ግርማ ካሣ ቀልድ ጨምሯል!

December 10, 2013

ነጻነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ

የግርማ ካሣን ጽሑፎች አልፎ አልፎ አነባቸዋለሁ፡፡ ሀገር ወዳድ መሆኑን ይጠቁማሉ – ጽሑፎቹ፡፡ ታታሪ ሰው ይመስለኛል፤ በጥረቱና በሀገር ፍቅር ስሜቱ እወደዋለሁ፡፡ ሁልጊዜ ሳይታክት ይጽፋል፡፡ ሳይታክቱ የሚጽፉ ብፁዓንነት የሚበዛባቸው ቢሆን ዕድለኞች ግን ናቸው፡፡ ብዙዎቻችን እየደከመን መጻፍ ቀርቶ ማንበባችንንም እያቆምን በምንገኝበት ሰዓት አዘውትሮ መጻፍ መታደል ነው፡፡

አያ ግርማ ሰሞኑን የጻፋቸውን ሁለት ያህል መጣጥፎች አንብቤያለሁ፡፡ ሁለቱም ግንቦት ሰባትን ለመንቀፍ ብዕራዊ አንደበታቸውን ያሾሉ ናቸው፡፡ መነቃቀፍ በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ አግባብነትና እውነት ያለው መነቃቀፍ ወይም መወቃቀስ የዕድገት መሠረት በመሆኑ ሊጠላ አይገባውም፡፡ ነቀፌታንና ትችትን መፍራት ብልህነት አይደለም፡፡ ብሂሉ “ያልተቀጣ ሕጻን ሲቆጡት ያለቅሳል” እንደሚል አንድ በግለሰብም ይሁን በቡድን ደረጃ የሚገኝ አካል ጥፋት ካለው ያን ጥፋት በተጨባጭ መረጃና ከተገኘም ማስረጃ ነቅሰው ቢመክሩት መካሪውን “አንተን ብሎ መካሪ፤ ለራስህ ምን ታውቅና” በማለት ምክሩን ላለመቀበል መሞከር አስተዋይነት የሚጎድለው ጠያፍ ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላው ቀርቶ ዕብድና ማይም ቢሆን እንኳን፣ ለሰው የሚያስላልፈው ገምቢ ሃሳብ አያጣም፡፡ ችግሩ መናናቅ ካልሆነ በስተቀር ወይም ጭፍን ጥላቻ ካላወረን አንዳችን ለአንዳችን ጥሩ መስተዋት ነን፡፡ ስንተቻች ግን የተደበቀ ሌላ አጀንዳ የምናራምድ ለመሆናችን ፍንጭ የሚሰጡ በቀጥታ ወይም በዐይነ ውሃችን የሚታወቁ ስስ ስሜቶች ከታዩብን ሚዛናዊነታችን ጥያቄ ውስጥ ይገባና ትዝብት ላይ ልንወድቅ እንችላለን፡፡ ጭፍን ፍቅርና ጭፍን ጥላቻ ሁለቱም በእኩል መንገድ ጎጂዎችና ጥቁር ጥላ የሚጥሉ ናቸው፡፡ መግባባት ሳይሆን መናቆርና ከንቱ መተቻቸት እንዲስፋፋ ያደርጋሉና ከነዚህ መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ለገምቢ ምክርና አስተያየት ልቦቻችንን ቀና አድርገን ብንሳሳብ ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ አለበለዚያ የዱሮው ጥፋት በአዲስ መንፈስ ወደአዲስ ሰውነት ውስጥ እየተዛነቀ መስማማት ሳይኖር እንደስከዛሬው እየተቋሰልንና እየተዳማን እንኖራለን፡፡ ለማንኛውም በዚህ ረገድ ልቦናችንን ክፍት ብናደርግ ጥሩ ነው፡፡ መገፈታተር ይብቃንና ስሜት ለስሜት ለመናበብ እንጣር፤ አንጎዳበትም፡፡

የግርማን መጣጥፎች የምመለከተው እንግዲህ ከዚህ በላይ ከጠቆምኳቸው ሃሳቦች በመነሳት ነው፡፡ ግርማ ግንቦት ሰባትን ለመንቀፍ የተጠቀመባቸውን አንዳንድ ቃላት አልወደድኳቸውም፡፡ በቀዳሚው ጽሑፉ ላይ የኢሕአዴግን ግንቦት ሰባትን አለመፍራት ለመግለጽ የተጠቀመባቸው ቃላትና ድምፀቱ ራሱ (ቶን) ለትችት የሚዳርገው ነው፡፡ በመጀመሪያ “ኢሕአዴግ ግንቦት ሰባትን አይፈራም” የሚለው ነገር ከግርማ ሣይሆን ከራሱ ከኢሕአዴግ ቢወጣ የተሻለ ነው – ግርማ የኢሕአዴግ ቃል አቀባይ እስካልሆነ ድረስ ማት ነው፤ በርግጥም በማግሥቱ ኢሕአዴግ ከምልክት ቋንቋና ከተግባራዊ እንቅስቃሴው ባለፈ በግልጽ “ግንቦት ሰባት ያሰጋኛል” ቢል ግርማን ማጣፊያው ያጥረዋል፡፡ ግርማ ቢያንስ በለዘበ አማርኛ “ግንቦት ሰባት አሁን ባለው (ወታደራዊ) አቋሙ ኢሕአዴግን የሚያስፈራው አይመስለኝም፡፡ ጊዜው ገና ነውና ኢሕአዴግ በጦር ማንንም የሚፈራበት ሁኔታ በግልጽ አይታየኝም፡፡…” ቢል የእኔንም ብዕር ባላናገረ ነበር፡፡ ግና አንዳች ነገር በሚያስጠረጥር ሁኔታ ግርማ የኢሕአዲግን የሕዝብ ግንኙነት ሥፍራ መውሰዱን መገመት ችያለሁ – ባለማወቅ ሊሆን እንደሚችልም አስባለሁ፡፡ ይህንን ስል ደግሞ ከጽሑፎቹ አጠቃላይ ይዘት በመነሣት ግርማን በወያኔነት ለመክሰስ ወይም ከነጭራሹም ለመጠርጠር በቂ ምክንያት አለኝ ለማለት እንዳልሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡

በበኩሌ ኢሕአዴግ እንደግንቦት ሰባት የሚፈራው ነገር እንደሌለ በሙሉ ልብ እመሰክራለሁ፡፡ ይህን ስል ግንቦት ሰባት አንዳንድ “ወዳጆቹ” እንደሚሉት ከ30 የማይበልጡ ተዋዎች ኖሩትም ዜሮ የተዋጊ ኃይል ኑረውም ያ ከጉዳይ ሳይጣፍ ነው፡፡ ግንቦት ሰባት መጠሪያው ብቻ ወያኔን የሚገባት እንደሚያሳጣው በስድስተኛው ሕዋሴ እረዳዋለሁ – ስሙ ብቻውን ያምጰረጵረዋል፡፡ ጠላት በሁለት ይከፈላል – ተጨባጭና እምቅ ተብሎ፡፡ እንደማንኛውም ጠላትና ወዳጅ አፍሪ አካል የወያኔ ጠላቶች ሁለቱም ናቸው፡፡ ይበልጥ ወያኔን የሚያሰጋው ጠላት ግን ከተጨባጩ ይልቅ እምቁ ነው፡፡ እምቁ ወደተጨባጭነት የሚለወጥበትን ሰዓት ደግሞ ወያኔ ቀርቶ ሰይጣንም ላያውቀው ይችላል፤ ግርማም እኔም አናውቀውም – ግን ያስፈራል፡፡ መፍራ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው፤ በአለመፍራት ጮቤ አይረገጥም፡፡ አልፈራም የሚል ጀብደኛና ጉረኛ ብቻ ነው፡፡ ግንቦት ሰባት ያነገበው ዓላማ በመላው ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚደገፍ ዓላማ ነው፡፡ ግንቦት ሰባት ሲጠራ ወያኔ የሚርበተበተውና ይይዘውንና ይጨብጠውን የሚያጣው እንግዲህ ንቅናቄው በኒኩሌር መሣሪያ ትጥቅ ታምቶ ሳይሆን በዚህ ንቅናቄ የትግል መቅደስ ውስጥ በክብር ታቅፋ የተቀመጠችው የወይዘሪት ነጻነት ፅላት ባልታሰበ ቅጽበት አፈትልካ ወደሕዝቡ መሀል የገባች እንደሆነ በወያኔና ጭፍሮቹ ላይ ሊደርስ የሚችለው አደጋ ከወዲሁ ቁልጭ ብሎ እየታየው ነው፤ ሌላ አይደለም፡፡ ለአቶ ግርማ ግልጽ ሆኜ ከሆነ ወያኔ ግንቦት ሰባትን አሳምሮ ይፈራዋል፡፡ ይህን ተጨባጭ የሚመስል ነገር በመናገሬ በግንቦት ሰባትነት ልፈረጅ አይገባም፡፡ ግርማን በወያኔነት መፈረጅ እንደማይገባን መከራከሬ እኔንም ነጻ ለማውጣት ነውና እኔንም ባለመፈረጅ እባካችሁን ተባበሩኝ፡፡

በዛሬው መጣጥፉ አቶ ግርማ ለዚሁ ንቅናቄ አንድ ግልጽ ደብዳቤ ጽፎ በዘሃበሻ ላይ አስነብቦናል፡፡ ብዙዎች የመንጫጫት ያህል ብዙ ነገር ጽፈዋል፡፡ ለወደፊቱ እንደዚህ መሆን የለበትም – “የአህያ ‹ጓዝ› በሆድ ይያዛል ነው”ና ለአንዳንድ ንግግሮችና ትችቶች ብዙ ክብደት መስጠት ቢያንስ ጊዜን ይሻማል፤ የትኩረት አቅጣጫንም ያዛባል፡፡ አንድ ሰው የመሰለውን ሲጽፍ በመጣበት መንገድ ተጉዞ በጽሑፍ ተገቢውን መልስ መስጠት እንጂ መሳደብና ሌላ ሌላ ታሪክ መቸክቸክ አስፈላጊም ተገቢም አይመስለኝም፡፡ ሥራ ፈት ወያኔዎች እንደዚያ ቢያደርጉ ሥራቸው ነውና ምንዳም ያገኙበታልና ምንም አይደል ሊባል ይችላል፡፡ በትግል ላይ ከሚገኙ ወገኖች ውስጥ በዚህ ዓይነት የአንድን ታዋቂ ጸሐፊ ስም ለማጉደፍ በመሞከር ሙያ ላይ የተሠማራ ሰው ካለ ግን ስህተት ነውና ለወደስተፊት ይታረም፡፡ እውነት እንደሆነች በብዕር ቱማታ ይቅርና በመትረየስና በታንክም ቢሆን ከላችበት ቦታ ንቅንቅ አትልም፡፡ ግንቦት ሰባት ከሻዕቢያ ሥር መወተፉ በርግጥም ሀገርን የሚጎዳ ነገር ካለውና ድርጅቱ ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ሃሳብ መሰንዘር የዜግነት ግዴታ እንጂ እንደባይተዋር ሊያስወቅስና ምን አገባህ ሊያስብል አይገባም፡፡ ቅስምን ለመስበር የሚደረገው ጥረት በብልህነትና በአስተዋይነት ቢቀየር መልካም ነው፡፡ ስለጋራ ሀገራችን መጨነቅ የሁላችንም ኃላፊነትና ግዴታም ነው፡፡

በበኩሌ ግንቦት ሰባት ከሻዕቢያ ጋር ብቻ ሳይሆን በዓለም አሉ ከሚባሉ አምባገነኖች ጋር ተባብሮና ዕርዳታም አግኝቶ ኢትዮጵያን ነጻ ቢያወጣ ደስተኛ ነኝ፡፡ ዝንጀሮዋ “ቀድሞ የመቀመጫየን” ነው ያለችው፡፡ ተደጋግሞ በብዙዎች እንደተነገረውም የአንድን ድርጅት የመታገያ መስመር የሚመርጥለት ራሱ ድርጅቱ እንጂ ሌላ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህን ስል ኤርትራ ለኢትዮጵያ ነጻነት የምትቆም ሀገር ስለመሆንዋ መጣጥፋዊ ዋስትና ዋስትና እየሰጠሁ እንዳልሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን ወያኔ በምንም መንገድ ከሻዕቢያ የተሻለ እንዳልሆነ በመሃላ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፡፡ ትልቁ ዕንቆቅልሽ…

ትልቁ ዕንቆቅልሽ አቶ ግርማ ግንቦት ሰባትን ከኤርትራ አውጥቶ ወደሀገር በማስገባት ከነሸንጎና ከነአንድነት ጋር በመተባር ወያኔን በ“ሰላማዊ ትግል ድባቅ እንዲመታ” ያደረገው ፌዘኛ ጥሪ እጅግ አስገርሞኛል፡፡ አቶ ግርማ አንዳንድ ነገሮችን ለማሰብ ሲፈልግ እንቅልፍ ይይዘዋል፡፡ አንዳንድ ነገሮችን ለማሰብ  ሲፈልግ ደግሞ ይነቃል፡፡ ግንቦት ሰባት ምርጫ አጥቶ ወይም ካሉት ምርጫዎች ውስጥ የመረጠውን መርጦ ወደ ትግል ሜዳ እንደገባ ነግሮናል፡፡ እሱ በዚያው ይቅናው ብለን ከመጸለይ ይልቅ ሳቢውን ግረፈው እንዲሉ ወደማይሠራ የትግል ሥልት በመጋበዝ ቃሊቲ እንዲወረወሩ ወይም ቀድሞ በተፈረደባቸው ፍርድ እንደነመንግሥቱ ንዋይ ተክለ ሃይማኖት አካባቢ እንዲንጠለጠሉ ለማድረግ የተሸረበ ሤራ ያለ ይመስለኛል፤ ለምን? ትግሉ ቢኮላሽ ማን ይጠቀማል? እነብርሃኑ እኛን ምን አምጡ አሉና አስቸገሩን? ለምንድነው አንድ መሆን ካተቻለ፣ መስማማት ካልተፈለገ ሁሉም በመሰለው መንገድ ታግሎ ሁላችን የምንፈልጋት ነጻነት እንድትገኝ ዕድል የማንሰጠው? ማደፍረስ የሚቀናን ለምንድነው?

ትግሉን ለማወክ ካልሆነ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ – ሰላምን በማያውቅ የወያኔ መንደር ውስጥ ሰላማዊ ትግል ፍለጋ እንዴት ኑና እጃችሁን ስጡ ተብሎ ይጻፋል? ችግሩ መጻፉ አይደለም – የተጻፈው ነገር ተግባራዊነት ግን አልተጤነበትም ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ግርማ ዐይቹን ጨፍኖ የጻፈውን ነገር እንደገና እንደሚያጤን እገምታለሁ፡፡ በአሁኒቷ ቅጽበት ማን ነው ለኢትዮጵያ አደገኛ? ግንቦት ሰባት ወይንስ ወያኔ ወይንስ ሻዕቢያ? ልብ ይደረግልኝ – ወደ “ጥንት” ታሪክ አልገባሁም፡፡

አቶ ግርማ ካሣ፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? እውን ወያኔ ለሰላማዊ ትግል በሩን ከፍቷል? በዓለም ዙሪያ ያሉ ወገኖቻችን ስለሳዑዲዎች አረመኔነት ለመግለጽ ለወገናቸው ሲሉ በየሚኖሩባቸው ሀገራት ዋና ዋና ከተሞች ሲሰለፉ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ በሰማያዊ ፓርቲ ሰልፎኞች ላይ የተደረገውን ሰምተሃል ወይንስ ያኔ በሀገር ውስጥ አልነበርክም? ከዚህ የነሰ ትንሽ መብት የት አለ? ለዚህች ሚጢጢዬ መብት – በሌሎች ሀገራት የተፈቀደ – በኛዎቹ ናቡከደነፆሮች ግን በኃይል እርምጃ የተደፈጠጠ ሰልፍ ምን ያመለክታል? እርግጠኛ ነኝ ግርማ እዚህ ቦታ ስትደርስ በጻፍከው ነገር ልትፀፀት ትችላለህ፡፡ እነእስክንድር ነጋ ለምን ዘብጥያ ወረዱ? … ወያኔን በሰላማዊ ትግል ፈቃጅነት መፈረጅ ራሱ እንደኔ ከሆነ ወንጀል ነው – በኢትዮጵያውያን ደም መቀለድም ነው፡፡ ስዚህ አንተ ግንቦት ሰባትን እንደፈለግህ ጥላው ነገር ግን በነሱ ሰበብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰላማዊ ትግል ሁሉም ነገር የተመቻቸ ነው በሚል ቃና የምታስተላልፍላቸውን የኑ ታረዱ ጥሪ በፍጹም አልተቀበልኩትም፤ እነሱን መጉዳት ከተፈለገ ሌላ መንገድ መፈለግ ይቀላል፤ ለወያ ግን አይስጣቸው፤ የወያኔን ቅጣትና የበቀል እርምጃ  “ለጠላትም አይስጥ”፡፡ “የደላው ሙቅ ያኝካል” አሉ፡፡ ለኔ አደገኛ ሆኖ ያገኘሁት ግንቦቶች ለወደፊቱ ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብሎ ከሚሰጋ አደጋ ይልቅ አሁን በመጣጥፍህ ውስጥ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ትግል መንግሥትን እንታገለው የሚለው የደናቁርት አስተሳሰብና የወያኔ ጭራቅነት ናቸው፡፡ ወያኔ ከጦጣና ዝንጅሮ የሰውነትና የአእምሮ የዕድገት ደረጃ ባልወጣበት ሁኔታ፣ ዘረኝነት ከአጥናፍ አጥናፍ ሀገሪቱን ሰቅዞ ይዞ መግቢያ መውጫ ባሳጣን ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነቱ ገድሎ ሊጨርሰን ባሰፈሰፈበት ሁኔታ፣ የትግሬዎች የበላይነት ነግሦ ሁሉም ነገር በነሱ ቁጥጥር ሥር ሆኖ እኛ የበይ ተመልካች በሆንበት ሁኔታ፣ … ምን ዓይነት ጥሪ ነው ለግንቦት ሰባት የምታስተላልፍላቸው? አሁን እነዚህ ሰዎች ከወያኔ ይበልጥ ለኢትዮጵያና ሕዝቧ አደጋ ሆነው ነውን? ለምን አንዳንዴ፣ እንዲያው ሲያመቸን አንዳንዴ እንደጤናማ ኢትዮጵያዊ ሆነን አናስብም? እስኪ እነዚህ ሰዎች የት ይሂዱና ትግላቸውን ይጀምሩ? አይ፣ እያሰብን እንጻፍ፤ እንናገርም፡፡ ለኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከሰይጣንም በባሰ ሁኔታ ታላቁ ጠላት ወያኔና እርሱ የዘረጋው የዘረኞች የቢዝነስ ኢምፓየር ነው፡፡ ከአፓርታይድ የሚበልጥ የጭራቆች ንጉሠ ነገሥት ወያኔን አራት ኪሎ አስቀምጦ ስለሻዕቢያ ማውራት፣ ታላቁን የመለስ ሙት መንፈስ ቤተ መንግሥት አስቀምጦ ስለግንቦት ሰባት “አደገኛነት” ማውራት የበቅሎዋን ተረት መተረት ነው፤ “በቅሎ አባትሽ ማን ነው?” መልስ፡- “እናቴ ፈረስ ነች!” አስፈላጊ ከሆነ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ፡፡

16 Responses to ግርማ ካሣ ቀልድ ጨምሯል!

 1. በለው! Reply

  December 15, 2013 at 5:31 am

  <<<ግርማ ካሳ ጥሩ አጫዋችነቱ ጨምሯል…ስለሚያውቃት ኤርትራ ሲነገር ስለኤርትራውያን አለቆቹ ሁልግዜም የሚሰጠው ሙገሳ ለየት ያለ አገም ጠቀም ነው ። ከቴዎድሮስ አድሃኖም ሌላ ሰው የለም ሲልም ሰነበተ … ግለሰቡ ፳፫ሺህ ስደተኛ አለን ብለው ፴፰ሺህ ግን ሕጋዊ መኖሪያና ሥራ ፍቃድ አሰጥናቸዋል "ቦንድ ገዝተዋል" ሲሉ ከርመው ፪ሚሊየን ኦውሮ ድራጎት ቦጭቀው ፶ሚሊየን ብር ለመልሶ ማቋቋሚ ተመድቧል ብለው የስደተኛ መርጃ ግን በሳውዲ አረቢያ ያለው ስደተኛ ቁጥር ከ፻፳ሺህ በላይ ነው ከፍተኛው ገንዘብ የተከፈለው በ(IOM)ብሎ መሰከረ።የአቶ ግርማ ካሳ ለአቶ ቶዎድሮስ አድሃኖም የቸሩት አድናቆት ስለምን ነበር!?ኤርትራ ስለኖሩ ነው?

  *አቶ ግርማ ካሳ በተከታታይ ጽሑፎቹ በጠቅ/ሚኒስትር ማዕረግ የሻቢያህወአት ጉዳይ አስፈፃሚውን ለአቶ ኀይለመለስን ይህንንም ያህል አላዳነቋቸውም…ብሄር ብሔረሰብ ስለሆኑ ነው?…ወይንስ ከንባታ ስላልኖሩ ይሆን? የራዕይ አስፈጻሚ እንጂ የራሳቸው ራዕይ ስለሌላቸው ነው? ያስተዛዝባል!?
  *አንዳንድ ጭፍን ደጋፊ ተደጋፊ፣ ጭፍን ተቃዋሚና አቋቋሚዎች ግራ ያጋባሉ።እነሱ ያልገቡበት ፖለቲካ ሁሉ ስሕተት ነው፣እነሱ ያልመከሩበት ዕቅድ ሁሉ አይሳካም፡አልሃቸውን ለመወታት (ለበቀል0 የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይለብሱት ማሊያ የለም፡፤ ለማናቸውም ማጭበርበርም ይሁን ለህዝብ ዘለፋ እራሳቸውን አጠናክረው ከድረገፅ ድረገፅ በመገለባበጥ አርዕስት በመቀየር አንድቀን ደጋፊ፣ ሌላ ቀን ተደጋፊ በአብዛኛው(የተንታኝ በታኝ) አጥፊ በመሆን ስድብ ለመጠጣት ቆርጠው ከተነሱ ሰወች መካካል ቀዳሚዎቹ…ግርማ ካሳ፣ጃዋር መሀመድ፣ ተስፋዬ ግብረእባብ፣ያሬድ አይቼህ፣ክፍሉ ሁሴን፣ ዳንኤል አሰፋ፣ዳንኤል ገዛኸኝ፣መስፍን አማን፣ፀሐዬ ደባልቀው፣ … ይጠቀሳሉ። በእውነቱ በስድብ የሚገኝ ትቅም ጥንቅር ቢልስ…በአሁኒቷ ቅጽበት ማን ነው ለኢትዮጵያ አደገኛ? ግንቦት ሰባት ወይንስ ወያኔ ወይንስ ሻዕቢያ? መስከረም ፪ ግንቦት ፯፣ግንቦት ፳..ሰኔ ፴ ያው ነው። *መጀመሪያ ህዝብ እራሱን ካላወቀ የነፃነትን ምንነት አይረዳም ስለዚህ በግድ ነጻ ማውጣት አይቻልም ።ቀድሞ ማንነታችንን አውቀን ቢሆን በህወአትሻቢያ ህገመንግስት(በማኒፌስቶአቸው)"እኛ የፈጠርናችሁ በእኛ ጥላ ሥር ብቻ የምትንቀሳቀሱ" ስንባል እሺ ብለን ቂጣችንን ጥለን ባባዶ ሆድ፣ ባዶ ሜዳ ላይ፣ አንጨፍርም ነበር!"።አራት ነጥብ።
  *አቶ ግርማ ካሣ፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? እውን ወያኔ ለሰላማዊ ትግል በሩን ከፍቷል?
  -ወያኔ አፍ አስከፍቷል የፖለቲካ ምሕዳሩን አስፍቶ "ጃንሜዳ ብቻ!"ብሏል፡ ኢ-ሻቢያህወአት አደባባይ!
  * ግንቦት ፯ የት ይሂዱና ትግላቸውን ይጀምሩ?
  - ዓለም አንድ መንደር ሆነች ስላሉ ምን አልባት ጃፓን ይሂዱ ማለቱ ይሆናል!? ሚስጥሩ ወዲህ ነው ግንቦት ፯ በሌሎች ጎረቤት ሀገሮች ሁሉ መብራት ውሃና መሬት ሰጥተን ስለዘጋንበት የቀረችዋን ኤርትራ ለምን ለግነቦት፯ ዕድል ከምንከፈትለት እራሱ ኢሳያስ አፈወርቂን የኅይለማርያም ደስአለኝ አማካሪ አድረግን አናስገለብጠውም ማለቱ ይመስለኛል።"ኅያለማርያም ገብረማርያምን(መለስን) አጠለቀው..ደብረጺዮን ኅያለማርያምን ባያወልቀው ታዘበኝ!።

  **ለኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከሰይጣንም በባሰ ሁኔታ ታላቁ ጠላት ወያኔና እርሱ የዘረጋው የዘረኞች የቢዝነስ ኢምፓየር (ፋውንዴሽን፤ጥርነፋ፤ኢፈርት፤ኪራይ ሰብሳቢ፤፵/፷ ዲያስፖራ፤ አደር-ባይ፣ ካድሬ፣ሆድአደር ምሁር፤አውርቶ አደር አርቲስትና ጋዜጠኛ) ነው፡፡ ከአፓርታይድ የሚበልጥ የጭራቆች ንጉሠ ነገሥት ሻቢያህወአት የወሮ በላ ቡድን አራት ኪሎ አስቀምጦ ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ ማውራት፣ ታላቁን የመለስ ሙት መንፈስ የሀገር ጥፋት፣የትውልድ ማምከንና ማባከን፤የታሪክ መሰረዝ፣የሀገር ሉዓላዊነት ማፍረስ፣(ራዕይ)ቤተ መንግሥት አስቀምጦ ስለግንቦት ሰባት “አደገኛነት” ማውራት የበቅሎዋን ተረት መተረት ነው፤ “በቅሎ አባትሽ ማን ነው?” መልስ፡- “እናቴ ፈረስ ነች!”የግንቦት አህያ ግን ሳይሆን አይቀርም አለች አሉ። አዎን! ከበቅሎ እንኳን የተሻላችሁ ሁኑ በለው! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ

 2. Megen Reply

  December 14, 2013 at 6:54 pm

  ሰዉ ጥራ ቢሉት ራሱ መጣ አሉ።
  ሰዉ ጠፋና ስነዚህ ዓላማ ቢስ ጊዜ ታጠፋላቺሁ። ጊዜ እኮ ወርቅ ነዉ።
  እሱ እኮ ምን ጻፈ ለመባል እንጂ ጠቀሜታ ያለዉ ነገር ከዓዕምሮዉ እንደማይፈልቅ የታወቀ ነዉ።
  እንደዚህ አይነቱን ዝተት እያረገፉ ለመጓዝ ጊዜዉ አሁን መሰለኝ !!

 3. lantabure Reply

  December 12, 2013 at 7:58 am

  ግርማ ካሳ
  ጹሁፍህን ላነበበ እንደው ምን ዓይነት ጥሩ ሰው ነው ሊልህ ይችላል ማለትም የኢትዮጵያን ሁኔታ ለማያውቅ ማለት ነው፡፡ የሚገርመው አንተ ተወዝፈህ እና ስራ ፈትተህ ሥራ የሚሰሩትን ስራ ባታስፈታ ምነበረበት፡፡ አሁን እንደው ማን ይሙት ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ሰላማዌ ትግል ማካሄድ ይችላልን? ናና ሞክራት ቂሌንጦ ግብተህ እንደ ሻማ ቀልጠህ ትቀራታለህ ቀላባጅ ወስላታ፡፡

 4. Henok Reply

  December 12, 2013 at 1:40 am

  “Do Not Under Estimate The Power Of Stupid People In A Large Group !” Unknown
  Before I make my statement I want to clarify that I am not a G7 member, but I respect them. I wrote this replay as a concerned Ethiopian citizen. I have read a few articles in the past by Girma and they have equally disappointed me. I respect him because he is relentlessly unintelligent but diligently try to bend public opinion. This shows that democracy works and we allow unintelligent people to express their ignorance in a public forum.
  It is obvious, the purpose of Girma’s article is to create doubt and to divide the G7 support group. Maybe some of the people who would be influenced by his article would join some other political groups. If that happens it is great for G7 filtering out the stupid people in their group.
  What would be the result of this? A weaken G7 and a stronger Woyane. Girma, you can’t have it both ways. So, do you currently work for Woyane or opposition groups? Maybe you didn’t write it at all. I am assuming you copy paste it from Aiga “stupid” Forum.

 5. Tulu Kassa Reply

  December 12, 2013 at 12:18 am

  Ato Girma is so much worried what G7 is doing. Had it been a positive concern, I would have give him a proper respect.He proudly talks about the past Kineget rise and failure.He is advising G7 to follow the same path that Kiniget passed through. If he opened his mind and look the true cause of the failure of peaceful method of struggle in ethiopia, Kinget is a perfect example. You are still preaching that a peaceful method of struggle in Ethiopia is the prefered method. In a country where the opposition party is hard to find a rental hall to have organization assembly;I do not see how it would be possible to call millions of people to assemble in the peoples square under the current political reality.The only freedom that the so called opposition parties are allowed to have in that country is the air that they breath. Ouside this they have nothing to show that the current political setup allows them an environment that is free and fair for for them to compete and bring meaningful change. If you are advising other organization like G7 to fall in the same trap,I do not think you will acchive that. Nice try. Ato Girma, if you can not fight them you can join them.

 6. koster Reply

  December 11, 2013 at 8:10 pm

  ay ye SEYE dekemezmur

 7. Kebede Reply

  December 11, 2013 at 5:50 pm

  ግርማ ካሳ ለእውነት ክብር ካለው አማኑኤል ዘሰላም እኔ ነኝ ይበል:: ለማወጣጣት አይደለም::እኛ እናውቃለን:: ግን ለህዝብ በአደባባይ ውነቱን ይናገር:: በኮድ ስም ለመጻፍ ለምን አስፈለገ? ወያኔ መጥቶ አይገለው? ከማን ለመደበቅ ነው? ከእኛ ከጽንፈኞቹ?

  አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ ጽሁፍንም ጨምሮ ስሙንና ፊርማውን በግልጽ ካላስቀመጠ አያምንበትም ማለት ነው:: ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለእዳ አይቀበለውም የሚባለው ለዚህ ነው::እርሱ ራሱ ግርማ ካሳ ያላመነበትን ለኛ የሚደሰኩርልን ምን ዓይነት አርቲፊሻል የሆነ ሰው ነው? እንግዲህ አድርባዮች ሁሉ እንዲህ ናቸው:: የማያምኑበትን ሕሊናቸውን በመሸጥ ነው የሚኖሩት እስከግዜው ድረስ::

  ግርማ ካሳ ወይም አማኑኤል ዘሰላም እንደአሁኑ ለወያኔ ሳያድርና ሕሊናውን ሳይሸጥ የጻፈውን ከታች ያለውን በመጫን ይመልከቱና ይፍረዱ::

  http://www.ethiomedia.com/adroit/our_neda.pdf

  ግርማ ካሳ ወይም አማኑኤል ዘሰላም ወይም አማኑኤል ዘወያኔ ሕሊናውን ከሸጠ በሗላ የጻፈውን ደግሞ ከዚህ በታች ይመልከቱ::

  http://erigazette.org/?p=4429

  እነዚህን ሁለት የግርማ ካሳን (አማኑኤል ዘሰላም) ጽሁፎች አነጻጽሮ ጥሩ ግምት ላይ የማይደርስ አእምሮ ያለ አይመስለኝም::

 8. maru Reply

  December 11, 2013 at 2:43 pm

  girma kassa is a sick retarded and moron guy who has no clue except deep hate against dr birhanu and other g7 members as same as the members of qale stupid room arrogants, and we should forget these idiots as they can not do anything except echoing thier nonsense 24/7

 9. bekele Reply

  December 11, 2013 at 2:20 pm

  don’t give attention for girma. I got information from Chicago he is not normal. I have a problem the website manger to posted his comment or non sense writting. leave G7 fight tplf. you guys do your job instead of insult G7.don’t waste time, iu am telling you guys tplf doesn’t give power by demonstration or peace full struggle. we have to armed and fight.

 10. samuel Reply

  December 11, 2013 at 1:48 pm

  የአቶ ግርማ ካሳን ሃሳብ በአሁኑ ጊዜ ለመቀበል በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም የፖለቲካው ወቅታዊ ሁኔታ የቼዝ ጨዋታ አይነት ሆኗል። እስኪ ወደ ኋዋላ መለስ ብለን እናስታውስ፦ ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በዲሞክራሲ መንገድ ምርጫ ይካሄዳል ብሎ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች አምነው ነበር። እኤአ ከ 1991 እስከ 2005 ድረስ ህዝብን 10 አመት አዘናጋ ከዚያም ሰላማዊ ሰዎች ጨፈጨፈ። ከዚያ በኋዋላ 13 አመቱን ይዞአል። 10+13=23 ሃገር በማዘረፍ ንፁህ ዜጎችን በመግደል በማሰር በዘረኝነት አድሎአዊ ፖለቲካ እያካሄደ ነው።
  ለአቶ ግርማ ካሳ ቀላሉ ምሳሌ ኔልሰን ማንዴላ ይመሩት ስለነበረው ANC ፓርቲ የተጠቀመባቸው ታክቲኮች በሰላምም በትጥቅም ትግል ነው። እንዲሁም ከማንኛውም የውጭ ሃይሎች እርዳታ በማግኘት ጭምር ነው።
  ለምሳሌ ያህል፦ በ1947 እኤአ 3ት አይሁዳዊያኖች ፋይናንስ አድርገውለታል። እነሱም Lithuanian Jew Sidelskogo Lazarus and his partners in the law firm of Mr Witkin and Eidelman. the world investment giant “Solomon Brothers” was the main customer of this small Jewish firm.በ1952 እኤአ ለ H.M. Basner law company መስራት ጀመረ። ማንዴላ የሰላማዊ ትግል ብቻ በቂ ስላልሆነ በ1950ዎቹ አካባቢ ከኢትዮጵያ ሌላ በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትር አቋርጦ አልጄሪያ ለ 2 አመት ወታደራዊ ስልጠና አድርጎአል። በ 1964 በሚሰራበት የአይሁዶች የጠበቃ ካምፓኒ ውስጥ እየሰራ ሳለ ነው እሱንና ሌሎችንም ጓደኞቹን እንዲሁም የሚረዱትን አይሁዶች ይዘው ለፍርድ ቤት ያቀረቡአቸው። ከተያዙት ውስጥ Denis Goldberg, Lionel Bernstein, Bob Hepple, Artur Goldreykh, Garolyyu Volp and Jaymz Kantor.ፍርድ ቤት የቀረበው ማንዴላ ብቻ ነበር። ሌሎቹ አመለጡ። እዚያ ባለው የእንግሊዝ ኤምባሲ አማካኝነት ወደ ሎንደን አመለጡ። ማንዴላም 27 አመት ተፈረደበት። ከዚያ ሁሉ መከራ ያመለጡት የማንዴላ ተከታዮች ጫካ ገብተው ታግለው አፓርታይድን ያሸነፉት። በሰላም ትግል ብቻ ከሆነ ግማሽ እድሜህን እስር ቤት ታሳልፋለህ። ለአቶ ግርማ ካሳ የምመክረው አቶ ተድላ አስፋው ግልጽ ደብዳቤ ለAmbassador Jendayi Fraze እንደጻፈው ሁሉ ለArtur Chaskalson:Chairman of the commission of experts. International Commission of Lawyers (Geneva), committee against tortures, the center of development of democracy and human rights.ግልጽ ደብዳቤ በሃገራችን ስለሚፈጸመው ወንጀልና ዘረኝነት ብትጽፍ መልካም ነው እላለሁ። ምክንያቱም ከማንዴላ ጋር ዘረኝነትን አብሮሲታገል የነበረ ነው።
  አቶ ግርማ ካሳ እኔም እንደርስዎ አስባለሁ ነገር ግን ከባዶ መሳሪያ ይዞ መከላከሉ ይሻላል። የግንቦት7 ፓርቲ የነጮችን ስውር ደባም ማስታዋል አለባቸው ። አሁንም ምሳሌ ማንዴላ፦ ማንዴላና ሌሎቹም በፖሊስ የተያዙ ጊዜ ሚስጥራዊ ዶክመንት ተገኘ። There were plans of “Operation Mayibuye” and the Umkhonto we Sizwe organization plans. The operation “Mayibuye” was developed intelligence services France and Great Britain and had the purpose destruction of the Republic of South Africa as the states. ግን ኔልሰን ማዴላ ይሄን ነገር አላደረገውም።ምክንያቱም ሃገሩን ይወድ ነበር። ስለዚህ ግንቦት7ቶች የነጮችን ስውር ደባ በጥንቃቄ አስተውሉ።
  አንድ የመጨረሻ ምሳሌ፦Zbigniew Brzezinski-United States National Security Advisor ሶቪዬት ህብረትን ከውስጥ ሆኖ የሚያፈርስልን ሰው አለን (ጎርባቾቭ) ሁለተኛው ሰው ደግሞ በዲሞክራሲ ስም ቀውስ የሚፈጥር መሪ ይመጣል(የልሲን) 3ተኛው ሩሲያን የሚበታትን ይመጣል(ጄኔራል ሌቤድ) ይህንን የሚስጥር ዶክመንት ሩስኪዎች አገኙት። ከዚያ በኋላ ጄኔራል ሌቤድ ባልታወቀ ሁኔታ ሄልኮፕተር ተከስክሶ ህይወቱ አልፎአል። ሩሲያም አልተበታተነችም። በዚህ ጉዳይ ላይ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር የነበረው ፓቬል ግራቾቭ ኢንተርቪው ሰጥቶበታል።

 11. Dagafa K Reply

  December 11, 2013 at 5:12 am

  Girma kassa smells like Dawit Kebede. Her ego again, this person was first joined Kinigit and then left partially by Shawel & Lidutu. May be someone like Dawit Kebede also played roll. Then he was sent to USA to infiltrate opposition forces and popular media like EAST. But, this time, he was unable to infiltrated opposition. Finally he returned to his comfort zone turn his weapons against G7.
  Kebede can say what ever he says, the train will never stop moving…

 12. zewdu Reply

  December 11, 2013 at 3:31 am

  Hallo Mr. Girma, we all agree on you have the right of opinion.That really doesn’t mean that your leader ship is required. I suggest you are good with your choice of struggle for your self, the problem is your prescription for the others, looks a little imposition. please, please, if you think that way is the only way out for the problem, that we all face, please go for it and proof it. please, keep in mind that we are watching as you do sir, journalists and politicians are currently suffering in the jail are not in their vacation some where in a resort area. these people believed the same principle as you do given their constitutional right of doing what they did that led them to where they are now.
  please, remember we are dealing with a kind of apartheid system that requires eradication with out any ha-station.

  you have seen, how these arrogant,s treated those peaceful protesters who didn’t even carry a stick on their hand. how do you explain the beating in front of the Saudi embassy? how do you explain the situation with the Graziani thing?
  My Dear Girma, please, may god bless your journey of no where. please take your choice for your self. Your prescription is nothing other than a tab… that will kill.
  Good luck

 13. qititu Reply

  December 10, 2013 at 6:55 pm

  At Girma Kassa must have been crossed-eyed on his mind’s eyes. Short and clear; We Ethiopians have profound respect and a firm believe in the excellent leadership of the men and women in Ginbot 7;we shall continue to support the movement in all aspects of contributions that this people’s movement shall achieve the goals; the goals of freeing our country and people from fascist woyane.

 14. Satenaw Reply

  December 10, 2013 at 4:20 pm

  አቶ ግርማ ካሳ (ጉዱ ካሳ)

  ደሞ ብቅ አልክ! ለምን ልከውት ይሆን ብዬ ሳስብ ያው እንደጠበኩት ሆነ ነገሩ::እስከመቼ ነው የኢትዮጵያውያንን ሃቀኛ ትግል ለማደናቀፍ ያላሰለሰ ጥረት የምታደርገው? ወያኔ የቤት ሥራ እየሰጠህ በላከህ ቁጥር እየመጣህ የምታስታውክብን አንገፍግፎናል::ስለ ግንቦት 7 ከወያኔዎች የበለጠ እንዲህ የሚያስጨንቅህ ምክንያቱ ምንድነው? አሁን አንተ ቁጭ ብለህ ብታስበው ወያኔ የሚባለው ሰይጣናዊ ሃይል በሰላም ይወርዳል ብለህ ታስባለህ? ለአንተና ለሞኝ ጓደኞችህ 23 ዓመት 23 ቀን ነው መሰለኝ:: መቼ ነው የምትማረው? ስንት ጊዜ በቂ ነው ለመማር ላንተና ለጓደኞችህ? ወይስ የወያኔን እድሜ ለማራዘም በቅጥረኛነት እያገለገልክ ነው እንደተለመደው?

  ለማንኛውም እስቲ አንድ ነገር ልጠይቅህ:: አንተ የመረጥከውን የትግል መንገድ ለመከተል መብት ሲኖርህ ግንቦት 7 ለምንድነው የራሱን ስትራቴጂ የመቀየስ መብት የሌለው? ወይስ አንተ አምላክ ነህና የምትለው ሁሉ ትክክል ነው:: ሁሉም ሰው ያንተን ሃሳብ መቀበል ግዴታው ነው? አይገርምም:: በወያኔ ላይ ማተኮር ሲገባን አሁን ኢትዮጵያ እንደገባው የውስጥ አርበኛ ዳዊት ከበደ አንተም ግንቦት 7 ላይ እንደወያኔ ማነጣጠርህ ለመሆኑ ጉዳዩ ምንድነው? ደሞዝህስ ስንት ነው ለመሆኑ? ላለፉት ቡዙ ዓመታት ተከታትለንሃል:: የሚገርምህ ነገር መቼ ብቅ እንደምትል እናውቃለን:: ብቅ ስትል በሳቅ እንሞታለን:: አንዱ ሰሞኑን ግርማ ካሳ ብቅ ይላል ሲለን ልክ እንዳለው ከተፍ አልክ::አንተ ጠንቋይ ትቀልባለህ ወይ አልነው? እርሱም አንድን ሰው በደንብ ስታውቀው ቡዙ ነገር መተንበይ ትችላላህ አለን::ለምን ልክ እንደ ጓደኛህ እንደ ዳዊት ከበደ ኢትዮጵያ ገብተህ አይለይልህም? ተወን እባክህ ተነቃቅተናል:: ወያኔን ቁጭ አርጎ ግንቦት 7ን ትነዘንዛለህ:: የወያኔ የወስጥ አርበኛነትህን ካወቅን ሰንብተናል::ተስፋ ቁረጥ:: ወይም ሌላ ዘዴ ፈልግ::

 15. fikadu Reply

  December 10, 2013 at 12:47 pm

  Thank you Netsanet.
  How could this Girma loose his sense of balance.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <strike> <strong>