በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የህዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!

March 20, 2014

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሰጠው መግለጫ

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የህዝብ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነው ተቃዋሚዎች ” ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ ” ጥያቄ ለመመለስ በስትራቴጂ አምስት ዓመት እቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት አስቆጥረዋል:: የውህደቱ ጉዳይ ለአንድነት ፓርቲ የአንድ ሳምንት ጥያቄ ሳይሆን ስትራቴጂ ግብ ነው:: የዚሁ አካል የሆነው እንቅስቃሴ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲዎች መሐከል መካሄድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል:: ሂደቱን ለመቋጨት በርካታ ድርድሮችና የደብዳቤ ልውውጦችም ቢከናወንም እነሆ አሁንም ተጨባጭ ውጤት በተግባር አለመታየቱ የሁለቱም ፓርቲ አባለት በጅጉን እያሳዘነ ነው::Andenat Party UDJ

በተለይ በቅርቡ እየተካሄደ ከነበረው ተግባር መካከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈልንን ደብዳቤ መሰረት በማድረግ የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲገናኙ የተጠየቀው ጥያቄ በደስታና በላቀ መንፈስ ተቀብለነዋል:: በዚሁ መሰረት መጋቢት 4 ቀን 2006 ዓ.ም ለፊት ውይይት የምንፈልገውና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተጠራውና የሁለቱ ፓርቲዎች የብ/ም/ቤት አባላትና የላዕላይ ም/ቤት አባላት በተገኙበት ለታሪክ በተቀረፀ ወሳኝ ስብስባ ስፊ የሃሳብ ልውውጦች ተካሂደው የፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የሚከተሉትን አስገዳጅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ነበር ::

በዚሁም መስረት:-

1. የሁለቱም ፓርቲዋች አባላት አላስፈላጊ ጥቃቅን ጉዳዮችን በማንሳት ውህደቱን አታጓቱ ውህደት የማትፈፅሙ ከሆነ እኛ አባላት በራሳችን ውህደት እንፈጽማለን የሚል ጥብቅ ተማፅኖና ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል::

2. በአጠቃላይ የሁለቱ ፓርቲዎች ፕሬዝደንቶችና አደራዳሪ ሽማግሌዎች በገቡት ቃል መስረት ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ቅድመ ውህደት የመግቢያ ሰነድ እንዲፈረም ከስምምነት ተደርሶ ነበር ::

3. የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የውህደት አስፈፃሚውን ጠቅላይ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑትን የስም ዝርዝር የፊርማው ሰነ ስርዓት በሚከናወንበት እለት እንዲያመጡ ተስማምተን ነበር ::

በከፍተኛ አመራሮች በሁለቱ ስራ አስፈፃሚዋች ውሳኔ መሰረት የሁለቱ ፓርቲ ፕሬዝደንት ተሰማምተው የቅድመ ውህደት መግቢያ ሰነድ በሁለቱ ፓርቲዎች የድርድር ኮሚቴ አባለት መካከል ተፈራርመን ሆቴል ተከራይተንና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝባዊ ሰብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ ክፍል የዕውቅና ሰነድ አግኝተን የመጨረሻ የሰነ ሰርዓቱን መርሃ ግብር በመጠባበቅ ላይ እያለን በድንገት በመኢአድ ፕሬዝደንት በኩል በቁጥር መ /ኢ/አ/ድ 278/06 መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም በዕለቱ የቅድመ ውህደት ፊርማውን መፈረም እንደማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓርቲያችን መድረሱ በእጅጉ አሳዝኖናል::

ከደብዳቤው እንደተረዳነው መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ከበርካታ የሃሳብ ልውውጥ በኋላ የደረሱበትን ውሳኔ የሚቀለብስ የሁለቱ ፓርቲዎች ተደራዳሪዎች እየተሰማሙ በቃለ ጉባኤ ያፀደቁትንና ከሁሉም በላይ የሁለቱ ፓርቲ ተደራዳሪዎች ለቅድመ ውህደት ባዘጋጁትና ባፀደቁት የመግቢያ ሰነዶች ላይ የሰፈሩ ነጥቦችን እንደ አዲስ በማንሳት በጥቃቅን ጉዳዮች በመጠመድ የቅድመ የቅድመ ውህደቱ እንዳይፈረም ተደርጓል ::

ለዚህ ታሪካዊና የሕዝብ ጥያቄ መደናቀፍ ምክንያት የመኢአድ ፕሬዝደንት ሲሆኑ ይህን ሆኔታ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ለሁለቱ ፓርቲዎች አባላት ደጋፊዎች በግል ተነሳሽነትና በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት ሂለቱን ፓርቲዎች ለማደራደር ሲደክሙ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ለህዝቡ ጥሩ ዜና ባይሆንም ላለመፈረሙ ሃላፊነቱን የሚወሰዱት የመኢአድ አመራሮች በተለይ ፕሬዝደንቱ መሆናቸውን ማሳወቅ እንወዳለን ::

በዚህ አጋጣሚ ለውህደቱ መሳካት የመኢአድ አባላትና ከፊል አመራሩ እያሳዩ ለሚገኘው ፍላጎትና ጥረት ፓእሪያችን መልካም አክብሮቱን መግለፅ ይወዳል ::

መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም

አዲስ አበባ
Andenar (UDJ)
andenat

17 Responses to በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የህዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!

 1. Selam Reply

  March 25, 2014 at 8:27 pm

  Endelebu esun ketewahadu behuwala abalatu bimertu ayshalem? likemenber kalhonku maletus yeseltan susegna ayasmeselebachewum? abalat yemeretu bilu teru neber ene gen kante yehen altebekum neber ayeee lekanes qefowoch nen hmmm

 2. SewAle Reply

  March 23, 2014 at 10:50 pm

  Who gave the mandate for “Andinet” to unilaterally give press release?
  As long as the two parties are working together for reunification, any difficulty to resolve outstanding issues should be addressed in a joint press release. However, what we see here is “Andinet” playing a dirty game to hijack AEUP.
  There is no duplication here. Unless you are a fan of Andinet you have post it.

  • alemayehu Reply

   March 25, 2014 at 5:56 am

   Dear Sewale

   You see the culture of labeling some one and painting with a color you want any one with different idea to appear the way you want

   Please look to your message how you clearly expressed your hate for “Andinet”
   When it comes to me my message serves for both,my recomendation to any of them is to resolve their conflict and if they cant to see an expert in the area if not to leave the plat form for others who could.

   Please try to help to narrow the gap in a constractive message.
   Thanks

 3. alemayehu Reply

  March 22, 2014 at 9:10 pm

  This is foolish,and irresponsible practice, first of all you cant unite because of “Shemagelewoich”intervention, You have to resolve your political difference, you need to have a short and long term strategy. Please be open minded and stop being greedy of power.

  It is shame you people repeatedly committing mistake, if you continue in this manner, you will never see that power you wish to have to be a master of those poor innocent Ethiopians.

  At least to reach to your dream be tolerant to each other and come together, if you are in short of skill to resolve your difference get a consultant, an expert in conflict resolution.

  Please don’t be”Mesalekeya” or “Mesakya”

  If you can’t make it leave the political field and let other play.

  Thanks

 4. getachew Reply

  March 22, 2014 at 7:12 am

  ስሜ ጌታቸው ይባላል ትውልዴ ጎንደር ነው። በየ ድረ-ገጹ አንዳንድ መጣጥፎች አስነብባለሁ። የትግራይ ወንበዴዎች ፋሽስታዊ ድርጊት እንዳለ ሆኖ ኢትዮጵያውያን ይህን ፋሽስታዊ ድርጊት ለመቅበር የሚያካሂዱትን « ሦሥተኛውን አብዮት» የሚያንኮላሹት የተቃዋሚ ኃይሎች ናቸው ብሎ ያለምንም ስጋት መናገር ወይም ሁሉንም ጠርቶ መናገር ቢቻል አይችሉትም እንጅ የተቀደደ ጆንያ አይነት መሆናቸውን እስኪበቃቸው መንገር እችላለሁ። በኢትዮጵያ ዓምላክ በሕዝብ ዓምላክ አንድ ሁናችሁ ምሩን የናንተን ዝባዝንኬና ዘውደኝነት መስማት ደክሞኛል።ስንቱ ባለዘውድ ስንቱ ደጃዝማች ይሁን?ኧረ በቃን ትግሉ ይጀመርና እንቀላቀለው እዚህ በባእድ አገር ማን የማንን ዲሽ ያጣባል?

 5. T.Goshu Reply

  March 21, 2014 at 11:01 pm

  Well, if the points of reason stated in the statement of UDJ are true, I strongly believe making the unfortunate setback because of the very few top leaders of AEUP is the right think to do. Imagine how it is extremely , if not stupidly outrageous to send a letter of regret not just at the eleventh hour but at the time the AEUP president and his close associates were early expected to put their signature of pre-merger or pre- unification document. I do strongly argue that this is kind of behavior cannot and should not be tolerated and treated endlessly with a very clumsy political culture of appeasement . The people of Ethiopia cannot and should not accept these kinds of very ugly political personalities from which they suffered for a quarter of a century ( 1991- present). Absolutely no way if we want to shorten the general crisis in which we found ourselves ! The members and supporters of those parties are in a very critical movement to get rid of those party leaders ( be it UDJ or AEUP any other for that matter)who have no a real sense morality let alone doing things rationally and constructively . They must be unequivocally be told that they have done more than enough damage to the progress towards freedom and justice and this kind of political game is no more tolerable ! Yes, we must call spade a spade when it is necessary.
  Imagine fellow Ethiopians, how these so-called politicians ( a few individuals) are getting heatless, if not mercilessly selfish . this kind of behavior is not considered or viewed only as a very dirty political game but it is also inhuman. Yes, the mentality of keep playing politics with the a very wild and voracious egoism must be engaged critically and rationally and courageously. I strongly disagree with those fellow Ethiopians who look uncomfortable with the very appropriate and timely statement by UDJ. There should not be any foolish type of appeasement or patience to those who are intended to paly their politics of ” My way or the high way”. We had enough deadly political game being played by the ruling party !!

 6. chuchebe Reply

  March 21, 2014 at 9:38 pm

  ፋይዳ የለሽ መግለጫ ነው። ወደ መነጋገር ሳይሆን ወደ መካረር የሚያመጣም ነው። በይደር ይዞ ከአባላት ጋር መነጋገርና መሬት ጠብ የሚል ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ወደ አንድ መምጣት ይቻላል። ድርጅቱ ባይመጣም አባላቱ ያኔ ይመጡ ነበር። አሁን ጣት መጠነቋቆልና ወያኔን ማስደሰት ይሆናል፡ ብቅ ያሉ መሪዎችን እንደ ሻማ እያቀለጡ ማየት ያስተዛዝባል። መሪያችን ይፈታ ብሎ ሰልፍ መውጣት የተሻለ ስራ ይመስለኛል። I am just sayin’አለ እንደልቡ ቂ ቂ

 7. menethio Reply

  March 21, 2014 at 8:31 pm

  እረ ዳቦዬን ነጠቀኝ ጨዋታ አለቀ አልጫወትም ያለዉን የሰፈራችን አኩራፊ ሕጻን ልጅን ሆናችሁሳ…. መዋሃድ ካልቻላችሁ ጊዚአችሁን በከንቱ ከማጥፋት በራሳችሁ ፐሮግራም ላይ ጠንክራችሁ መስራት ነዋ ጊዜን በከንቱ ፈርም አትፈርም ከማባከን ጠንክሮ የሰራ ህዝብን መሰብሰብ ይችላል,,, ወይስ የመጨረሻዉ ትልቁ ግብ የፓርቲ ሊቀመነበር መሆን ነዉ ወይስ የኢትዮጵያን ህዝብ ለነፃነት ማቅረብ ይሆን? የቱ ነዉ ትልቁ ህልም?,,

  ኢትዮጵያ ማለት ፍቅር,,,

 8. Abegaz Reply

  March 21, 2014 at 4:34 pm

  Get civilized, Andnet party. You just do not blame by name calling. All you have to say is, “because of some outstanding issues the planned merger between the two parties has not been possible for the moment, and we hope it will be done in the future.”

 9. zignet Reply

  March 21, 2014 at 2:02 pm

  ማናችሁም ብትሆኑ ንጹሓን አይደላችሁም ፤ (ሁሉም አጠፉ አንድም ፃድቅ የለም መፃፍ ቅዱስ )
  ዛሬ ወገናችን መሰረታዊ ፍላጎት አይገባህም በተባለበት በዘመነ ልማትና እድገት
  ሁለቱም ፓርቲዎች በህዝቡ መሃል እየኖሩ ችግሩን በአይነብረቱ እያዩ ግድ ካላላቸው ድሮም ለሀገርና ለወገን ስላልነበር የልባችሁ ፍላጎት ፍንትው ብሎ ታየ እናመሰግናለን
  ለሌሎች አመራሮችና ደጋፊዎች የምጠቁማችሁ ነገር ቢኖር እነንህ ግለሰቦች መንግላችሁ አስወግዱና ውህደቱም ሆነ ስራው በቀና እውነተኛ ልጆች ትግሉ ወደፊት ይራመድበት ካልሆነ ደግሞ በሰበብ አስባብ ንፁሃን ወገኖቻችን አታሳስሩን አታሰቃዩብን።
  ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ፤ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ብክብር ትኑርልን አሜን።

 10. abdu Reply

  March 21, 2014 at 10:44 am

  ሁለቱም ያረጁና ስልጣን ሽኩቻ የተጠናወታቸው ፖለቲከኞች ናቸው። ኢንጀነር ግዛቸው ያዳከመውን ፓርቲ አንድነትን ተመልሶ እመራለሁ ማለቱ ለምንድን ነው? ጥቅም ፍለጋ ነው? ካሜሪካ የሚመጣ ዶላር ፍለጋ ነው? አንዱአለም ለምን እንዲረሳ ይደረጋል??

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>