ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ጀርመን ነዋሪ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ !!!!

December 10, 2013

የሰልፉ አላማ

በጀርመን ፓርላማ በኩል ይህን በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመ ኢሰባአዊ ድርጊት ወደ አውሮፓ ህብረት እንዲሁም ወደ ተባበሩት መንግስታት እንዲደርስ ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ እና የሕዝብ ድጋፍ ለማግኘት ለሰባአዊ መብት የምንቆረቆር በሙሉ በዚህ ሰልፍ ላይ ተገኝተን የተገደሉትን የተደፈሩትን ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ እንታደጋቸው ያስችለን ዘንድ በጀርመን ነዋሪ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በአክብሮት ጥሪ እናደርጋለን ::

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ በጀርመን!!

Protest in German

 

One Response to ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ጀርመን ነዋሪ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ !!!!

 1. AbiyEthiopiawi Segawi-Wemenfesawi Reply

  December 10, 2013 at 1:23 pm

  ሽልንጌን ይላሉ።

  እነዚህ ይሁዳ፤
  ልባቸው ያልጸዳ፤
  ሰው ላስገደሉበት፣በደም ይበላሉ፤
  ጊዜ እየጠበቁ፤ሽልንጌን ይላሉ።
  ደሞዜን ሂሳቤን ያስገደልኩበትን፤
  ሕሊናዬን ስሸጥ ልቤ የደማበትን፤
  ሳምንቱ ዛሬ ነው”ይከፈለን”ብለው፤
  ደግሞ ይገላሉ ገንዘብ ተቀብለው።
  ገንዘብ ነው ጌታቸው፣
  አምላክም የላቸው፤
  ማንም ሰው ይገደል፤
  ይደፋ ይሰቀል፤
  ድፍት ብሎ ይቅር፣
  ሳይታወቅ ቅር-ቅር፣
  ዝም ጭጭም ይባል አስተዋሽም ይጥፋ፤
  የሰዉ ደምም ቢፈስ፤ፈሶም ቢከረፋ፤
  “ምን አገባን”እኛ ባደባባይ እያሉ፤
  ሕዝብ የሚያስገድሉ ከጎናችን አሉ።
  ለማታውቁ ሁሉ፤
  ሽልንጌን ይላሉ።
  ሰብ-ዓዊነት ብሎ መብትና ነፃነት፤
  የሰው ፍቅርን ክብር ዛሬ ለእኩልነት፤
  አህያውን ፈርተን
  ለምን ዳውላውን?እንወቅ ለይተን፤
  ዘርፈው አዘርፈው ሕዝብ እየገደሉ፤
  በአገራችን ንብረት፣ሐብታም ነን የሚሉ፤
  ሰርተው-ያገኙት ሳይሆን ከድሆች አፍ ነጥቀው፤
  በሚሊዮን ገድለው በሚሊዮን ሰርቀው:-
  ደማችንን መጠው፣መጠው ሲያስመጥጡን፤
  ያውም ሳውዲ ልከው በዶላር የሸጡን፤
  አልበቃ ብሏቸው እያስቀጠቀጡን፤
  ከግድያ ስንተርፍ በቁም-መሞት ቀጡን።
  ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።
  እነዚህ ይሁዳ፤
  ልባቸው ያልጸዳ፤
  ሰው ላስገደሉበት፣በደም ይበላሉ፤
  ጊዜ እየጠበቁ፤ሽልንጌን ይላሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <strike> <strong>