይደለም፤ ባህልንና የፈረስ ስም እንዴት እንድሚውል አለማወቅ ነው።
  በተረፈ ደግሞ፤ የግጥም ደራሲ ትልቁ ፈጠራው፤ ቃላትን በፈለጋቸው መልክ ደርድሮ፤ መልዕክቱን ማስተላለፍ ነው። ተራራዉ ዞር እንዲልለትና ያን ሀገር እንዲያይ ሲገጥም፤ እንዴት ተራራ ዞር በል ይባላል ብለን አንጠይቅም። የገጣሚዉን የፈጠራ ነፃነት ለመግፈፍ መጣር፤ የኪነትን ሂደትና የፈጠራ ስፋት አለማወቅ ነው። ገጣሚው ታሪክ አዋቂ ነኝ ብሎ ታሪክ ሊያስተምር አልቃጣውም። ታሪካችንን አንስቶ፤ በኪነት ሙያው ሊያስገነዝበን ችሏል። የቃላቶቹም ሆነ የገጥም አደራደሩ ባለቤት የኪነቱ ባለሙያ መስክ ነው። ስለ ስነ ግጥም ማወቅ ከፈለጉ፤ ራሱን የቻለ የስነ ጥበብ መስክ ስለ ሆነ ለባለ ሙያዎች ይተዉላቸው። እንዲያው በተረዱት መልክ ይደሰቱ።
  ከክብሮት ጋር
  ከእስከመቼ አዘጋጆች

 9. Baye Reply

  April 17, 2012 at 1:46 am

  Dawit

  This is like Tsegur sinteqa. I dont think the people learn History from Songs and eulogy only A person wo is ready to learn history reads books and research papers.Ababal new enji sewom iko Balcha Abanebso blo yemiterachew yeferes lij endalhonu iyetereda yimeslegnal. loool

 10. Fresenay Kebede Reply

  April 16, 2012 at 6:29 pm

  Thank you Ato Dawit.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>