የዓለም ደቻሳ ቤተሰቦች፣ አሳዛኝ ፎቶግራፍ

April 1, 2012

(ECADF) ዓለም ደቻሳ እንደሌሎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ አረብ ሀገር (ሊባኖስ) የተጓዘችው ስራ ሰርታ ደሀ ቤተሰቦቿን ለመርዳት ነበር። ይሁንና ዓለም ደቻሳ በአረብ ሀገር በሚገኙ ኢትዮጵያውያኖች ላይ የሚፈጸመው ግፍ እጣ ተድርስዋት በሊባኖስ ጎዳና ላይ እየተጎተተች ስትደበደብ ተመለከትን። (ይህ የሆነው በአቅራቢያው በሚገኝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊተ ለፊት ነበር) ቀጥሎም የበለጠ አስደንጋጩ ዜና ተሰማ፣ ዓለም ደቻሳ ህክምና እየተደረገላት በነበረበት ሆስፒታል ዉስጥ አራስዋን አጠፋች ተባለ። እውነት ዓለም ደቻሳ እራስዋን አጥፍታ ይሆን? ወይንስ አጠፏት? የብዙ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው። ከዚህ በታች የምትመለከቱት የዓለም ደቻሳ ቤተሰቦች ፎቶ ግራፍ ብዙ ይናገራል…።

Alem Dechasa’s only crime is coming to Lebanon to make some money for her poor family back in Ethiopia.

16 Responses to የዓለም ደቻሳ ቤተሰቦች፣ አሳዛኝ ፎቶግራፍ

 1. solomon Reply

  April 1, 2012 at 11:21 am

  Alem is one of few Ethiopians who are brutally abused and then killed. There are thousands of other who even their parents know what happened on them.

  UNLESS WE ALL STAND UP AND FIGHT WOYANE THE MISERY OF US BOTH HOME AND ABROAD CONTINUES

 2. Begizew Reply

  April 1, 2012 at 3:27 am

  ለአለም ደቻሳ 3/16/2012 በጊዜው በቀለ ጃለታ ሜኖሰታ
  ይች አለም ጠፋች
  የደቻስዋ ጉብል ተገፋች
  የኢትዮጲያ ኦርኮማዋ ተወገደች
  ተለማምጣ በነነች
  ተንሰቅስቃ ተነነች
  በከብት አገር ተወልዳ
  ከአራዊት ጋር ተለማምዳ
  ከእንስሶች መንደር ተወግዳ
  እንቆቅልሻ ይች አለም
  የት እንደገባች አናውቅም
  ፀሀይ በቃ አታገኝም
  ጨለመባት የኛው ኑሮ፤የዚህ አለም
  ተንከራታ ሳትደሰት
  ተነቅላ ከዕትብቷ መሬት
  ከሰፊው አፈር ግባት
  ወገኖቸ ሳይጠይቋት
  አዘገመች ወደ አቀበት
  የሊባኖስ ፍሬ ቅስፈት
  ነጎደች ወደ ማይደረስበት
  ሥር ሰደደች ወዲያው ጠወለገች የኛ አትክልት
  ከአድማስ ማዶ ሰው ካለባት
  ከቅዱሳን ከአዕላፍት
  ከንጹሓን ከመላዕክት
  ልትኖር ይሆን በአንድነት
  ይሆን ይሆን ይች እመቤት
  ወይስ…..
  የእሳ ምኞት
  የእሳ ቅዠት
  የህልም እዣት
  ከአገር ማዶ ባሻገር
  ወይ አልኖረች በኛው ሸገር
  ልመናዋ ለመጥፋት ነው ላለመኖር
  ወደ ምርጡ ለመንደርደር
  ከእንባችን ጋር ትዘክር
  የእሳ አይደለም፤ የኛው ነው ይህ ተዝካር

  በቁም ቁመታችን
  ህያው ሳለ ቁመናችን
  ያሳየናል፤ይታየናል መሞታችን
  በቁልቅለት መውረዳችን
  መልክ ማግኛ፤ መስታውት ነው ምሥላችን
  ተከተፈ ወገናችን
  ሥለያዘን ጠላታችን
  ሄደችብን ውዳችን
  የስቃዩ ፤ መመሳሰል አንድነቱ
  እዚያም እዚህ፤ተመሳሳይ በሁለቱ
  ስለገባት ከጥንቱ፤ ከጥዋቱ
  መመለሱን፤ ጠላችው የኑሮው ክፋቱ
  ሁሉን ጣለች የኛ ቢፍቱ
  እነ ጊፍቲ ፤ እነ ቡልቶ፤ እነ ጉልቱ
  ተዋረዱ ሆኑ ገልቱ
  እንግዲህ፤ እነሱም ሀሁ ይበሉ ይንገላቱ
  ለመኖር ይዋቱ
  ይታገሉ ከእንስሳቱ
  ከልምዳችን ከእንግልቱ
  አትበሏቸው ኑሩ በርቱ፤ ምናለበት አውሬዎቹ ቢሞቱ
  የሰው ዘሮች እንዲኖሩ እንዲፈቱ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>