የአማራን አርሶ አደር ለመታደግ ወያኔን ማስወገድ!

April 1, 2012

የግንቦት ሰባት መግለጫ

Click here for PDF

Ginbot 7 press release in Amharicየመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ በኢትዮጵያ ደሃ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ላይ ላይ የሚያደረሰው ግፍ ዝርዝሩ ብዙ ነው። በተለያዩ ቦታዎች የወያኔ ሠራዊት በአካል በመዝመት የፈጃቸው አርሶ አደሮች በሺህ መቆጠር ጀምረዋል። የወያኔ ኩባንያዎች የሚጫኑባቸውን የማዳበሪያ እዳ መክፈል እያቃታቸው ሺዎች ለእስራትና ለንብረት ዘረፋ ተዳርገዋል። በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መሬታችሁ ከሩቅ አገራት ሃገራት ለመጡ ቱጃሮች ኢንቨስተሮች ይፈለጋል እየተባሉ ከቤታቸው ከእርሻቸው እየተፋነቀሉ የሃገር ውስጥ ስደተኞች ሆነዋል።

በተለያዩ አካባቢዎችና ወያኔ ባመቻቸው የዘር ፖለቲካ እየተጠለፉ አርሶ አደሮች እርስ በርሳቸው እየተጋጩ በርካታ ህይወት መጥፋት የጀመረው በወያኔ ዘመን ነው። የሃገሪቱ አርሶ አደር የወያኔ ጭሰኛ እንጅ ባለሃገርና ባለመሬት እንዳልሆነ እንዲሰማው ተደረጎ ከዛሬ ነገ ምን ይመጣብኝ ይሆን በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቆ ህይወቱን መግፋት ከጀመረ ውሎ አድሯል።

ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በአማራ አርሶ አደሮች ላይ የሚፈጽመው ጥቃት የዚሁ የወያኔ ፀረ-አርሶ አደሮች መርሃ ግብር አካል ነው። ከሰሞኑ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በሚገኙ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ደሃ አርሶ አደሮች ላይ የሚፈጸመው ግፍ በአንድ በኩል በዚህ መነጽር የሚታይ ቢሆንም በሌላ በኩል ወያኔ በተለይ ለአማራ ህዝብ ካለው ስር የሰደደ ጥላቻና በቀል የሚመነጭ መሆኑን መዘንጋት አይገባም።

ባህር ተሻግረው የመጡ ቱጃሮች በሺዎች የሚቆጠር ጋሻ መሬት በነፃ ሲሰጣቸው ኢትዮጵያው ገበሬ ከአንድ የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ክፍል ሂዶ ለማረስ መሞከሩ “መጤ” ሲያስበለው፤ ለእንግልትና ሰቆቃ ሲዳርገው ማየትና መስማት እጅግ ልብን ይሰብራል።

በተለይም በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች ውስጥ በሰፈሩ የአማራ ዝርያ ባላቸውአርሶ አደሮች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እጅግ አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሷል። በርካታ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ገበሬዎች በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በተለያዩ ቦታዎች ለዓመታት ሲያርሱት የነበረው መሬት ተነጥቀው፤ “በነፍጠኛነት” ተዘልፈውና ተደብድበው፤ በብዙ ድካም ያፈሩት ጥሪት ተነጥቀው መባረራቸው እጅግ አሳዛኝ ጉዳይ ነው። ይህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብቻ አይደለም። ይህ የለየለት ዘረኝነት ነው።

የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ “መሬት የሚሸጠው በመቃብሬ ላይ” የሚለው ያለ ምክንያት አይደለም። መሬት ለመለስ ዜናዊ አማራንና የሚጠላውን ሁሉ ማጥቂያው፤ ወዳጆቹን ደግሞ መጥቀሚያ መሣሪያው ነው። መሬት ለመለስ ዜናዊ የሚሰጠው አገልግሎት ዘርዝሮ መጨረስ ቢያዳግትም አንዳንዱን ብቻ ለአብነት ያህል ብቻ እንጥቀስ።

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ “መሬት አይሸጥም” በሚለው ሰበቡ የኢትዮጵያን መሬት በሙሉ በእጁ በማስገባትነቱ ዘረኛ በሆነ መመዘኛው ለወገኖቹና ለአጨብጫቢዎቹ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን እየሰጠ በአንዲት ቅጽበት የሚሊዮኖች ብሮች ጌታ አድርጓቸዋል። በአንፃሩ ደግሞ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ገበሬዎች ለቤተሰቦቻቸው ቀለብ የሚሆን የጓሮ አትልክት መትከያ ቦታ አጠተው በረሃብ እንዲሞቱ እየተደረገ ነው።

አርሶ አደሩን ከረሃብ ለመታደግ በቀድሞው መንግሥት ትዕዛዝ በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች ሰፍረው የነበሩ ድሃ የአማራ አርሶ አደሮች ዛሬ “በነፍጠኛ ሥርዓት” ርዝራዥነት እየተከሰሱ ስቃይ እንዲደርስባቸው እየተደረገ ነው።

አማራው ከአማራ ክልል ውጭ ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልል ውስጥም ባይተዋር ተደርጓል። ጥንታዊውን የወልድባ ገዳም ግቢ ለስኳር ምርት በሚል በከበርቴዎች ዶዘር መታረስ ጀምሯል። ቦታው ከመታረሱ በፊት የአካባቢውን ገበሬ ይሁንታ የጠየቀ የለም። አቤት ለማለት የቃጡ አርሶ አደሮችና መነኮሳት በመለስ ዜናዊ ቅጥረኖች ተንገላተዋል።

የወልቃይት ጠገዴን ተወላጆችን መሬት በግድ በማስለቀቅና በማፈናቀል የትግራይ ተወላጆች ብቻ ተመርጠው እንዲሰፍሩበት ተደርጓል። በዚህም ምክንያት በሁለት አስር ዓመታት ውስጥ ብቻ የአካባቢው ነዋሪ የብሄረሰብ ስብጥር ሙሉ በሙሉ ተለውጧል።

ሰፊ የእርሻ መሬት ከአማራው ተነጥቆ ለሱዳን ተሰጥቷል። አባቶቻችንና እናቶቻችን ጦር አሰልፎ የመጣን ጠላት ተፋልመው ያቆዩልንን መሬት ለሱዳንና ከሩቅ አገራት ለመጡ ቱጃሮች ተሰጥቷል።

መለስና እኩይ ቡድኑ የኢትዮጵያን ሃብትም ተከፋለው ስለጨረሱት ለወጣቱ የተረፈው እዳ ብቻ ሆኗል። ለም መሬታችን ለባዕዳን በመሸጡ የገጠሩ ወጣት የሚያርሰው ቁራሽ መሬት እያጣ መሰደድ ከጀመረ ውሎ አድሯል። ወጣት ገበሬ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ለመሰደድ ከቀዬው ነቅሎ የተነሳው በመለስ የአገዛዝ ዘመን ብቻ ነው። በገጠርም በከተማም የሚገኙ ወጣት ሴቶች ወደ አረብ አገራት ለመሄድ በረሃ ማቋረጥ፤ ባህርን በታንኳ መሻገር የጀመሩት በዚሁ የግፍ አገዛዝ ዘመን ነው። ዘመናዊ ትምህርት ያገኘው ወጣትም በተማረው ትምህርት አገሩንና ወገኑን የማገልገል ህልሙ ተጨናግፎ ስደት እጣ ፈንታው የሆነው በመለስ የአገዛዝ ዘመን ነው።

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በደል እያደረሰ ቢሆንም በቂም ላይ የተመሠረተ ክፋቱ በአማራው ላይ ይበረታል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፀነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ ዘረኛ በሆነ መንገድ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው በደልን አጥብቆ ይቃወማል። የወያኔን “ከፋፍለህ ግዛ” ፓሊስ ማስቆም የሚቻለው ራሱ ወያኔ ሲወገድ በመሆኑ ትግላችንን አስተባብረን በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ በጋራ እንዝመት ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

5 Responses to የአማራን አርሶ አደር ለመታደግ ወያኔን ማስወገድ!

 1. zelalem Reply

  April 12, 2012 at 7:50 pm

  አይዞን አይዞን ወያኔ አማራን እንዲህም ባዶ እጁን ሆኖ ይፈራል . ይህን እንኳን በተለቭዥን አላሳዩም ለምን ይመስላችዋል???? አንድ ላይ እንዳይነሱ እና እንዳይተባበሩ እናም ባዶ እጁን ላለ አምራ እኮ 3 የታጠቅ ወያኔ ነው የሚያጅበው ይህን ህዝብ በፍጽም ይፈራሉ . አማራ ስልጣን ይዛ እንኳን እንዲህ ሊያረጋቸው ከነመፈጠራችወም አይስባችወም ያወም ወያኔን እይረዱ እንኳን እንሱ ቢሆኑ ኖሮ የሸፈተ አማራ ቢኖረማ ትረዳላችው በሚል ሰበብ ታየኝ. እናም ወለላ ጥሩ ገጥመሻል አማራ እንገንጠል ስላለ ሻብያ እንኳን 30 አላስገነጥል ብሎን ስንታችን አለቅን በሚል ቂም ይዘዋል ግን ለማየት ያብቃን የወያኔን መጨረሻ.

 2. Anbessa Reply

  April 2, 2012 at 8:09 pm

  እርግጥ ነው ወያኔ ዘረውኛ አማራን ሊጨርስ የመጣ እርግጥ ነው G7 ች እባካችሁ በርቱ እንበርታ የአማራ ዘር የሚባል አለቀ እባካችሁ የሰው ያለህ

 3. neqniq Reply

  April 2, 2012 at 6:24 pm

  Its high time we need to embark on action! action! action! Right now.

 4. T. Goshu Reply

  April 1, 2012 at 10:57 pm

  It is a very precise, facual, timely, deeply powerful as well as action-oriented statement and call!! Yes, it is absolutely true that it is slef -defeat if we contiune “treating” our terribly painful symptoms instead of fighting against the root cuase of our deadly illnesses ( an evil-guided political system). Yes, we have to admit that we are not still (after 20 years) working hard to make a strong bridge between our serious talks and the action which is desperately critical to reach our common and desirable destiny.

  I think we have to regret positively for what we lack behind and make unprecedented progress . We should not waste any additional precious time and energy simply complaining about the incredible humuliation we have come across . I do not think it is an exageration to say that it would be our grave mistake if we are not courageous enough to say we cannot tolerate the deadly political game that buries us alive any more.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>