Home » ጦማሮች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም... » ወርቃማው የጵጵስና ዘመን እንዲህ ነበር! (መስቀሉ አየለ)

ወርቃማው የጵጵስና ዘመን እንዲህ ነበር! (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ

በግብጽ ይኖር ስለነበረ እልመፍርያኖስ ስለሚባል ደገኛ አባት ስንክሳሩ ላይ ከሰፈረው በድንግዝግዝ እንደማስታውሰው እንዲህ ይላል። እርሱ ከጥንት የግብጽ ገዳማት በአንዱ በኖረበት ዘመን ሊቀ ጳጳሱ እድሜው ይገፋና እረፍተ ስጋው ይሆናል። እርሱን ሲረዳው የነበረው አቃቤ መንበሩ ደግሞ በግዜው አልነበረም። እንደምን የለም ቢሉ መንገድ ሄዶ ነው ይላል፤ ጳጳሳት ከየአገሩ ተሰብስበው ቀብሩከተፈጸመ በኋላ አቃቤ መንበሩን ሾመው ሊሄዱ ቢጠብቁት ሊመጣ አልቻለም። በዚህ መሃል ቀኑ ገፋባቸው። መንበር እንበለ ጳጳስ አለ አርባ ቀን አይቆይምና እልመፍሪያኖስን ሹመውና በእስክንድሪያ መንበር ላይ አስቀምጠውት ሄደዋል።

Archbishop history in Ethiopian Orthodox Church

ብዙም ሳይቆይ አቃቤ መንበሩ ወደ ግብጽ ቢድርስ የከተማው ወሬ ሁሉ ጠረኑ ተቀይሯል፤ “ይኽ ነገር ምንድነው” ብሎ ግር ቢሰኝ ሊቀ ጳጳሱ ማረፉን እና እልመፍርያኖስ መሾሙን ነገሩት። ደንገጸ ይላል፤ “እኔ አቃቤ መንበሩ ስንት አመት ጠብቄ በላየ ላይ፤ ይኽችማ አትደረግም፤ እንደውም ሿሚዎቹንም ተሿሚውንም አውግዣለውሁ” ብሎት አረፈው። ይኽን የሰማ አባ እልመፍርያኖስ “ተውኝ ብላቸው እምቢ ብለው ያለፈቃዴ ሾመውኝ ወንድሜን አሳዘንኩት” አለ። በውድቅት ሌሊት ተነስቶም አክሊሉን በቅድስተ ቅዱሳኑ መንበር ላይ አስቀምጦ ጠፍቶ በእግሩ ወደ ፋርስ ሄደ።

በፋርስ ከሚገኙ መናኛ ገዳማት በአንዱ እራሱን ሳይገልጥ እንጨት ለቃሚ ሆኖ በማገልገል ምንኩስናውን ጠብቆ መኖር ቀጠለ። ትህትናውን አይተው ዲቁና እንስጥህ ቢሉት እምቢኝ፤ እውቀትም ምግባርም የለኝም፤ “ለኔ ብጤ ጨዋ እንጨት ሰበራው መች አነሰኝ” አለ። አስረው በግድ ሊያደቁኑት ሲሉ ድቁና እንዳለው ተናገረና በድቁናው እንዲያገለግል ሆነ።ጥቂት አመታት እናዳለፉ ለመቅደስ ያለው ፍርሃት፤ ምግባሩንና አያያዙን አይተው ክህነት ተቀበል አሉት፤ እምቢኝ ብሎ በድጋሜ ጠፍቶ ሊሄድ ቢል አሁንም አስረው አምጥተውታል፤ ቢሆንም ግን ክህነት ሊሾሙትም ባሉ ግዜ ክህነት አይደገምም እና ክህነት እንዳለው ተናግሮ በክህነቱ መሰየም ጀመረ። ገባሬ ሰናይ (ገባሬ ሰናይ የእየሱስ ክርስቶስ ሌላኛው ስሙ ነው፤ የደግ ነገር ሁሉ ምንጭ አንተ ነህ ሲለው ነው) ሆኖ አሃዱ ባለ ግዜ የድምጹ ቃና መላእክት የሚነጠፉለት የሚመስል ጸጋ የበዛለት ሰው ፤ ምእመናን ከእጁ ቡራኬ ሊቀበሉ የሚሻሙበት ደገኛ ካህን፤ ህይወቱ በሰዎች ፊት እንደ መጸሃፍ የተገለጠ፤ ለጸሎት የማይደክም፤ ከመቅደስ የማይለይ ደገኛ አባት መሆኑ ማንንም የሚገዛ ሆነ።

በመጨረሻም ይሕን እንደ እንጨት ለቃሚ በገዳም ውስጥ መኖር የጀመረ አባት እራሱን ቢደብቅ ጸጋው ግን እራሱን በራሱ እየገለጠበት በሰው አገር በሞገስ መኖሩን ቀጠለ፤ ሁሉ የሚታዘዙለት ይኽ አባት በመጨረሻም ጵጵስና እንዲቀበል በተጠየቀ ግዜ ግን የእስክንድርያው እልመፍርያኖስ መሆኑን ለመጀመሪያ ግዜ ገልጦ ተናገረ። ከመንበሩ በውድቅት ሌሊት ተነስቶ እንደወጣ የቀረው የዚህ ደገኛ አባት ነገር ለብዙዎች የእግር እሳት ሆኖ ይኖር ነበረና ዜናው በቁስጥንጥንያ፣ በደማስቆና በእስክንድሩያ ተሰማ። ይኽን የሰማው የእስክንድርያው አባት ግን ክፉኛ ነፍሱ ታወከ፤ “አባቴን እንዲህ አሳዝኘው ኖሯል” ብሎ አምርሮ አለቀሰ። አምላኬ ቢታረቀኝ ብሎ አባ እልመፍርያኖስ እንደሄደው እርሱም ከመንበሩ ወርዶ ከግብጽ ተነስቶ ፋርስ ድረስ በባዶ እግሩ በመጓዝ ከጉልበቱ ስር ተደፍቶ “ፍታኝ፣ መንበሩንም ተረከበኝና ለቀረችው እድሜየ የንሳሃ እድል ስጠኝ” ብሎ ተማጽኖታል።

በእንዲህ አይነት ደገኛ አባቶች ገድልና ትሩፋት ያሻበረቀው የቤተክርስትያናችን ታሪክ ዛሬ የፈረንጅ አሳማ-የፈረንጅ አሳማ፤ በሚሸቱ፣ በደደቢቱ አቢዮታዊ ዲሞክራሲ የተጠመቁ ዘረኛ ወንበዴዎችና ሃሳውያን መፈንጫ ሆኗል።ለኔ “አባ ኃይለ ማርያም” ነኝ የተባለው መናፈቅ ከከበቡን ከብዙዎቹ መሳጢ ተኩላዎች አንዱ ነው።

የጻድቁ እልመፍርያኖስ በረከቱ ይድረሰን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Click here to connect!