ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ መግልጫ

April 10, 2012

Click here for PDF

መዝገብ ቁጥር (Ref)009

ቀን (Date) 4/8/2012

ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ መግልጫ

የታሪካችን መለያ የሆኑት ገዳሞቻችንና  የእምነት ተቋሞቻችን ከመደምሰሳቸውና ጨረሰው ከመጥፋታቸው  በፊት በጋራ እንከላከላችው።  ኢትዮጵያ አገራችን በታሪክ ዘመኗ አይታውና ገጥሟት የማታውቀው ህልውናዋን ከምድረ ገጽ ጨርሶ የማጥፋት ዘመቻ ወያኔ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሎበት ይገኛል። ሰሞኑን በአሰቦት በዝቋላ ገዳሞች ላይ በተለይ ደግሞ በጐንደር ክፍለሃገር የሚገኘው ታላቁ የታሪክ ቅርስና ቅዱስ ገዳማችን ዋልድባ ውስጥ እየተደረገ ያለው፤ የማጥፋት ዘመቻ እጅግ አሳስቦናል። አስቆጥቶናልም። የወያኔ መንግሥት በማናህሎኝነት ለም የሆኑትን  የጎንደር ታሪካዊ ቦታዎች፤ የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት በኃይል ነጥቆ በመውሰድ ወደ ትግራይ ካካለለና ነባሩን ማህበረሰብ  አፈናቅሎና አጽድቶ ከጨረሰና የትግራይ ሰዎችን ብቻ ካሰፈረ በኋላ፤ ለብዙ ሽህ ዓመታት ተጠብቆና ተከብሮ  የቆየው ታሪካዊነትና ታላቅ ቅርስነት ያለው፣ ቅዱስ የዋልድባ ገዳም የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሚል ሰበብ፣ አራት የገዳሙ አብያተ ክርስትያናትንና ከሃያ ሽህ በላይ ገበሬዎችን ለማፈናቀል እቅድ ሲያወጡና  በገዳሙ  የተቀበሩትን፤ የቅዱሳንና፤  የአያት ቅደመ አያቶቻችን እናት አባቶቻችን አጽም ቆፍረው ሲጥሉ ማየቱና መስማቱ እጅግ ያሳዝናል ያስቆጣልም። በ03/24/2012 በአመሪካ ድምጽ ሬድዮ ቃለ መጠይቅ መሰረት አቶ ሲሳይ መረሳዕ የተባሉ የማይ ጸብሪ አስተዳዳሪ  በዋልድባ የአባቶችና የቅዱሳን መቃብር እየቆፈራቹህ እያወጣችሁ አይደለምን ሲባሉ አይ የወልቃይቴዎች መቃብር ነው የቆፈርነው የሚል ጥላቻ፤ ትምክህትና እብሪት የተሞላበት መልስም አሰምተውናል። (ለማድመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ)።

ወያኔ  ስልጣን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ በግልጽ ሆነ በስውር  ታሪካዊ የሆኑትን ቦታዎች፤ የማፈራረስ፤ ቅዱስ ገዳማትን  የማቃጠል፤ ታሪክ አዋቂዎችንና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን መንጥሮ  ከምደረ ገጽ የማጥፋት፤ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸውን  ወጣት ልጃገረዶችን ለአረብ አገር ባርነት ያለምንም ተጠያቂነት አሳልፎ የመስጠት ፤ በሰላምና በሥራ እጦት ምክንያት ወገኖቻችን ወደ ሰደት በአራቱ አቅጣጫ እየወጡ ለከፋ ኖሮ እንዲጋለጡ የማድረግ፤ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከለም መሬታቸው በማፈናቀል ለውጭ ሀገር መንግሥታትና ከበርቴዎች የመሸጥ፤ የኢትዮጵያችን ሉዓላዊነቷን የማስደፈር፤ የሃይማኖት ግጭቶች እንዲነሱ የመጣር፤ በተለይ አማራውን ለማጥፋትና ለማዳከም ከሃያ አመታት በላይ ያላቋረጠ ጥረት የማድረግ፣ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ እናንተ አማራዎች ስለሆናችሁ ወደ ክልላቹህ ሂዱ እየተባሉ ከድቡብ ኢትዮጵያ፤ ቤጅ ማጅ  ጉራ ፈርዳ ወረዳ ንብረታቸውንና ሀብታቸውን ጥለው እየተደበደቡ በግድ  እንዲባረሩ የማድረግ (ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ ) ኢሰብአዊ ድርጊቶች ከሚጠቀሱት ጢቂቶቹ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት ለዜጎቹ ያለውን ንቀት የተገነዘቡ እንደ ሱዳን ሌሎች አረብ አገሮችም ኢትዮጵያዊያንን ሲያሰቃዩ በፈላ ውኃ ሲመልጧቸው፤ በፎቅ ሲወረውሯቸው፤ ሲደፍሯቸው፤ ከአቅም በላይ ሥራ ሲያሰሯቸው፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ በካርቱም በየ አቢያተክርስቲያኑ እየገቡ ልጃገረዶቹን በጠራራ ፀሐይ ነጥቀው ሲወስዷቸው ይታያል።

ውድ ወገኖቻችን፤ በዝቋላ፤ በአሰቦትና፤ በጐንደር ዋልድባ ገዳማትና በተለያዮ የእምነት ተቋሞች ላይ ሆን ተብሎ እየደረሰ ያለውን ጥቃትና የማፈራረስ ተግባር ልሳነ ግፉዓን በጥብቅ እንደሚያወግዝና ይህንን እኩይ ተግባር በመቃወም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአስቸኳይና በአንድነት በመነሳት መብቱንና ነጻነቱን፤ ታሪኩንና ቅርሱን በሚችለው መንገድ ሁሉ እንዲከላከል እናሳስባለን!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም ትኑር!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>