ወያኔ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመት መታሰብያ በዓል እንዳይከበር ፍቃድ ከለከለ

December 4, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመትን በተለያዩ ዝግጅቶች አስቦ ለመዋል በጃንሜዳ የመሰብሰብ ፍቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ ይሁንና መንግስት ጥያቄውን ተልካሻ ምክንያቶችን በመደርደር ውድቅ ማድረጉን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሰማያዊ ፓርቲ ልኳል።

Semayawi party, Addis Ababa

brhanutekleyared

የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡

እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?

ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!

6 Responses to ወያኔ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመት መታሰብያ በዓል እንዳይከበር ፍቃድ ከለከለ

 1. H kirross Reply

  December 6, 2013 at 2:49 pm

  Tire liberation front , led by the dead fascist zenawi MAIN AGENDA was to liberate tigre. since marching to addis ababa they have been working 24/7 to dismantle Ethiopia. TPLF do not think that they belong to Ethiopia. that is why Ethiopian history does not mean any thing to tplf.

 2. andnet berhane Reply

  December 6, 2013 at 2:25 pm

  የታሪክ ማንነትን በመናቅ የሚደረግ እብሪት በዝምታ የምታለፍ ሳይሆን በተግባርና በማንነት ጥያቄ ላይ ያተኮረ በመሆኑ መልስና የሚደረገውም ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ የሚመለከት ባለመሆኑ የታሪክ ወራሹ ሕዝቡም ይህን ትኩረት በመስጠት ያለ ፍራቻ ወጥቶ የአፄ ምኒሊክ እረፍትን ማክበርና ሀገራዊነቱን ማሳየት ይኖርበታል፡ ወያኔ(ኢሕደግ)የግል ንብረቱ ለማድረግ የሚፈልገው ኢትዮጵያ ሃገራችን እሁላችን መሆናንና እኛም ባላገሮች መሆናችንን በድፍረት በጽናት ማሳየት ይጠበቅብናል፡
  ይህ እብሪት መተንፈስ ይገባዋል ታፍኖና በይሉንታና ልጆቼን ምን ላብላ ስደት አልሄድም እያለ የሚቀባጥረው ካለበት እስኪጨልምበት ይቀመጥ የሰቆቃ የመብትና የንሮ ጫና ያለበት የሚጠብቀው አማራጭ አንድና አንድ በመሆኑ መብቱንና ነጻነቱን ማስከበር የግድ ይለዋል ሰላማዊ ትግል አስፈላጊ ነው ነገርግን በተናጠል ሳይሆን በአንድነት ውጤት ስላለው በምሳሌነት የሚጠቀሱት በታይላንድ በከቭ እየተደረጉ ያሉት ህዝባዊ ሰላማዊ አመጾች መማርና ራሳችንን አዘጋጅተን በአንድነት የምንነሳበት ወቅቱ አሁን በመሆኑ ከወያኔ የምንጠብቀው ምንም የተለወጠ ባህሪ ስለሌለው እንድሚባለው (ካይጥ ምን ይጠበቃል ) የሚለው በቂ በመሆኑ ሕዝብ የስልጣን ባለቤትነቱን ማስመስከር ይኖርበታል ይህ ጊዜ ማብቃት ይኖርበታል በቃ!በቃ!እቃ!ታሪክ አይሻርም ባለታሪኮች አይሞቱም ትውልድ ሲዘክራቸውና ሲኮራባቸው ይኖራሉ
  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝቦች
  ውድቀት ለምባገነነኖች ለትምክህተኞችና እብሪተኞች
  ኢትዮጵያ በነጻነት በክብሯ ለዘላለም ትኑር

 3. semail Reply

  December 5, 2013 at 1:38 pm

  it is not surprising that the fascist woyane who:
  - banned demonstration against Mussollini’s attrocities on the Ethiopian people
  -beat up demonstrators who stood up against saudi barbarism on our people
  - who has put Ethiopia on sale on the world market,

  has banned demos in honour of Menelik. The TPLF bandas whose parents served as porters and house servants for Mussolini’s soldiers cannot be expected to do otherwise.

 4. Sergute Selassie Reply

  December 5, 2013 at 12:41 pm

  የሰማያዊ የማያቋራጥ የፅናት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የወያኔን ዝርዝር ሆድ ዕቃ ለህዝብ እያጋለጠ የወያኔን መሰሪ የመንደር ወይንም የጎጥ መርህ እያሰዬ ነው። ሰማያዊ በር ሲዘጋ በመስኮት፤ መስኮት ሲዘጋ በጣሪያ …. ጣሪያ ሲዘጋ ከመሬት በታች …. በትጋት ሰላማዊ ትግላቸውን ቀጥለዋል። ሰማያዊ ተከለከልን፤ ታሰርን፤ ተደበደብን፤ ተዘረፍን፤ ተገለልን ብለው ለአፍታም ከተነሱበት ሰፊ ህዝባዊ ዓላማ አልታቀቡም። እውነት ለመናገር ይህ የሰማያዊ አብነታዊ ጉዞ አዲስና መምህርም ነው። ፀጥ ረጭ ብሎ የነበረውን የመከራ ሸክማዊ ዘመንንም ጥሰት በመስዋዕትነት አቅልመውታል።

  እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 5. በለው! Reply

  December 4, 2013 at 5:08 pm

  -”በአንድ ወቅት የቀዳማዊ ኀይለስላሴን ሙት ቀን ለመዘከርና ለእራሳቸውም ማስታወሻ የሚሆን መታሰቢያ ሐውልት እንዲቆም ጉዳዩ የሚመለከታቸውና ቤተሰቦቻቸው እኛ የሞቱ ጠ/ሚርን በጠየቁ ግዜ…እንዲህ ብለው መልስ ሠጡ፡፡ (፩)”አፄው ከሞቱ ብዙ ግዜአቸው ነው የምትጠሯቸውም ሰዎች ግራ ይጋባሉ… * የሚሰራው ሀውልት ግን….!
  (፪)አጼው ሲሞቱ በሥልጣን ላይ አልነበሩም ከሥልጣን ወርደው ነው የሞቱት፡

  (፫)ሐውልት እንዲሰራበት ተጤቀው ክልልና ቦታው የሌላ ብሔር ስለሆነ ሌሎችን ሊያስቀይም ይችላል፡ለመታሰቢያነት ግን ትንሽ ነገር ያለ ፎቶ ቢቆም ክፋት የለው”
  ***********
  አሃ! ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ በቁማቸው በነሐስ ሐውልት ያሰሩት ክልሉ የእሳቸው ነው።ታጋይ ህወአት እና የአሜሪካ ምሁር ስለሆኑ ነው። ብሔር ብሔረሰብ መነገጃነቱ ይህ ነው።”ተጨቁነህ ማንነትህ ሳይታወቅ እና በማኒፌስቶ የፈጠርንህ ሲባል የሚፈነጥዘው ለዚህ ነው።
  *ህወአት ማኒፌስቶ(ሕገመንግስቱ)አንድ ገጽ ተኩል ሥልጣን አስተቀለላቸው ተጠቅላይ መልስ ዜናዊ እነዴት በዘጠኑም ክልል ለመቀበር ቻሉ። ታጋይ አይሞትም!ምንአልባት መለስን የገደሏቸው ከሥልጣን ሳይወርዱ ሞቱ ብለው በሀውልት ሊያንበሸብሻቸው ነው ማለት ነው።እውነትም እራዕዩን እናስፈጽማለን!?ፈፀሙባቸው በለው ወይ ጥጋብ!

  ዛሬም ነገም ኢትዮጵያ የማን ናት!?”የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ” አለ

  **ለጠላታችን ግራዘያኒ መታሰቢያ ሐውልት መቆም ተቃውሞ ካልተወጣባት **ወገን ላሠረ፣ ለገረፈ፣ለደፈረ፣ሰደቅን ላንቋሸሸ፣ሉዓላዊነትን ላዋረደ፣ዓረብ ኢትዮጵያዊው ሕዝባዊ ተቃውሞ ማሰማት ከተነፈገ ከታሠረ ከተደበደበ፤ ኢትዮጵያ አለችን?
  *ግለሰቦች የራሳቸውን ሥምን ዝና ሐውልት በእየሙዚየሙ ከሰቀሉ፤ ሳይሞቱ ምስላቸውን ቀርጸው ማስመለክ ከቻሉ በእርግጥም ህወአት ብሔር ብሔረሰቦችን የቁም ከብት አድርጓቸዋል። በሬ ከአራጁ ይውላል ማለት አደለም!
  **ለመሆኑ ይህ የቀድሞ መሪዎቻችሁን አታስታውሱ ታሪክ ተፅፏል፤ ሀገር ፈርሶ ክልል ተገንብቷል ወጣቱ ሁሉ የተደቀለው በህወአት ነው ማለት ይሆን? አዲሲቷ ሀገር በመፈቃቀርና በመከባባር በአንድ ፖለቲካ ጥላ ሥር ተንበርክኮ የህወአትሻቢያ አሽከር መሆን። የ፻ዓመት ታሪክ፣የሚሊኒየም ክብረ በዓልና የሚሊኒየም ግብ(ጉድጓድ)
  **ለህወአትሻቢያ መስቀል አደባባይ ለብሔር ብሔረሰብ ጃንሜዳ ተብሎ የተወሰነው ተሻረ ማለት ነው።ይህንን የሚሰራው የህወአት ግራ ክንፍ ሙስና ሻንጣ ተሸካሚው ኦነግና ኦብነግ ብአዴን(አማራ መሳይ ዲቃሎች ማህበር)መሆን አለባቸው። ይቺን ካልተቃወሙ ይጋለጣሉ! ይባረራሉ! ይታሠራሉ! ይገደላሉ!አድርባይ አሉ ወ/ሮ አዜብ ይህ በእነ እነድሪያስ እሸቴ(ጣረሞት) ሆድ-አደር ምሁር ተብዬዎች የተቀመመ መርዝ ነው። በትግራይ ተወላጆች ሚሰራ ብቻ አደለም። ሸዋ እጅህን አላግባብ አንድ ቦታ መቀሰርህን አቁም ጠላትህ በሁሉም ቤተሰብና ክልል ብሔር ውስጥ ነው። እራስህን ፈትሽ!ንቃ ተደራጅ!
  “የፎቶግራፍ ኢግዚቪሽንና የፓናል ውይይት ለማካሔድ የተመረጠው ቦታ ጃንሜዳ ውስጥ ለፀጥታ ትበቃ አመቺ ባለመሆኑ የተጠየቀውን ዕውቅና ጥያቄ ዕውቅና ለመስጠት የምንቸገር መሆናችንን እንገልፃለን። ከሰላምታ ጋር!
  **ይህ ቃል ከህወአት ቋንቋ ወደ ብሔር ብሔረሰቦችና ሲተረጎምና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሲተላላፍ: _መረጃና ብጥብጥ አገልግሎት፣
  _ለህወአት ፖሊስ ቡድን ኮሚሽን፣
  _ለአዲስ አባባ ከተማ አስተዳዳር ወንጀል አቀነባባሪ ፖሊስ ንዑስ ኮሜቴ ከምስጋና ጋር!

  “ዝግጅቱ እምዬ ምንይልክን አስታኮ ቦንብ ለመቅበር፤ አዘጋጆችን ለማሰር፤ ተሳታፊውን ለማሸበር ዘግጅቱ ብዙ ወጪ አለው ጥቅሙ ይህን ያህል ፊልም ሊያሰራ ብቁ አደለምና ተረጋጉ፣ እናንተም አዘጋጆች የእኛን ጉልበት የሚመጥን ብጥብጥና ሁከት ሊፈጥር የሚያስችል ብዙ አድር-ባይ፣ ካድሬ፣ ሌቦችን፣ ሊያሳትፍ የሚችል ደመቅ ያለ ትርፋማ ሆነ ዝግጅት አዘጋጁ በማለት ተከለከለ የሚል ትርጓሜ አለው። ዘመኑ ሥራ መክፈት ድህነትን ማታገል አደለም!?

  **ጎበዝ የዚህ ዘመን ባንዳ ከመቼውም በበለጠ በቂ እርምጃ ያለ ምህረት ሊወሰድበት ይገባል።ኢትዮጵያ መጨረሻው መስቀልኛ መንገድ ላይ ናት እናልፋለን ወይም እንጠፋለን።እምዬ ምንይልክ በመላው ጥቁር ሕዝብ ልብ ውስጥ ይገኛሉ ይኖራሉ ይከበራሉ!። አሁን የሀገር ሉዓላዊነት ፣ዜግነት፣ የትውልድ ምንነት የመከነበትና የባከነበት፣ሰንደቅ የተዋረደበት የጠፋበት ወቅት ላይ ነንና!ሀገር ሲድን ታሪክ ይተርፋል!!ቅድሚያ ሀገርን ለማዳን ሙሰኛን፣ አድርባይ፣ አስመሳይ፣ሆድ-አደርን፣ ሌባን፣ ከአካባቢህ አጥራ!ሸዋ ተበላህ በላው። ሠላም ለሁሉም! ስለማንነታቸው የሚያውቁ ሁሉ ስለ ታሪክና ሀገር ይጨነቃሉ!!አለበለዚያ ተናጋሪ እንስሳ ሆኖ እየበሉ ለመኖር ሳይሆን ለመብላት መኖር ይባላል በለው!። ይታሰብበት በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <strike> <strong>