Recent Posts

Ethiopia First Hijrah Foundation

የውስጥ ጥላትን መከላከል ወሳኝ ነው! (ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን)

ቀጣዩ የወያኔ አረመኔያዊ መንግስት ቅንብር ደግሞ የሙስሊሙ መሪዎች ይቅርታ በውጭ አገር በሚኖር የሙስሊም ድርጅት እንዲጠየቅላቸው እና ሁሉም ከእስር እንዲለቀቁ ከዚያም ትግሉ ለዘላለም እንዲጠፋ መንግስትም ከተጠያቂነት ቅሌት እንዲተርፍ ለማድረግ ነው። ይህን አይነት ክህደት ለመፈጸም ከመንግስት ጋር ለመተባበር የትኛው የሙስሊም ድርጅት ሊታጭ ይችላል በማለት የዳያስፖራው ህብረተሰብ ሲጠያየቅ ለሳምንታት ቆይቷል።

Read More »
ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

ለልጅ የሳቁለት፣ ለውሻ የሮጡለት፣ ለፖለቲከኛ ያጨበጨቡለት (ይገረም አለሙ)

አንደኛ የፓርቲው አመራሮች ያልተናገሩትን ሁለተኛ በዚሁ ምክንያት አያሌ የፓርቲው አባላት በእስር ላይ እያሉ አቶ ጀዋር ህዝባዊ እንቅስቃሴው በኦፌኮ አንደተመራ መናገሩ ምን ይሉታል፡፡ ፓርቲውንና አመራሮቹን እየከሰሰ፤ በታሰሩትም ላይ ምስክርነት እየሰጠ መሆኑን ተገንዝቧል፡፡ ጭበጨባ ያሰከረው ፣አጉል ውዳሳና ሙገሳ ያሳበጠው ፖለቲከኛ እንዲህ ነው ነገር የሚያበላሸው፡፡

Read More »
ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

እንደገና መሬት ላራሹ! (ገለታው ዘለቀ)

በኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ጉዳይ፣ የመሬት ላራሹ ጉዳይ ሙሉ መልስ ጠፍቶት እነሆ ግምሽ ምዕተ ዓመትን ፈጀብን። ዛሬም ግን ይህ ጥያቄ እንደገና ተቀጣጥሎ እልባት ካላገኘ አገራችን ከችግር ትወጣለች ማለት የማይሆን ነገር ነው።

Read More »
Ethiopian Border Affairs Committee

ለኢትዮጵያውያን ምንም የሚቀር ሀገር የላቸውምን? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

የድንበር ማካለል የቴክኒክ ኮሚቴ ኃላፈው አብደላ አል ሳዲቅ እንዲህ ብሏል፡ “ለሁለቱ ህዝቦች ትብብር ያግዝ ዘንድ የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ገበሬዎች የእራሱን መሬት እንዲያርሱ ፈቅዷል፡፡ ሆኖም ግን ኢትዮጵያ አል ፋሺጋ በሱዳን ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ መሆኑን በጽናት በማመን እውቅና ትሰጣለች፡፡“

Read More »
Professor Berhanu Nega our Muse

ብርሃኑ እንደ ቸርችል- እኛ እንደ እንግሊዞች (ነጋ አባተ- ከእስራኤል)

የእኛው ዶ/ር ብርሃኑም የሲቪክ ማህበራትን፤ ልዩ ልዩ ብሄረሰቦችንና ምሁራንን በጥልቅና በዕውነተኝነት ስሜት የዕንያያዝን ጥሪ አቅርበዋል። ሲቀጥሉም "ምናልባትም በአርበኞች ግንቦት ሰባት የማትደሰቱ ብትኖሩ እንኳን ወደ የፈለጋችሁት የትግል አቅጣጫ ተሰማሩና ተያይዘን ሃገራችንን ከገባችበት አሮንቃ እናውጣት...

Read More »
ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

ዝምታው ይሰበር (ውቢት ዘውዱ ታደለ)

ድሮ ልዩነታችን ውበት እንዳልነበር ዛሬ ኢህአዴግ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የሚዘራውን የብሔርተኝበት ጥያቄ በቃ ልንለው ይገባል፡፡ ትላንት አባቶቻችን በአንድነት ሆነው አስከብረው የሰጡን አንድ ኢትዮጵያ ዛሬም በቆራጥነት አለሁሽ እንበላት፡፡ ይበቃል በል ወገን! እናት ልጇን በረሀብ እያጣች፣ መስኖዎች እየደረቁ፣ መሬት እየተሸጠ፣ ሰው እየሞተ፣ እየታሰረ፣ ሀገር በሰቆቃ እየታመሰች ሳለ ዝምታው ዝምታው ምንድነው? ይበቃል በል ወገን! ዝምታን በቃ ብሎ ከሰበረው የኦሮሞ ህዝብ ጋር እንነሳ፡፡ የኢህአዴግ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ያሴረውን የብሔርተኝነት ሴራ ወደኋላ ትተን ለአንድ ኢትዮጵያ ቃላችንን እናሰማ፡፡

Read More »
Addis Ababa Master Plan

ድንቄም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን? ማስተር ፕላኑማ የዘ-ህወሀት ነው! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የዘራፊ ቡድን (ዘ-ህወሀት) ስብስብ ከህዝብ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ካጋጠመው በኋላ መናገሻ ከተማዋን ወደ አካባቢው የእርሻ መሬት የማስፋፋት ድርጊቱን የሚያቆም መሆኑ ታውጆ ነበር፡፡ “የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን” የማዘጋጃ ቤቶችን እና በመናገሻ ከተማይቱ ያልታቀፉ አካባቢዎችን ስልታዊ በሆነ መልኩ በማካተት ፈጣን የሆነ ግዙፍ የምጣኔ ሀብት የያዘ ከተማ ለመገንባት ነው የሚል ስልትን መርህ አድርጎ የተነሳ ነበር፡፡

Read More »
Prof. Berhanu Nega's town hall meeting in Washington D.C.

የአቶ ግርማ ካሳ ቅዠት (ስንታየሁ በሱፈቃድ)

አቶ ግርማ ግን ለአመታት የሆነ ያልሆነውን ከመጻፍ ውጪ የትኛው ቦታ አልታዩም፡፡ ስለሆነም የሚነግሩን የሚያምኑበትን ከሆነ ወያኔ ርስዎን የሚፈልግበት ምክንያት ይኖረዋል ተብሎ ስለማይገመት (ካለ ይንገሩን) ቀጣዩ ምርጫ ከመድረሱ በፊት በቶሎ ወደ ሀገር ቤት ይምጡና...

Read More »
Protest in Washington DC, against the Killing of protesters in Ethiopia

የተቃውሞ ሰልፎቻችንን በሚመለከት (ዳዊት ዳባ)

ዲሲ ላይ ታላቅ የተቀቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው። በፅሁፍ ለአሜሪካ መንግሰት የምናስገባው አቤቱታ የዘት በአፅኖት ሊታሰብበት ይገባል። ግልፅና ጠጠር ባለ መንገድ ቅሬታችን መያዝ አለበት።

Read More »
Abune Petros was born in 1892 in a farmer family in the city of Fiche

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ወደነበረበት ቦታ መመለስ የህዝቡ ትግል ውጤት መሆኑን ሰማያዊ ገለጸ

በአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ግንባታ ምክንያት ሚያዝያ 24/2005 ዓ.ም ፒያሳ ማዘጋጃ ቤት አካባቢ ከነበረበት ቦታ እንዲነሳ ተደርጎ የነበረው የአርበኛ አቡነ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ከሦስት አመት ገደማ በኋላ ነገ ጥር 29/2008 ዓ.ም ወደነበረበት ቦታ እንዲመለስ የህዝቡ ትግልና ያላቋረጠ ጥያቄ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ፡፡

Read More »
ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

የወልቃይት ባህልና ማንነት — መልስ ለአቶ ሃይሉ የሺወንድም (ከጎሹ ገብሩ)

ተ.ሐ.ህ.ት የወልቃይትን ሕዝብ ትግርኛ በመናገሩ በገመድ ጎትታ ተከዜን አሻግራ ትግሬ መሆን አለብህ እንዳለችው እንግሊዝም አሜሪካዉያንን ቋንቋየን ሰለምትናገሩ የያዛችሁት መሬት በቁጥጥሬ ሥር አዉዬ የፈለኩትን አደርጋለሁ ማለት ትችላለች እንደማለት ነው።

Read More »
ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

የወንድሞቻችን ቅኝ ተገዥዎች አንሁን (ከአንተነህ መርዕድ)

ዛሬ ታላላቅ አፍሪካውያን ከተናገሩት መነሳትን መረጥሁ። አንጋፋው ደቡብ አፍሪካዊ ታጋይ ዴዝሞን ቱቱ “When the missionaries came to Africa, they had the Bible and we had the land. They said ‘Let us pray’. We closed our eyes. When we opened them we had the Bible and they had the land”. ተቀራራቢ ትርጉሙ “ሚሲዮናውያን ወደ አፍሪካ ሲመጡ መጽሃፍ ቅዱስ ይዘው ነው። እኛ ደግሞ መሬት ነበረን። ‘እንጸልይ’ አሉን። ለጸሎት ዐይናችንን ጨፈንን። ጸሎቱን ጨርሰን ዐይናችንን ስንከፍት ግን እኛ መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ ታቅፈን ስንቀር እነሱ ግን መሪታችንን ይዘውት አገኘን” የሚል ነው።

Read More »
ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

“የተናገሩት ከሚጠፋ፤ የወለዱት ይጥፋ “ – ተዓማኒነት (ከሠሎሞን ታምሩ ዓየለ – ካሊፎርኒያ)

ኢትዮጵያዊ ወጥነት ያለው ሥነ ቃል ይመስለኛል። ነገር ግን አላረጋገጥኩም ። አንዳንዴ ሥነ ቃሎችና ምሣሌያዊ አባባሎች ከአገር አገር ይወራረሳሉና ። ተዓማኒነት ስለ ማንነታችን ከየትኛው ጎራ እንድንመደብ የሚያደርገን ሃይል ያለው ቃል ነው። ወይ ከዕውነተኞቹና ከሃቀኞቹ አሊያም ደግሞ ከውሸታሞቹ፤ ከወሽካታዎቹ ፤ ከነዳላዎቹና ቀዳዳዎቹ ተርታ ያስወሽቀናል። ከግለሰብ ጀምሮ ድርጅቶችንም ይዞ በማህበረሰቡ ውስጥ የምንሰጠውን አገልግሎትና የምናበረክተውን ድርሻ ጠቃሚነታቸው የቱን ያህል እንደሆነና ዋጋቸውንም ደረጃቸውንም ለመተመንና ለመስፈርም ፤ ምን ያህል ዕውነትን የተንተራሰና መሰረት ያለው ለመሆኑ ጭምር የሚገልጽ ይመስለኛል። ተዓማኒነት ከዚያም በላይ ሰዎችንም ሆነ ድርጅቶቻቸውንም ሊገልጽ ይችል ይሆናልና የቃሉን ዋጋ ግን በዚህ ብቻ ለመግታት አልሻም።

Read More »
A town hall meeting Berhanu Nega

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የዋሽግቶን ዲ ሲ አካል የጠራው ስብሰባ ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚገኙበት

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለስራ ጉዳይ ከኤርትራ መጥተው በመካከላችን ይገኛሉ። ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የዋሽግቶን ዲ ሲ አካል ሊቀ መንበሩን አግኝታችሁ መወያየት እንድትችሉ በታላቅ አክብሮት ይጋብዛችኋል።

Read More »
UEMSG logo

ሌሊት በመታን ድንጋይ ቀን አንደገምም! (የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት)

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ የሁሉም ሙስሊም ጉዳይ ነው። የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው። በዚህ ዙሪያ የሚደረጉ ክንዋኔዎች ለሁሉ ግልፅና ሕዝብ ያወቀው መሆን አለበት። ሕዝቡም ማወቅ ያለበት፣ ነገሮች ተበላሽተው ከወደቅንና ከተዋረድን በኃላ ሊሆን አይገባውም። ካለፈው ተሞክሮ ትምህርት መገብየትና ላንደግመውም መጠንቀቅ አለብን።

Read More »
Welkait in Gondar, Ethiopia

ወልቃይት ጠገዴ ማነው?

በቅድሚያ ግን ለጠቅላላ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ እነዚህ ለህወሃት ፍርፋሪ የተንበረከኩና የወልቃይት ጠገዴን ማህበረሰብ ህወሃትን ለመሰለ “የቀን ጅብ” አሳልፈው የሰጡ ግለሰቦች እነማን እንደሆኑ ለአንባቢ በመጠኑም ቢሆን ግልፅ ማድረጉ አይከፋምና እነሆ...

Read More »
Ethiopian Border Affairs Committee

ኢንሳ የአየር ላይ ፎቶ በማንሳት ላይ የሚገኘው ለሱዳን ተሰጥቷል የሚባለውን አልፋሽጋ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ መሆኑ ታወቀ

ካለፈው ጥር ወር መግቢያ ጀምሮ የአየር ላይ ፎቶ እየተነሳ ያለው አካባቢ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ” ኢትዮጵያ መሬቱ የእኛ መሆኑን እውቅና ሰጥታለች” በማለት ለአልጀዚራ የተናገሩት አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራው ቦታ መሆኑ ታውቋል።

Read More »
ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

“የቡዳ ፖለቲካ” ዶ/ር መረራና አቶ ግርማ (ይገረም አለሙ)

ለዚህች ጽሁፍ መነሻ ምክንያት የሆነኝ አቶ ግርማ ሰይፉ የዶ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ እና መቀበል ያቃተው መራራ እውነት በሚል ርዕስ ያስነበቡን ጽሁፍ ሲሆን ርሳቸው ለጽሁፋቸው ምክንያት የሆናቸው ደግሞ “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” የሚለው የዶ/ር መረራ መጽሀፍ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

Read More »
Resolution from from Los Angeles

በሎስ አንጅለስና አካባቢዋ የምንገኝ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የጋራ አቋም መግለጫ

ጥር 14, 2008 ዓ.ም (January 23, 2016) በሎስ አንጅለስ ከተማና አካባቢ የምንሮር አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ተሰባስበን በወቅቱ የአገራችን ሁኔታ በተለያዩ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ አገራችን ያለችበትን አደገኛ ሁኔታ በቂ ግንዛቤን ከአስጨበጡን ተጋባዥ ምሁራን ጋር ሰፊ ውይይት በማካሄድ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በኦሮምያ ክልል የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው በገዥው ቡድን ሕይዎታቸው ለተቀጠፈ ወገኞቻችና በጎንደር 1ኛ ከሱዳን ከታጠቀ ኃይል ጋር 2ኛ ከወያኔ የታጠቀ ኃይል ጋር 3ኛ ወያኔ በፈጠረው የከፋፍለህ ግዛ ተንኮል በቅማንትና በአማራ መካከል በተደረገው ግጭት ሕይወታቸው ለተቀጠፈ ወገኖች የፀሎትና የመታሰቢያ የሻማ ማብራት ዝግጅት አድርገን የሚከተለውን ባለስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል።

Read More »
Trondheim Ethiopians protest

በኖርዌይ፣ ቱሩንዳሄም ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ

በኦሮሞ ኢትዮጵዊያን ኮምኒቲ በትሮድላግ አዘጋጅነትና የዲሞክራሲያዊ ለወጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ኖረዌይ ትሩንድላግ ቅርንጫፍ ጽቤት ትሩንዳሄም አባላት በተጋባዥነት በተገኙበት፣ በዛሬው እለት ጥር14፣2008ዓ/ም በረዶና ቅዝቃዜው ሳይበግራቸው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በትሩንዳሄም ከተም በማድረግ ፍቅርንና አንድነትን ለማይዎደው ለትግራይ መንድርተኛ ነጻ አውጭ(TPLF) በደያስፖራ ደጋፊዎች ቅስም በምስበር አንገት አስደፍተው ውለዋል።

Read More »
People-to-People Forum

እኛ ለኛ ሕዝባዊ መድረክ!

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) እሁድ የካቲት 6፤ 2008ዓ.ም./ February 14, 2016 ከ1:00 - 5:00 PM በሚያደርገው የእኛ ለእኛ ሕዝባዊ ውይይት ላይ እንዲገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

Read More »
ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

መተባበር በተግባር (ይገረም አለሙ)

ከፖለቲከኞቹ ትግል ይልቅ የተጠራቀመ ብሶት የቀሰቀሰው የህዝብ ቁጣ ወያኔን አንበርክኮት የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ያለውን ካልፈለጋችሁት ትቸዋለሁ፣ ካልወደዳችሁት አይተገበርም እስከማለት አድርሶታል፡፡

Read More »
UEMSG logo

የወያኔ “የማንቂያ ደወል” ደኩሜንታሪ — ውሸት ሲገነፍል!

ወያኔ በራሱ አንደበት የደህንነት አባል ነኝ ብሎ የተናገረ ግለሰብና በእሥር ላይ ያለ ወንጀለኛ ግለሰብ ሳይቀር ምንም የሃይማኖት ዕውቀት የሌላቸውን ቦዜነዎች እንደ እስልምና እምነት ምሁራንና ተንታኞች አርጎ በደኩሜንታሪው አቅርቧቸዋል።

Read More »