Home » ዜናዎች » የአሜሪካ መንግስት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሙሉ ስምምነት ላይ ደረሰ

የአሜሪካ መንግስት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሙሉ ስምምነት ላይ ደረሰ

United States Congress

ትላንት ጁላይ 27 ቀን 2017 ካፒቶል ሂል የአሜሪካ ምክር ቤት ሬይ በርን ህንጻ ቁጥር 2172 በዋለው የህግ ረቂቆች የተሰሙበት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ መግስት ሰብዓዊ መብቶችን በመጣስ የሚሰራችው ወንጅሎች በሰፊው ከተኮነኑ በኋላ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ህገውሳኔ ረቂቅ 128ን ለቀጣይ የህግ ሆኖ መጽናት አቅጣጫ እንዲሻገር ወስኗል።

የህግ ረቂቁ ዋና ዋና ያካተተቸው ጉዳዮች

  • የ2015 ዓም ምርጫ ማጭበርበር ህወሃት መሩ መንግስት መቶ እጅ አቸነፍኩ ያለበት
  • በ2016 በኦሮሚያ እና አማራ የኢትዮጵያ ክፍሎች ህዝባዊ አመጽ ተነስቶ በነበረ ወቅት ተፈጽሞ ለነበረው ያለፍርድ ግድያ፤እስራትና እና ሰቆቃ። በመቶዎች የሚቆጠሩየኢትዮጵያ ዜጎች ሞት
  • የመናገር፤መጻፍ መሰብሰብ፤መደራጀት መብቶች መታፈን፤ጋዜጠኖች ላይ ሰቆቃ እስራት መፈጸሙ
  • ጸረ ሽብረተኛ “ህግ” አወጣሁ በማለት ተቃዋሚ ሃይሎች እንዳይላወሱ ማድረግ

ህገ ውሳኔ ረቂቅ 128 ትን በግንባር ቀደምትነት የሚመሩት የኢዮጵያንም ጉዳይ አበክረው ያውቃሉ ይከታተላሉ የሚባሉት የኒው ጀርሲው ተወካይ ሚስተር ክሪስ ስሚዝ ለጉባኤው ሲናገሩ ህወሃት መሩ የኢትዮጵያ መንግስት የፊቱን ጉድፍ እንዲያይ ከፊቱ መስታወት ቀርቦለታል ብለዋል።

ሚስተር ክሪስ ስሚዝ ሰቆቃ የተፈጸማባቸው ኢትዮጵያውያን አንዳንዶቹን በስም እያነሱ ህዝብ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሚውለውን ግፍ ለጉባኤው ዘርዝረው አስረድተዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትም በየጊዜው ያጠናቀረውን የሰባአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያን ዘርዝሮ ያቀረበን የጽሁፍ መረጃዎች በስብሰባው ላይ ጠቅሰዋል።

ህገ ውሳኔ ረቂቅ 128 በሁለቱ የአሜሪካ ምክር ቤት ወገኖች ማለትም በሁለቱም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፑብሊካውያን እና ዴሞክራቶች የተደገፈ ነው። 56 ተወካዮች ከሁለቱም ወገን ገና ከመሰረቱ ደግፋውታል።

አብረዋቸው የሰሩትን የኮሚቴ አባላት በማመስገን የጀመሩት ክሪስ ስሚዝ የኢትዮጵያ መንግስትን እንደ ወዳጅ ብንቆጥረውም መረን የለቀቀ ሰባዊ መብት ሲፈጽም ደግሞ ዝም ብለን አንመለከትም ብለዋል።

የካሊፎርኒያውም ተወካይ ሚስተር  ሮሄርባከር የኢትዮጵያ መንግስት ጭካኔ የተሞላባቸው ተግባራትን ፈጻሚ፤በሙስና የተጨማለቀ፤ቀማኛ ስራት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ጁላይ 27 ቀን 2017 በዋለው ስብሰባ ከትዮጵያው ግፈኛ መግስት ጋር ስማቸው የተጠራው ሰሜን ኮርያ፤ከመካከለኛው ምስራቅ ሂዝቦላ፤የቬኔዙዌላው አምባገነን ማዱሮ እና ሌሎች የላቲን አሜሪካ አምባገነኖች ናቸው።

ይህ ጉባኤ የተደረገው የወያኔ ኤምባሲ በዋሽንግቶን ዲሲ በኢትዮጵያ ሰባዊ መብት ጥሰት እንደሌለ፤ መንግስት ልማት ላይ እንዳተኮረ አድርጎ ለማውገርገር በኤምባሲው ጥሪ ባደረገ ሳምንት ነው። ይህን ዝግጅትም የኢትዮጵያ ወጣቶች አስተጓጉለውታል።

በአሜሪካ የሚገኙ ዜግነትን የተቀበሉና ሌሎችም በሙሉ የያሉበት ግዛቶች የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ጋር ቀድሞም ሲያነጋግሩ ቆይተዋል። በመጪው ወር ምክር ቤቱ ለእረፍት ስለሚዘጋ ኢትዮጵያውያኑ ተወካዮቹን ቀጥለው እንደሚያናግሯዋቸው ይጠበቃል።

የወያኔ ኤምባሲ ህወሃት መሩን መንግስት ያወገዘው ህገ ውሳኔ ረቂቅ 128 “የማይገባ፤በዚህ ጊዜ መቅረብ የሌለበት ነው” ባይ ነው። ለፍርድ ይቀርባል ሲባል ሬሳው ለዘመዶቹ በሚሰጥባት ኢትዮጲያ።

ህዝባዊ አመጽ በሚቻለው ሁሉ እየተደረገባት ላለችው ኢትዮጵያ መልካም ቀንን የሚበስር ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል እናደርገዋል እያሉ በዳያስፖራ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሲናገሩ ይሰማል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Click here to connect!